በዎላይታ ዞን የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በየጤና ተቋማት መድሃኒት አለመገኘቱ ለመቆጣጠር ፈተና እየሆነ መሆኑ ተገለፀ።

በዞኑ ወረርሽኙ በአንድ ሳምንት ብቻ ከአስር በላይ ሰው ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በርካቶች በበሽታው መያዙም ተነግሯል።

ሰሞኑን በዞኑ ከአራት ወረዳዎች በላይ በተከሰተው በዚሁ በኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከሀያ በላይ አዋቂዎችና ህፃናት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ህክምና እየተከታተሉ እንዲሁም ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉት በየቤታቸው እንዳሉ ለWT የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ይሄ ኩፍኝ (measles) በሽታ ወረርሽኝ በዎላይታ ዞን በክንዶ ዲዳዪ፣ በክንዶ ኮይሻ፣ በኦፋ ወረዳ ደሜ ቀበሌ፣ በዳሞት ሶሬ ወረዳ ሱንቃሌ ቀበሌ እንዲሁም አጎራባች ወረዳዎች እየተስፋፋ መሆኑንም አንድ በዚሁ ዘመቻ እየተሳተፈ የሚገኝ የዞኑ ጤና መምሪያ ባለሙያ ያስረዳው።

በዚሁ ወረርሽኝ እስካሁን ከአስር በላይ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ በርካታ ግለሰቦች በከፍተኛ ህመም ላይ መሆኑን ባለሙያው ለWT ሚዲያ አብራርቷል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦችን ለማከም የሚያስችል መድሀኒት በየጤና ተቋማት አለመገኘቱ እንዲሁም በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦች በየቤታቸው የሚገኙ ስላሉ ወረርሽኑን ለመቆጣጠር ፈተና መሆኑን አስረድቷል።

በአሁኑ ወቅት “የጤና ዘርፍ አመራሮች ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠቱና የወረርሽኝ መረጃ ይፋ ከሆነ የአከባቢው ገፅታ ያበላሻል” በሚል ወደ ክልል ሆነ ወደ ፈደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፓርት ባለመደረጉ የሰው ህይወት እንዲያልፍ እያደረገ ስለመሆኑም አክለው ገልጿል።

የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ በዘመቻ መንገድ ቶሎ መቆጣጠር ባለመቻሉ በአሁኑ ወደ ሌሎች አከባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን ጠቅሶ የሚመለከታቸው አካላት “ለራሳቸው ስምና ገፅታ መገንባት ቅድሚያ ሳይሰጡ” የሚመለከታቸው አለምአቀፍ ተቋማት እገዛ እንዲያደርጉ በሽታው ያለበትን ሁኔታ ይፋ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስቧል።

በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ ለማግኘት ወደዞኑ ጤና መምሪያ በድጋሚ በተደጋጋሚ ስልክ ብንሞክርም ያልተሳካ ስሆን ምላሽ ካገኘን እንመለስበታለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: