ምርጫ ቦርዱ በተለይም በዎላይታ ዞን በተፈፀመ ምርጫ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ውጤት ይፋ ለማድረግ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ተገለፀ።

“ህዝበውሳኔው ሕዝብን የማይወክልና የህዝብ ፍላጎት በምርጫው ባልተካተተበት በህገወጥ እንዲካሄድ የተወሰነ” በሚል “ህዝቡ ከምርጫ ካርድ ባለመውድ እምቢተኝነት” ከማሳየት ጀምሮ በምርጫው ዕለትም ሁሉም ከቤት ባለመውጣት የዘመናት ጥያቄ ለማሳካት በሚያስችል ሁኔታ አብዛኛው ህብረተሰብ ክፍሎች አለመምረጡን የተለያዩ ማስረጃዎች ዋቢ አድረገን መዘገባችን ይታወቃል።

ህዝበውሳኔው የዎላይታ ሕዝብን የማይወክልና የህዝብ ፍላጎት በምርጫው ያልተካተተበት መንግስት በጉልበት ለማስፈጸም እየሞከረ የሚገኘው ህገወጥ አካሄድ ከቤት ባለመውጣት የህዝብ የዘመናት ጥያቄ ለማሳካት በሚያስችል ሁኔታ መግባባት ላይ ተደርሶ የተወሰደውን እርምጃ የአከባቢው ፓሊሶች፣ ሚሊሻ እንዲሁም አመራሮች ቤት ለቤት በመግባት በኃይል እንዲወጡ ሙከራ ማድረጋቸውንም ከየአካባቢው የደረሱ ተጨባጭ መረጃዎችን ጠቅሰን አድርሰናል።

“የዎላይታ ህዝብ የጠየቀው ራስን በራስ የማስተዳደር እና በስሙ የሚጠራ ክልል መመስረት ብቻ በመሆኑ ይሄ ምርጫ በሌለበት ህዝባችን ትናንት በደም መስዋዕትነት ወደመጣበት እንዲመለስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማስቆም ብቸኛው አማራጭ ምርጫው በሚካሄድበት ቀን አብዛኛው በፀጥታ ኃይል ተገደው፣ በብር ከመንገድ የተገዙና ከመንግስት አመራሮች በስተቀር ሁሉም ቤት የመቀመጥ አድማ በማድረግ ለቀጣይ ትውልድ ትልቅ አሸናፊነት ወኔ ለማውረስ ባለመምረጥ የወሰደበትን አኩሪ እርምጃ ቀጣይ ህዝቡ ያልተሳተፈበትና ያልመረጠው ውጤት ስገለፅ ባለመቀበል እንደሚደገም የሁኔታው አስተባባሪዎቹ አስረድቷል።

አሁን ላይ ምርጫ ቦርድ “ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በፀጥታ ኃይሎች አስገድደው፣ ሰውን ከመንገድ በብር በማታለል እንዲሁም መንግስት አመራሮችና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ብቻ መረጡ የተባለው ምርጫ የለለው ህዝበውሳኔ ምርጫ ሰፊው ህዝብ ያልተሳተፈበትና ያላመኑበት መሆኑ አሁን ባለው ሁኔታ በምርጫ ቦርድ ደረጃ ተጭበርብሯል፣ የምርጫ ሂደቱ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለና የአመራሮች ጠልቃ ገብነት የተንፀባረቀበት ተብሎ ምርጫውን ለመሰረዝ፣ ከእንደገና ለማካሄድ ወይንም በቦታው እንዲፀና በሚል ውሳኔ ለማሳለፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን አስተባባሪዎች ለWT በላኩት መረጃ አመላክቷል።

የምርጫ ሂደቱ “ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለና የአመራሮች ጠልቃ ገብነት የተንፀባረቀበት መሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች በተጨባጭ በአይናቸው ያዩት ሀቅ በመሆኑ “በዚህ ሂደት ምርጫ ተካሂዷል ተብሎ የሚወሰን የትኛውም ውሳኔ ተቀባይነት የሌለውና ምናልባት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አሁን ላይ ከየትኛውም መንግስታዊ ጫና ነፃ ሆኖ እውነተኛ የህዝብ ድምፅን ለማስከበርና ይፋ ለማድረግ የተዘጋጀው ውሳኔ ሀሳብ በተግባር ካሳየ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው እውነተኛና ገለልተኛ ተቋም ተብሎ በህዝብ ዘንድ ለዘላለም ምስክርነት የሚያሰጥ ስራ ይሰራል” ብሏል አስተባባሪዎቹ።

ምርጫ ቦርዱ ከዚህ ሀቅ በተቃራኒው ህዝበውሳኔው “ከህዝብ ፍላጎት ውጪ በፀጥታ ኃይሎች አስገድደው፣ ሰውን ከመንገድ ብር በመስጠት በማታለል እንዲሁም የመንግስት አመራሮችና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ብቻ የመረጡትና ሰፊው ህዝብ ያልመረጠው፣ ያልተሳተፈበትና ያላመኑበት ምርጫ መሆኑን እያወቀ ቦርዱ ለህዝብ ሳይሆን ለጥቂት የመንግስት አካላት ወግኖ ተቀባይነት የለለው የውሸት ውጤት ይፋ ካደረገ በዎላይታ ተቀባይነትና ተፈፃሚነት አለመኖሩን ከወዲሁ በማሳሰብ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ለሚፈጠረው የትኛውም አይነት አደጋ ኃላፊነት ሊቀበል እንደሚገባም አስተባባሪዎቹ በጥብቅ አሳስቧል።

ከዚህ ህዝበውሳኔ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የአለምአቀፉ የዎላይታ ተወላጆችና አጋሮቹ ህብረት፣ የተለያዩ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ሌሎች ተቋማት የሚያወጡትን የአቋም መግለጫ እናደርሳለን።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይሄንን ምርጫ አካሂዷል የተባለው ከሰባት ቀን በፊት ጥር 29/2015 ዓ. ም ሲሆን በተወሰነ በየጣቢያው ውጤት ከመግለፅ ባሻገር እስከዛሬ ድረስ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት በቦርድ ደረጃ የተገለፀ ውጤት የለም ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *