የኮሌኑ ቤተሰቦች በጋሞ አከባቢ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ወኪል እንደገለፁት “በአንድ ክፍል ከአንድ መቶ አርባ በላይ ሰዎች በታጎሩበት እኝህ የአገር ኩራት የሆኑ የአገር ባለዉለታ በእስር በመሰቃየት ላይ መሆኑን በማስረዳት ያለምንም ጥያቄና ክስ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ በድንገት ታፍነዉ በጋሞ ዞን ከአርባምንጭ ከተማ ሴቻ ደረቅ ፓሊስ ጣቢያ ከታሰሩ ሁለት ሳምንታት ተቆጥረዋል” ስሉ አብራርቷል።

“አገርን ለመጠበቅ፣ ህዝብን ከማንኛዉም ጥቃት ለመከላከል፣ የህግ የበላይነትን ለማስከበር  የተመደበዉ በኢፌዴሪ  አገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ የዕዙ አዛዥ ናቸዉ። ዕዙ ከሚገኝበት ምዕራብ አባያ ካምፕ ነዉ በዕረፍት ቀናቸዉ ወደ አርባምንጭ ከተማ በሄዱበት ነዉ ድንገት ታፍነዉ የታሠሩት” ስል አንድ ከፍተኛ መኮንንና ጉዋደኛው ገልጿል።

ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ በአሁኑ ሰዓት በአገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ አዛዥ ሆነዉ በአስተማማኝ ደረጃ እዙን እየመሩ የሚገኙ ጀግና ከመራር መሆናቸዉን ወኪላችን ያነጋገርናቸው  የቅርብ የሥራ ባልደረቦቹ የሚናገሩት።

ይሁን እንጂ እኚህ የአገር የቁርጥ ቀን ልጅ ባልታወቀ ምክነያት ያለምንም ክስ በጋሞ ዞን ፓለቲካ አመራሮች ትዕዛዝ ዕዙን ትተዉ በአሁኑ ሳዓት በሴቻ ደረቅ ፖሊስ ጣብያ የሀገር ባለውለታ እንደ ተራ ሰው ለሳምንታት በእስር ላይ ይገኛል ብሏል።

ከሰሞኑ አሁን ከስልጣናቸዉ የተባራሩ የጋሞ ዞን አሰተዳዳሪ የነበሩ እና ጨቋኝ ወንበዴ ግብራበሮቹ ጋር በሸረቡት ሴራ ነዉ ኮሎኔሉ በህገወጥ መንገድ ከሚመሩት ዕዝ ነጥለዉ ድንገት በማገት በደረቅ ፓሊስ ጣቢያ ያሰረው ነው የተባለው።

“ሴራቸዉም ወራት ያስቆጠረ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሠላማዊ የሻራ ማህበረሰብን በማሸበር ከአምሳ በላይ ንፁሀን በመግደል እና ሀብት ንብረታቸዉ በመዝረፍ በርካቶችን በእስር ቤት በማጎር በርካታ የሻራ ቀበሌ ነዋሪዎችን ለስደት በመዳረግ እያሰቃዩ ይገኛሉ፤ ይህንን እኩይ ተግባራቸዉን ለመፈፀም ከተጠነሰሰዉ ሴራ ጋር የተያያዘ እንዲሁም ባለፈው በትግራይ ጦርነት ወቅት የትግራይ ተወላጆች በአከባቢው በጅምላ የተገደሉበት መረጃ አውጥቷል ከሚል መረጃ ጋር በተያያዘ የኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ እገታና እስራት” ስሉ ቤተሰቦቹ ያስረዱት።

“በአቅራቢያ የሚገኘዉ የደቡብ ምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ፈጥኖ እየተጨፈጨፉ  የሚገኙትን የሻራ ህዝብ ይታደጋል” በሚል ሰጋት ነዉ ኮሎኔሉን ቀድመዉ ማሰር የቻሉት ሴረኛዉ የዞኑ አመራሮች፣ ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ ደግሞ የእዛ የሻራ ቀበሌ ተወላጅ መሆናቸዉ ነዉ” በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።

“በጠቅላይ ሚኒስቴር የሚመራን የአገር መካላከያ ሠራዊት ጉዳይ ላይ በእብሪት ጠልቃ በመግባት ከአንድ የዞን አስተዳዳሪ መሰል እርምጃ መዉሰድ ይችላል ወይ?? የደቡብ ምዕራብ ዕዝ ከዛዥ ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ  እስራት ማዕከላዊነትን የጣሰ አጅግ አሳፋሪ ተግባር ከመሆኑም በላይ በአገር ደረጃ ሠራዊቱን የተዳፈረ አጠያያቂ እና አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል” ስሉ የስራ ባልደረቦች እየገለፁ ይገኛሉ።

“ኮሎኔሉ ታስረዋል!! ፍትህ ለኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ!! ማዕከላዊ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ፈጥኖ ጣልቃ በመግባት ኮሎኔሉን ሊያስፈታ ይገባል” ስሉም ቤተሰቦቹና የሙያ አጋሮቹ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የጋሞ አከባቢ በመግለፅ ጥሪ አቅርቧል።

“ኮሎኔል ገብሬ ግንባሬ ከ1985 ዓ.ም ጀምረው  የኢፌድሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በሚታገሉበት በተለያዩ ግንባሮች በጀግንነት በፈፈፀሙት ጀብድ እና በቆራጥነት ለአገር ባበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋፆ በሠራዊቱ በተለያዩ መዋቅሮች የማዕረግ ደረጃቸውን በማሳደግ የኮሎኔልነት ማዕረግ ከመንግስት እዉቅና በክብር የተጎናፀፋ ጀግና፣ ታታሪ እና ታማኝ አገር ወዳድ ጀግና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆናቸዉ እየታወቀ እንደ ተራ ሰው መታሰሩ በዕዙ የሚገኙ ሁሉንም አባላት ያስቆጣ አስነዋሪ ተግባር ነው” ስሉም ከፍተኛ መኮንኑ ምስክርነት ሰጥቷል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *