የህዋሃትን አስነዋሪ ድርጊት የሚያወግዝና የመንግስትን እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ በዎላይታ ነገ ይካሄዳል
በነገው ዕለት በዎላይታ ዞን ጽንፈኛው ህወሃት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን አስነዋሪ ጥቃት የሚያወግዝ ስልፍ ይካሄዳል።
ጽንፈኛው ህዋሃት ቡድን በሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ለማውገዝና በሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመቆም ሰለማዊ ሰልፍ ነገ ህዳር 03/2013 ዓ/ም በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሁለገብ ስቴዲየም እንደሚካሄድ የዎላይታ ዞን አሰተዳደር በመግለጽ ለህዝቡ ጥሪ አስተላልፏል።
ሰልፉ ከጧቱ 12 : 00 ጀምሮ ከረፋዱ 3:00 ሰዓት እንደሚጠናቀቅም የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል።