1669296697649

ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በሙከራ ደረጃ መላክ የጀመረችው የኤሌክትሪክ ኃይል ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሙሉ አቅም ይገባል

ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ወጣ ብሎ በላሾ ቀበሌ የተገነባው የዎላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ስቴሽን የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እየተመጠነ የሚላክበት ማዕከል የሙከራ ኃይል የመላክ ሥራ ጀምረዋል።


ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በሙከራ ደረጃ መላክ የጀመረችው የኤሌክትሪክ ኃይል ከአንድ ወር በኋላ ወደ ሙሉ አቅም እንደሚገባ ተገለጸ።

የኢትዮ ኬንያ ፕሮጀክት የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) እንደገለጹት ይህ ፕሮጀክትበአሁኑ ወቅት የሙከራ ሃይል ማስተላለፉን በሚገባ እያከናወነ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የሙከራ የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ ሥራ አየተከናወነ ሲሆነ የሙከራ ስርጭቱ ለአንድ ወር ያህል ከቀጠለ በኋላ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ ይገባል ብለዋል።

የዎላይታ ሶዶ የኮንቨርተር ስቴሽን የኦፕሬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ግርማ በበኩላቸው፤ ይህ ፕሮጀክት በቀጣይ ከኬንያ ባሻገር የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ እና ሌሎችም የጎረቤት አገራት የሚተላለፍበት መስመር መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮ ኬንያ ፕሮጀክት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባ ሲሆን ፕሮጀክቱ በዓለም ባንክ አና በአፍሪካ ልማት ባንክ በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ነው።

ከዎላይታ ሶዶ ከተማ ወጣ ብሎ በላሾ ቀበሌ የተገነባው የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ስቴሽን የኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እየተመጠነ የሚላክበት ማዕከል የሙከራ ኃይል የመላክ ሥራ ከጀመረ ስድስት ቀናት ተቆጥረዋል ስል ኢፕድ ዘግቧል ።