
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት መካከል የተደረሰውን ስምምነት አደነቁ፡፡
ዋና ጸሃፊው ስምምነቱን አስመልክተው በሰጡተ መግለጫ ፥ በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል ጦርነቱን በዘላቂነት በማቆም የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን በደስታ እንቀበለዋለን ነው ያሉት።
ስምምነቱ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወትና ለሁለት አመታት ያስቆጠረውን ግጭት ለማስቆም ወሳኝ የመጀመሪያ እርምጃ ነውም ብለዋል።
ዋና ጸሃፊው ስምምነቱን መላው ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲደግፈውም ነው የጠየቁት።
አክለውም ፥ በሁለቱም ወገኖች ለተደረሰው ስምምነት የተቀመጡ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡