በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ አተገባበር፣ የዲዛይን እና የሳይት ገለጻ ላይ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) መስራችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አለውበል አልማው ስለፕሮጀክት ዓላማና አተገባበር ላይ ገለጻ አድርገዋል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በባህርዳር እና ዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገነባ ሲሆን ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) የተሰኘ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድርጅት ድጋፍ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

ዎላይታ ሶዶ የተመረጠችበት አስተማማኝ ሠላሟ የተሰፈነበት፣ ሌሎች አጎራባች ክልሎችና ዞኖችን ያማከለ እና በዕድገት ላይ የሚትገኝ ከተማ መሆኗን ነው የገለጹት።

ፕሮጀክቱ በውስጡ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁሉ-አቀፍ ልማቶች ያቀፈ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ኢንተርናሽናል ሆስፒታሉ ከ168 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የሚገነባ መሆኑንና የመጀመሪያው ደረጃ ህንጻ በ20,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የኩላሊት ነቀላ፣ የኦክስጅን ማምረት፣ የጤና ምርምር ማዕከል፣ የኢንተርናሽናል ስብሰባ አድራሻ የያዘ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ግንባታው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ውሉን በማጠናቀቅ በቅርቡ እንደሚጀምርም አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቱ ለብዙ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር እና የቱሪዝም ዘርፍ አንጻርም የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል።

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ፕሮጀክት በዎላይታ ሶዶ ከተማ እንዲገነባ በማድረጉ የተሰማውን ደስታ በዞኑ አስተዳደርና በራሴ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ይህ ለዎላይታና አጎራባች ህዝብ ትልቅ ዕድል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በማህበራዊ ዘርፍ አንጻር የሚያበረክተው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዞኑ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን የዞኑ አስተዳደርና መላው የዎላይታ ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጣለሁ ብለዋል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *