“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል ርእስ የሁለት ደቂቃ ፕሮግራም በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
=====
በዛሬው እለት ከረፋዱ 5:30 ጀምሮ የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን በግራ ደረታቸው ላይ አድርገው በመቆም ለመከላከያ ያላቸውን ክብር የገለጹ ሲሆን፤ በቀጣዩ አንድ ደቂቃ ባሉበት ሆነው ባለማቋረጥ በማጨብጨብ ለሀገር መከላከያ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።
በህውሓት ጁንታ ላይ የሚካሄደው ዘመቻ የህግ የበላይነትን በማስከበር ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን የማስጠበቅ አገራዊ ግብ ያነገበ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ናቸው።
ፕ/ር ታከለ አክለውም፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ መንግስት የአገሪቱን ሰላም፣ አንድነትና እድገት ለማስጠበቅ እያደረገ ያለውን ህግን የማስከበር ስራ በመደገፍ ከሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆም ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ሲል የዩኒቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዘግቧል።
