የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛልም ብሏል፡፡

የሚዲያ አካላት እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ሁልጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሪታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለንም ነው ያለው ፡፡