በደቡብ ክልል የክልሉ መፍረስ ሳይረጋገጥ የንብረት ቆጠራና ክፍፍል ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከስፍራው ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት “የክልሉ መፍረስ ሳይረጋገጥ የንብረት ቆጠራና ክፍፍል ተግባር” መጀመሩን ያመለክታል።

የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት በደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥያቄ ተከትሎ የሚስተዋሉ የመንግስት ንብረት ዝርፊያ፣ ከህግ አሰራር ውጪ ተግባራት እንዲሁም የማሸሽ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ስለመምጣቱ አረጋግጧል።

በተለይም በክልሉ ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከህዝብ ከመንግሥት መዋቅሮች በጥሬ ገንዘብና በአይነት የተሰበሰበው ወደ ማዕከል ሙሉበሙሉ ሳይደርስ በኮሚቴ የተዋቀሩ ግለሰቦችና አመራሮች ክስ በሚሊዮን የሚቆጠር ስገባ እንደነበር ገልጸዋል።

በጦርነቱ ወቅት ህዝብ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ከየቤቱ፣ መንግስት ሰራተኞች ከደሞዛቸው ሳይወዱ በግድ የሰጡትን ገንዘብ በተጨባጭ ለግል ጥቅም በተደራጀ መንገድ ያዋሉ ከወረዳ፣ ከዞንና ክልል ድረስ በከፍተኛ አመራሮች መኖሩን አረጋግጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ “ክልሉ ይፈርሳል” በሚል ለመናገር በሚከብድ ሁኔታ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ እንኳን በግዜ ሳይሰጥ በሚቸገሩበት ክልል በየመስሪያ ቤቱ ህገወጥ አሰራር ተዘርግቶ በተለይም ከሰሜን ጦርነት ወቅት ጀምሮ ዝርፊያ መጧጧፉንም በቁጭት ተናግረዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ የፋይናንስ ስራአትን እየመራ ያለው ህጋዊ አሰራር ሳይሆን አመራር በስልክ ባዘዘው መንገድ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ካለ በየመስሪያ ቤት ገብቶ የኦዲት ስራ ሰርቶ አለአግባብ በተደራጀ መንገድ የተዘራውን የህዝብና የመንግስት ሀብት ብያስመለስ ይሻላል ስሉም ባለሙያው ተማፅነዋል።

በየወቅቱ የሚስተዋሉ መሰል ችግሮችን ለማጋለጥ የተቋቋሙ መስሪያ ቤቶቹም ከጥቅመኞች ጋር ተባባሪ ስለሆኑ ለማን አቤቱታ እንደሚናቀርብና ብናቀርብ እንኳን የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ለእውነት የሚሟገቱ ሰዎች ጭምር ዝምታ እንዲመርጡ አድርጓል ስል ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ከተለያዩ ሰነዶች ጋር መረጃ ሰጥተዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በክልሉ በየመስሪያ ቤቱ ክልሉ ይፈርሳል በሚል በተደራጀ መንገድ የመንግስትና የህዝብ ንብረት ለግል ጥቅም ለማጭበርበር የሚደረገውን እንቅስቃሴ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የፈደራል መንግስት በአስቸኳይ ጠልቃ ገብቶ እንዲያስቆም ጠይቋል።

በተጨማሪም የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ክልል አደረጃጀት ተክትሎ ለብቻው የቀረው የቀድሞ ደቡብ ክልል ለእያንዳንዳቸው የምክርቤት አባላት ግማሽ ሚሊዮን ብር የተሰጠ ሲሆን ለቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በስማቸው አንድ አንድ ሚሊዮን ብር ከመንግሥት ካዝና ወጪ ተደርጎ መሰጠቱን ስሙን ለድህነቱ ያልገለፀው ከፍተኛ ፍይናንስ ባለሙያ መግለፁን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *