በዳዉሮ ዞን በተከሰተዉ አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት(አተት)በሽታ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

በዞኑ የታርጫ ዙሪያ ወረዳ 32 ሰዎች; በታርጫ ከተማ 29 ሰዎች በገና ወረዳ 2 ሰዎች በበሽታዉ ተይዘው የታከሙ መሆናቸዉን የገለፁት የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ መተኪያ በጋጆ የ5 ሰዎች ህይወት በዚህ በሽታ ማለፉንም ገልፀዋል።

በሽታዉን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ የዞኑ መንግስት የጤና አጠባበቅ ጣቢያ የአተት ህክምና ማዕከል አደራጅቶ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የገለፁት የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ መተኪያ በጋጆ ህብረተሰቡ ከተቻለ ዉሃን በዉሃ አጋር አክመዉ ካልሆነም አፍልተዉ እንድጠጡ እንድሁም ማንኛዉም ሰዉ ንጽህናዉ በተጠበቀ የመፀዳጃ ቤት በአግባቡ በመጠቀም ወረርሽኙን መከላከል ይገባል የተባለውን
የዳዉሮ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።