

ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ከደቡብ ቴለቪዥን ጋር በመተባበር “በህዝበውሳኔና በሪፈረንደሙ ዙሪያ ባዘጋጁት ቅድመ ክርክር ጭብጥ ላይ ከዎብን እና ዎህዴግ ተቋውሞ መግጠሙ ተገለፀ።
“አድሱ ክልል አስተዳደራዊ አዋጭነት፣ ኢኮኖሚያዋ ፋይዳ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች” በሚል ርዕሰ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ከደቡብ ቴለቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ቅድመ ክርክር ጭብጥ መድረክ ላይ የተሳተፉ የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር እና የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ንቅናቄ ተወካዮች የቀረበው የክርክር ጭብጥ ሀሳብ ላይ የህዝብ ፍላጎት ያልተካተተበት መሆኑን በመግለፅ ቅድመ ክርክር መድረኩን ጥለው እንደወጡ ለWT ሚዲያ ከየፓርቲዎቹ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
እንደ መረጃ ምንጫችን “በዚህ ሂደት የሕዝባችን ፍላጎት ያልተካተተበት ኢሕገመንግስታዊ የሪፈረደም ሂደት የሚያከራክረን አጀንዳ የለም” በሚል ለአክራሪዎች በሚገባ በማስረዳት ወደ ዋናው ክርክር ሳይሄዱ ተወካዮቹ የቅድመ ክርክሩን አቋርጠው መውጣታቸውን ገልጿል።
የቅድመ ክርክር ጭብት ሀሳብ ላይ የተካሄደው መድረክ በትናንትናው ዕለት ጧት ከሶስት ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ሮሪ ሆቴል መሆኑንም አክለው ገልጿል።
“አድሱ ክልል አስተዳደራዊ አዋጭነት፣ ኢኮኖሚያዋ ፋይዳ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች” በሚል ርዕሰ ጭብጥ ሀሳብ የዎብን እና የዎህዴግ ተወካዮች “በህገመንግስቱ መሠረት የህዝብ ፍላጎት ያልተካተተበት ነው፥ የዎላይታ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚል አማራጭ የክርክር ነጥብ በሌለበት መከራከር አንችልም ብለው ወደ ዋናው ክርክር ቦታ ሳይሄዱ መድረኩን ረግጠው ሲወጡ በመድረኩ የኢዜማና ሌሎች ፓርቲዎች ተወካዮችና ግለሰቦች ወደኋላ እንደቀሩና ወደ በቀረበው የህዝብ ፍላጎት ያልተካተተበት በተባለው ጭብጥ ሀሳብ ዙሪያም ክርክር ለማካሄድ ወደ ደቡብ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ መሄዳቸውንም ከደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ዎብን እና ዎህዴግ ከወትሮው በበለጠ መንገድ ከህግና ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በኃይል ለማካሄድ እንቅስቃሴ የተጀመረው ሪፈረንደም ተፈፃሚነት እንዳይኖር የሚያደርገውን ትግል ህብረተሰቡን በማስተባበር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንም አስረድቷል።
የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/@wolaitatimes