በገሱባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይረክቴርና የነርሶች ኃላፊውን ጨምሮ 7 የሆስፒታሉ ሰራተኞች ታሰሩ።

በሆስፒታሉ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይረክቴር እና የነርሶች ኃላፊውን ጨምሮ 7 የሆስፒታሉ ሰራተኞች በገሱባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን እንድ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙን ያልገለፀ የሆስፒታሉ ባለሙያ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

እንደባለሙያው ገለፃ ከ28/04/2015 እስከዛሬ ድረስ ገሱባ ሆስፒታል ከመንግሥት ስራ ቀንና ሰዓት ውጭ ያለው በማቆሙና መሠረታዊ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ በአከባቢው እናቶች ተስፋ ቆርጠው እቤታቸው እየወለዱ እንደሆነ ተናግሯል።

ለጤና ባለሙያዎቹ የራሳቸው መብት ጥያቄ በመጠየቃቸው ብቻ በቴናና ቀን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይረክቴር እና የነርሶች ኃላፊውን ጨምሮ 7 የሆስፒታሉ ሰራተኞች በገሱባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ያለምንም ህጋዊ መጥሪያ የሰፈር ምልሻና ፓሊስ በአከባቢው ባለስልጣናት ትዕዛዝ ብቻ አስሯቸዋል።

“እነሱ ለብቻ ያጠፉት ነገር የለም ጥያቂያቸው የኛም ጥያቄ ነው በሚል ቅሬታ ሁሉም ጤና ባለሙያና ዶክተሮች ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ይደው በመቆም ከ6:00 በኃላ እስካሁን ሰዓት ሆስፒታሉ ያለ ባለሙያ መዘጋቱን በመግለፅ “ዎላይታ ውስጥ ያለው መንግስታዊ አፈና የራስ መብት መጠየቅ በማይቻልበት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ” ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መድረሱን አስረድቷል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ከምንም በላይ የሰዉ ልጅ ህይወት ማዳን እየተቻለ እንዳይሞት ጠልቃ ገብቶ የከፋ አደጋ ሳይከሰት መፍትሔ ቢያበጅለት መልካም እንደሆነም ጠይቋል።

በተመሳሳይ ዜና በዎላይታ ዞን የቦምቤ ሆስፒታል ባለሙያዎች የማታና ሳምንት መጨረሻ (ቅዳሜና እሁድ) ቀናት ስራ ካቆሙ ሁለት ወራት ሆኗል። በወረዳው መብራት በሳምንት ሰስት ቀናት ወይንም ቢመጣም ወዲያው ይሄዳል። ጀኔሬተር ከተበላሸብን ሁለት ወር የሆነ ሲሆን ከዝህ የተነሳ ከፍትኛ የጤና ባለሙያዎች እያሉ የኦፍራሶን አገልግሎት ተቋርጧል።

በሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች የአንድ ዐመት ሙሉ የትርፍ ሥራ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ሦስቱም ጤና ጣቢያዎች የማታና የሳምንት መጨረሻ ስራ ካቆሙት ሁለት ወር መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንደ ጤና ባለሙያዎች ገለፃ በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለረጅም ጊዜ እንደማይከፈልና ለህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ ስባል በመቶ ሚሊዮን ብሮች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና ለአመራር ስብሰባ ምክንያት በማድረግ በአበል መልክ ስለሚውል በአከባቢው የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገ መሆኑንም ከደረስን መረጃ ለማወቅ ችለናል።

የህክምና ባለሙያዎቹ በጤና ተቋማት ያለውን ተጨባጭ ችግር ማውራት፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ መጠየቅ እንዲሁም የትኛውም አይነት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በየትኛውም መንገድ ማጋለጥ ከሰራ የሚያስባርር እንዲሁም የተለያዩ ጫናዎች እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ነው” በማለት ገልፀው “ይሄንንም ጥልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር በግልጽ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ዕድል ማግኘት በራሱ ትልቅ ድልና ነገሮቹ እንዲስተካከሉ በር ከፋች ይሆናል” ስሉም መረጃውን ያደረሱ ባለሙያዎች በደስታ ሁኔታውን አስረድተዋል። የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/@wolaitatimes

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *