ከሌላ ቦታ የተገዛ ዳቦ ነበር

በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዱቀት ፋብሪካ አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር መመረቁ ተገለፀ።

በቅርቡ በዎላይታ ሶዶ ከተማ በቀዳሚዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ተገንብቷል የተባለው ፋብሪካ ዳቦና ዱቄት ማምረት ሳይጀምር ከሌላ ቦታ ዳቦ በማስመጣት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመጡ እንግዶች በተገነባው ፋብሪካ እንደተመረተ ተደርጎ መቅረቡን ከስፍራው የWT መረጃ ምንጮች ያደረሱት ዘገባ ያመለክታል።

ፋብሪካው ተገንብቶ ተጠናቋል ከተባለ በኃላ አልሰራ ስል 3 ጊዜ ተጨማሪ ማሽን በየሁለት ሚልዮን ብር ተገዝቶም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በመጡበት ቀንም ጭምር አልሰራ ስል የአከባቢው አመራሮች ፋብሪካው ዳቦ እያመረተ እንደሆነ በማስመሰል ለማሳየት ከሌላ ቦታ ዳቦ ተገዝቶ መጥቷል ስልም ምንጮች አክለው አረጋግጧል።

ይህም ልሆን የቻለው ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፋብሪካውን ለማስመረቅ ወደ ዎላይታ ይመጣል ተብሎ ቅድመ ዝግጅት ከተደረገ በኃላ ፋብሪካው ዳቦና ዱቄት ማምረት ባለመቻሉ የኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን በባሌ ከተማ አቅራቢያ ለሚያስገነቡት ሎጅ መሠረት ድንጋይ ከጣሉ በኃላ በዚያው መመለሳቸውን ተከትለው “ጠቅላይ ሚኒስቴር እመጣለው ብለው ዝግጅት ተደርጎ ለምን አልመጡም”? የሚል ወቀሳ ብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ በመሆኑ የአከባቢው አመራሮቹ ያንን ወቀሳ ለማስታገስ ፋብሪካው ዳቦ እያመረተ እንደሆነ በማስመሰል ለማሳየት ከሌላ ቦታ ዳቦ ገዝተው አምጥተው ለእንግዶች ለማሳየት እንደሞከሩም ይገመታል እንደ ምንጮች ገለፃ።

በተቃራኒው በወቅቱ ከባለቤታቸው ቀደማዊት አመቤት ጋር በ10 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገነባ የተባለውን የዳቦ ፋብሪካ ለማስመረቅ ወደ ዎላይታ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአከባቢው ህብረተሰብ ክፍሎች ትችት ገጥሟቸው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ “ህዝቡ የጠየቀውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ነፃነትና በሀገሪቱ ዕኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የክልል አደረጃጀት ይመለሳል በሚል በተደጋጋሚ ቃል የገቡ ቢሆንም በሽንገላ ቃላቸው ለማታለል የሚደረግ ነው” በሚል በብዙዎች ዘንድ ይተቻሉ።

ዎላይታ ላይ ልጆቻቸዉ ወደ ጎዳና ሳይወጡ በተወለዱበት አካባቢ የአባትና የእናት ፍቅር እያገኙ ቢያድጉ አይጠሉም፡፡ ግን ይህ እድል የለም፡፡ ከህፃናት ጀምሮ በየጎዳናው ለስቃይና ለስደት ኑሮ ተገዷል። የሚማሩ ልጆችም ተስፋ ቆርጠዉ በየሠፈራቸዉ ከተመረቁ 5 ዓመት እና በላይ የሆናቸዉን ከመቶ ሺህ በላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ድግሪ ምሩቃን እና አሁንም ሥራ አጥ ሆነዉ የተቀመጡትን ወጣቶች እያዩ ትምህርት ላይ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ በሀገሪቱ የትም ብትሄድ የዎላይታ ልጅ በብዛት የሌለበት የለም። በየቦታው የሚኖሩት ለጉብኝት ሳይሆን በአከባቢው ምንም አይነት የስራ ዕድል ባለመኖሩና መንግስትም ለዚሁ ችግር ትኩረት ባለመስጠቱና ዕቅድም ያለመኖሩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ወደ ዎላይታ ይመላለሳሉ፡፡ ነገር ግን የዎላይታ ችግር አልገባቸዉም፡፡ የዎላይታ አመራሮቹም ለስልጣናቸዉ ሲሉ እዉነታዉን አይናገሩም፡፡ ለማወቅም የፈለጉ አይመስልም። የዎላይታ ችግር የዳቦ ፋብሪካ አይደለም፡፡ ዳቦማ በየሠፈሩ ይመረታል፡፡ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ጨምሮ በየከተማው 20 የሚደርስ ዳቦ ፋብሪካ አለ። ዎላይታን ያስቸገረዉ የዳቦ መግዣ ነዉ እንጂ ይላሉ፡፡ የዎላይታ ወጣት የሥራ ዕድል ይፈልጋል፡፡ ብዙ ሰዉ የሚይዝ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገነቡለት ይፈልጋል፡፡ ሠርተው ገንዘብ አገኝተው ዳቦ መግዛት ይችላል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደለመዱ ዳቦዋን አመራሮች ይበሏታል እንጂ ሕዝቡ አይቀምሳትም የሚል ሙግት በብዙዎች ዘንድ ይንፀባረቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ከህዝብ ጋር ስወያዩ ቃል ከገቡት ነገር አንዳች ነገር አልፈፀሙም የሚሉም አልጠፉም። እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዎላይታ ህዝብ ፍላጎት ወጪ በተቃራኒው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ለማሳየት “በህዝብ የሚወደዱና ለህዝብ የሚወግኑ አመራሮች በማንሳትና በማሳሰር ለህዝብ ክብርና ጥቅም ደንታ የሌላቸው ጥቂት ግለሰቦችን ተጠቅሞ የህዝብ ጥያቄ እንዳይመለስ ያደርጋሉ” የሚሉ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ እየሆኑ ናቸው። በዚህም ምክንያት የገዥው መንግስት #ብልፅግና ፓርቲ ከአመራር ውጪ ቃሉን ለመስማት የሚፈልግ አንድ ዎላይታ ማግኘት ከባድ እየሆነ ነው። ምክንያቱም በተግባር ሁሉም ነገር ከህዝብ ፍላጎት ውጪ ነው ይላሉ። እርስዎስ በዚህ ሀሳብ ላይ ምን አስተያየት ይሰጣሉ ?

የአከባቢው አመራሮች ፋብሪካው አገልግሎት መስጠት ሳይጀምር ዳቦ እያመረተ እንደሆነ በማስመሰል ለማሳየት ከሌላ ቦታ ዳቦ ገዝተው አምጥተው ለእንግዶችና ለጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምር ለምን ለመሸወድ ተፈለገ ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: