የተፈመውን ወንጀል ድርጊት ወራዳችንን ወክለው በፓርላማ ተመራጭ ለሆኑት የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጭምር ብናቀርብም ምላሽ አላገኘንም ስሉ አርሶአደሮች ገለፁ

በደቡብ ክልል ዎላይታ ዞን አበላ አባያ ወረዳ በይፋ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ የተጠርጣሪ እና የምስክር ቃል የተሰጠበት፣ ከስድስ መቶ ኩንታል በላይ ከነጭ አሸዋ ጋር የተቀየጠ የአፈር ማዳበርያ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ቢሆንም ግለሰቦቹ ተጠያቂ ባለመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት አሁንም የህግ የበላይነት እንዲያስከብሩ የአከባቢው አርሶአደሮች ጠይቋል።

ይህ ማዳበርያ ከመንግስት መጋዝን መንግስት ለአርሶ አደሩ የሚያቀርበውን በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ትዕዛዝ እያወጡ የተቀየጠውን ለገበሬው ስያሰራጩ አመቱን ሙሉ የቆዩበት ስራቸው መሆኑ እዝግቢቱ ስያዝ በባዕድ ነገር መኖሩ የተረጋገጠ ቢሆንም በህግ ተጠያቂነት እንዲኖር አለመደረጉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል።

ከረጢቱ ላይ የታተሙ የማብቂያ ጊዜን የምገልጹ ሃሰተኛ ህትመቶች፣ አፈሩን ከዋናው ማዳበሪያ ጋር የሚቀይጡበት ሂዴት የሚያሳዩ የተለያዩ መሣሪያዎች አስረጂ የሆነበት ህገ ወጥ ድርጊት ከክልሉ ፀሬ ሙስና ጭምር በመምጣት ለወራት ምርመራ ያደረጉ ቢሆንም የምርመራ ባለሙያዎችን በገንዘብ የያዟቸው መሆኑን ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና እየተከታተሉ የሚገኙ አርሶአደሮች ተወካዮች የተናገሩት።

የዚያ አከባቢ በፓርላማ የህዝብ ተመራጭ የሆኑት ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ-የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ ጥላሁን ከበደ-የደቡብ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ፣ አቶ ተስፋየ ይገዙ-የክልሉ ም/መስተዳድር ጨምሮ ሌሎች ቢሯቸው ድረስ በመሄድ አቤቱታ በፅሁፍ የቀረበላቸውና ጉዳዩን በጥልቀት እና በዝርዝር እያወቁ መፍትሄ ላለመስጠት ዝምታ መምረጣቸው ቅሬታ እንደደፈጠረም ተገልጿል።

ከላይ በስም የተጠቀሱ የሥራ ሃላፊዎች በህዝብ የተመረጡ እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት የተሸከሙ ሆነው በህዝብ ጫፍ የወጣ በደል ላይ ፍትህን ለማስፈን ያለመስራታቸው በህዝብ ዘንድ ጥሪጣሬ እየፈጠረ ነውና እውነተኝነቱን በማረጋገጥ ፍትህ እንዲሰጡን እናሳስባለን ስሉም ጠይቋል።

ጉዳዩ ሆን ተብሎ በአንድ ግለሰብ ስም መውጣት የማይችል ገንዘብ በቼክ ተፈርሞ ለግለሰቦች ጥቅም ለማዋለ የተደረገ ስለመሆኑ የፌደራል ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሃላፊ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ህዝቡ ከወረዳው ተደራጅቶ እስከ ቢሯቸው ድረስ የወሰዱትን አበቱታ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንደከተታቸውም ጉዳዩን እየተከታተሉ የሚገኙ የአርሶአደሮች ተወካዮች የገለፁት።

ከአባያ አስፓልት ሥራ ተብሎ የመቃብር ጭምር ካሳ ከፍሎ ለማስነሳት በማዘጋጃ ስራ አስኪያጅ፣ መሃንዲስ እና የቀበሌ ሊቀ-መንበር በተከፈተው አካውን በእያንዳንዱ ስም 193 ሺህ ብር በ3ቱ ግለሰቦች 579 ሺህ ብር ወጪ ተደርጎ መዝገብ ላይ በሰፈሩ በህይወት በለሉ ሰዎች ስም ተወዳድቋል ስሉም አስረድቷል።

በወረዳ ከባዕድ ነገር (ነጭ አሸዋ) ጋር የተቀየጠ ማዳበሪያ ከአርሶአደሮች በተሰበሰበው ብር ተገዝቶ ጥቅም ሳይሰጥ እንዲቀመጥ ያደረጉ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው አካላት አሁንም ጠልቃ እንዲገባ በድጋሚ ጠይቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: