

በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ ይሰራል በተባለው መንገድ ግንባታ ውል ስምምነት በተመለከተ ስለ ጉዳዩ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጠይቁ፣ አሁን ላይ እኔ መረጃ የለኝም” የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይረክር የሆኑት አቶ ሳምሶን ወንድሙ ብለዋል።
በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ እና ከካዎ ጦና አደባባይ በሆርባብቾ በድሮ አረካ መንገድ የሚገጥም የ14 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ ለማከናወን ከአሸናፊ ተቋራጭ ጋር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በዛሬው ዕለት ውል የመፈራረም ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል ተብሎ በዞኑ ሚዲያዎች ብቻ በተሰራጨው ዘገባ ላይ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይረክር የሆኑት አቶ ሳምሶን ወንድሙን ጠይቀው ምላሽ አግኝተዋል።
በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ ሪዞርት ሆቴል እስከ ግብርና ኮሌጅ በ2013 ዓ ም ለማሰራት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የአለምአቀፍ ጨረታ ያወጣ ቢሆንም እስካሁን ምንም እንቅስቃሴ አለመጀመሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

የህዝብ ቅሬታ መነሻ አድርጎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሳምሶን ወንድሙን በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ ሲሰጡ “በ2013 ዓ.ም የመንገዱን ግንባታ ባለስልጣኑ መጀመር ያልቻለው በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ምክንያት ነበር” በማለት ምላሽ ሰጥቶ ነበር።
በከተማዋ ዕድገት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምክንያት ለትራፊክ አደገና መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ውስንነትና ችግሮች እየተስተዋለ የሚገኘው ከሌዊ ሪዞረት አንሰቶ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ የሚወስደውን ዋና የአስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በ2013 በጀት ዓመት የአስፋልት ኮንክሪት ለመስራት አለም አቀፉ ጨረታ በሃገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ማሰራት አለመቻሉን ይናገሩ እንጂ በወቅቱ መቼ እንደሚሰራ ኃላፊው አልገለፁም ነበር።
በዛሬው ዕለት “በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ እና ከካዎ ጦና አደባባይ በሆርባብቾ በድሮ አረካ መንገድ የሚገጥም የ14 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ ለማከናወን ከአሸናፊ ተቋራጭ ጋር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ውል የመፈራረም ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል ተብሎ በዞኑ ሚዲያዎች የተሰራጨውን መረጃ ተከትሎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይረክር የሆኑት አቶ ሳምሶን ወንድሙን በስልክ አነጋግሮ ምላሽ አግኝቷል።

አቶ ሳምሶን ምላሽ ስሰጡ “ስለ ጉዳዩ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጠይቁ፣ ስለጉዳዩ አሁን ላይ እኔ መረጃ የለኝም በሚል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የውል ስምምነቱ ያን ያህል በብዙ ገንዘብ የሚሰራ ከሆነ ለምን የባለስልጣኑ ሰዎች እውነተኛነቱን አላረጋገጡም ? በዜና ላይ ለምን የመንገዶች ባለስልጣን አካል አስተያየት አልሰጠም ? ሌሎች ሚዲያዎች ወይንም በባለስጣኑ ዌብሳይት የአሸናፊ ድርጅት ስም በይፋ አልወጣም? ስራው መቼ ተጀምሮ መቼ ያልቃል ? የግንባታ ወጪጪ ምን ያህል ነው? በሚል የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለአቶ ሳምሶን ላነሳው ጥያቄ “አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት አልችልም ወደፊት አዲስ ነገር ካለ እነግርሃለሁ” ብለዋል።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይረክተር የሆኑት አቶ ሳምሶን በጉዳዩ ዙሪያ ተጠይቀው ስለሰጡን ማብራሪያ በተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን በግል ስልክ በተደጋጋሚ ብንደውልም ምለሽ አልሰጡም።
በሌላ ዜና ባለፈው አመት አጋማሽ አካባቢ በዎላይታ ዞን የአየር ማረፊያው የሚገነባው ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው ግንባታ እንቅስቃሴ አንድ ወር በላይ መቆሙን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል።



ባለፈው አመት አምስት ወር ገደማ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለጉብኝት ዎላይታ በመጡበት ወቅት የዚሁ አየር መንገድ ግንባታ ሂደት መመልከታቸውን ተከትሎ የግንባታ ሂደት ከኤር ስትሪፕ ደረጃ ደረጃውን የጠበቀ ሁሉንም አይነት አውሮፕላን ማስተናገድ በሚችልበት ዘመናዊ ደረጃ እንዲገነባ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተናግረው በወሰኑት መሠረት ነው ተብሎ በወሬ ደረጃ ቢገለፅም ስለ ጉዳዩ ለህዝብ በይፋ በሚዲያ ሆነ በሌላ መንገድ አለመገለፁ ለብዙዎች ከፍተኛ ቅሬታና ጥርጣሬ እየፈጠረ ይገኛል።
ግንባታው የቆመበትን ምክንያት ለማግኘትና በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ የግንባታ ባለቤት የሆነውን የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ኢሜል፣ በቢሮና በግል ስልክ ላይ በተደጋጋሚ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ብጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛነት ባለማሳየቱ ማካተት አልተቻለም።
የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው ነበር።
የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በ1999 የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉም ይታወቃል።