መንግስት የጀመረው ጉዞ ጦርነት ሳይሆን ህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ መሆኑን የዎላይታ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ

የህዝብን የለውጥ ፍላጎት መቋቋም አቅቶት ለመታደስ እና ጊዜው ከሚፈልገው ሁኔታ ጋር ራስን አሻሽሎ መሄድ ከብዶት ህዝብ አንቅሮ የተፋው የህወሐት #ጁንታ ቡድን ለፍርድ የሚቀርብበት ግዜ መድረሱን የወላይታ ዞን አንዳንድ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ትላንት በመግለጫ እና በተበተበው የተንኮል ሴራ ተማምኖ አልነኬ ነኝ ሲል የከረመው የጁንታ ቡድን ዛሬ ላይ በሰራዊታችን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት ሲጀምር ያ ሁሉ ድንፋታ ቀርቶና ትዕቢቱ ተንፍሶ መግቢያው ጠፍቶታል፡፡

አሁን ሰአቱ የድርድር ሳይሆን የፍርድ ሲሆን በእርግጥም ከዚህ ጁንታ ቡድን ጋር ትላንት በውይይት እና በምክክር ነገሮችን ለመፍታት የሄድንበትን እልህ አስጨራሽ መንገድ ልንመርጥ የቻልነው የጁንታው ፀባይ ጠፍቶ ሳይሆን መሸሸጊያውን ህዝብ ስር ለማድረግ መሞከሩ እና የጀመርነው የለውጥ ጉዞ ባሩድ የለሽ እንዲሆን በማሰብ ነበር፡፡

ነገር ግን ሰላም ከአንድ ወገን መሻት እና ጥልቅ ፍላጎት ብቻ መምጣት አይችልምና፤ ሰላማዊ መንገዶችን መከተል ሲገባው ሊያጠቃ አድፍጦ የመጣው የጁንታው ስብስብ በሳበው ምላጭ የመጥፊያው የመጀመሪያው ደወል ሆና ትፃፍ
ዘንድ ግድ ሆኗል፡፡

እናም ትዕግስት ሊቀይረው ያልቻለውን ጁንታ በህግ አግባብ ተጠያቂ ማድረግ ግዴታ የሆነበት ሰአት ላይ ደርሰናል፡፡

አሁን መንግስት የጀመረው ጉዞ ለጦርነት ሳይሆን ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ነው፡፡ መንግስት በአጭር ጊዜ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ቤት አቅርቦ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ መቀጠል ያስፈልጋል የተባለውን መረጃ ከዞን አስተዳደር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ድል ለኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት!!!
ድልና ነጻነት ለትግራይ ሕዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!