በዎላይታ በኩፍኝና ወባ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን የ38 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በጤና ተቋማት ላይ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ክልል በተለይም በዎላይታ ዞን ከተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ለጤና ስራ የሚበጀተው ገንዘብ ላልተፈለገ አላማ ስለሚውልና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ትኩረት ባለመሰጠቱ በዞኑ ባሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መስረታዊ የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ የብዙ እናቶችና ህፃናት ህይወት ማዳን እየተቻለ እየሞቱ መሆኑንም የጤና ባለሙያዎች ገልጿል።

ለህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ ስባል በመቶ ሚሊዮኖች ከዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና በአመራሮች ተከፋፍለው በማለቁ በዞኑ የወባ፣ የኩፍኝ ወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገና በርካቶች እንዲሞቱ እያደረገ ስለመሆኑ በዎላይታ ዞን በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

እንደ ዶክተሮቹ እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ገለፃ በአሁኑ ወቅት በዎላይታ ዞን ባሉ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መስረታዊ የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ የብዙ እናቶችና ህፃናት ህይወት ማዳን እየተቻለ እየሞቱ መሆኑን ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ተናግረዋል።

ለአብነትም በዞኑ በክንዶ ድዳዬ፣ ገሱባ፣ ባሌ፣ በቦሎሶና ቢጣና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የእናቶችንና የህፃናት ህይወት ለማዳን ቀላል የሚባሉ የህክምና ቁሳቁስ እንኳን ባለመኖሩ በተጨማሪም የተከሰተውን የወባና የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ማትረፍ እየተቻለ ሞት እየተከሰተ መሆኑንም ስማቸው ከተገለፀ የተለያዩ ጫናዎች ይደርስብናል ያሉ ዶክተሮች አክለው ገልጸዋል።

በተጨማርም እንደ ጤና ባለሙያዎች ገለፃ በዞኑ በአብዛኛው ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ የትርፍ ጊዜ ክፍያ ለረጅም ጊዜ እንደማይከፈልና ለህብረተሰቡ ጤና አጠባበቅ ስባል በመቶ ሚሊዮን ብሮች የሚመደበው ገንዘብ ለፓለቲካ ስራዎችና ለአመራር ስብሰባ ምክንያት በማድረግ በአበል መልክ ስለሚውል የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ስራ አስቸጋሪ እያደረገና ከዞን ባለሙያዎች ጭምር ወረርሽኝ ወደተከሰተበት አከባቢ ለመሄድ የተመደበው ገንዘብ ለሌላ አላማ በመዋሉ ሁኔታዎችን አስቸጋሪ እያደረገ እንደሆነም በዞኑ በተለያዩ መንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።

ሰሞኑን በዞኑ ከአራት ወረዳዎች በላይ በተከሰተው በዚሁ በኩፍኝና ወባ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን የ38 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ አዋቂዎችና ህፃናት በሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ህክምና እየተከታተሉ እንዲሁም ወደ ጤና ተቋማት መምጣት ያልቻሉት በየቤታቸው እንዳሉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦችን ለማከም የሚያስችል መድሀኒት በየጤና ተቋማት አለመገኘቱ እንዲሁም በበሽታው የተጠቁ ግለሰቦች በየቤታቸው የሚገኙ ስላሉ ወረርሽኑን ለመቆጣጠር ፈተና መሆኑን አስረድቷል።

በአሁኑ ወቅት “የጤና ዘርፍ አመራሮች ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠቱና የወረርሽኝ መረጃ ይፋ ከሆነ የአከባቢው ገፅታ ያበላሻል” በሚል ወደ ክልል ሆነ ወደ ፈደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፓርት ባለመደረጉ የሰው ህይወት እንዲያልፍ እያደረገ ስለመሆኑም አክለው ገልጿል።

የህክምና ባለሙያዎቹ በጤና ተቋማት ያለውን ተጨባጭ ችግር ማውራት፣ የትርፍ ጊዜ ክፍያ መጠየቅ እንዲሁም የትኛውም አይነት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተት በየትኛውም መንገድ ማጋለጥ ከሰራ የሚያስባርር እንዲሁም የተለያዩ ጫናዎች እንዲደርስባቸው የሚያደርግ ነው” አስረድቷል።

በባለሙያዎች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተመለከተ ማብራሪያና ምላሽ እንዲሰጡ የዎላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ግልና በቢሮ ስልክ በተደጋጋሚ ብንደወልም ምላሽ አላገኘንም፣ በተጨማሪም ወደ ደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊውን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ምላሽ ካገኘን መረጃውን እንደሚናደርስ እናሳውቃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: