የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተደዳሪ የነበሩ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የኢፌዲሪ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾሙ።

አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የኢፌዲሪ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ መሾማቸው ተገልጿል።

የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩትና በወቅቱ አብሮ የነበሩ አመራሮች በተለይም “የዎላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ህገመንግስታዊ መብት ጥያቄ” በህጉ መሠረት ለማስመለስ ህዝባዊ ውግንና በማሳየታቸው “ህገመንግስታዊ ስረዓትን በኃይል መናድ በሚለው ወንጀል ተጠርጥረው ከስልጣን እንዲወርድ ተደርጎ እስርቤት ረጅም ጊዜ ቆይቶ በፍርድቤት ነፃ ተብሎ መውጣታቸው ይታወሳል።

ከታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ የሾሟቸው የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ፒ ኤች ዲ) መሆናቸውንም አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በፌስ ገፃቸው ካጋሩት የሹመት ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

የዎላይታን ሕዝብ በታማኝነትና በቅንነት እንዲሁም በጀግንነት የመሩትና ያስተዳደሩት ተብለው የሚታመኑት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የዎላይታ ሕዝብ መብቱና ጥቅሙ እንዲከበር ያደረጉት ተጋድሎ በመላ ዎላይታ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የተከበሩና የተመሰገኑ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የዎላይታ ሕዝብ መብትና ጥቅም እንዲከበር ባደረገው የጀግንነት ትግል ምክንያት 2012 ዓ.ም በፍንቀላ ከሥልጣናቸው ከተነሱ በኃላ ለእስራት፣ ለእንግልትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው ነበር።

ሆኖም በጠ/ሚ አብይ አህመድ በሐገሪቷ እርቅና ሠላም ለማውረድ በጀመሩት መልካም እንቅስቃሴ ከዳጋቶ ኩምቤ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በንግግርና በውይይት ለመፍታት በማለም ይህን ሹመት ሊሰጡ እንደቻሉም ይገመታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: