ታሪክ አዋቂ፣ መምህር፣ ጋዜጠኛ፣ ተርጓሚና ደራሲ የጋሽ ገብረሚካኤል ኩኬ ቀብራቸው በኦቶና ቅድስት ማርያም ቤተከርስቲያን ተፈፀመ።

የመጀመሪያ የጋዜጠኝነት ሙያቸውን በለገዳዲ ሬዲዮ ጣቢያ የጀመሩና ለረዥም ዓመታት በደቡብ ትምህርት በሬዲዮ፥ በዎላይታ ሶዶ ፋና ኤፍ ኤም ሬዲዮ 99.9፣ በዎላይታ ወጌታ ማህበረሰብ ሬዲዮ 96.6 ሬዲዮ እና በዎላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ በአርታኢነት ሙያ በትጋት ሲያገለግሉ የቁዩት ጋሽ ገብረሚካኤ ኩኬ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በቀን 22/07/2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

የቀብር ስነስርዓቱ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ የስራ ባልደረቦቻቸውና ወዳጆች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በዎላይታ ሶዶ ከተማ በኦቶና ቅድስት ማርያም ቤተከርስቲያን ተፈፅሟል።

አንጋፋው ጋዜጠኛ ቀደም ሲል በመምህርነት ሙያቸው እውቁን ሳይንቲስት ቅጣው እጁጉን ጨምሮ በረካታ ምሁራንን ያስተማሩ መምህርም እንደነበሩ ይታወቃል።

ታሪክ አዋቂ፣ መምህር፣ ጋዜጠኛ፣ አርታኢ፣ ተርጓሚና የብዙ ሙያዎች ባለቤት የሆኑት ገብረሚካኤል ኩኬ ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ዘመድ አዝማድ፣ እንዲሁም የሙያ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን በድጋሚ የWT ሚዲያ ይመኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: