በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት “ልዩነቶች በእርቅና በሰላማዊ ውይይት ተፈቶ ለህዝቡ ልማት ሁሉም በጋራ እንዲሰራ” በሚል የተቋቋመ ኮሚቴ እንቅስቃሴ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ከልካይ ባደራጃቸው ህቡዕ ቡድን እየተደናቀፈ መሆኑ ተገለፀ።

የዚሁ”ልዩነቶች በእርቅና በሰላማዊ ውይይት ተፈቶ ለህዝቡ ልማት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ የሚወጣበትንና እርቅና ሰላም የሚያወርድበት ሁኔታ ለመፍጠር በሚል በተዋቀረው ኮሚቴ ላይ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ፣ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ ዶ/ር ብርሃነፀሐይ ተክለወልድ እንዲሁም በከፍተኛ አመራሮች የተካተቱበት በመንግስት ጭምር ይሁንታ የተሰጠው በጎ እንቅስቃሴ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ከልካይ እስከ ወረዳና ዞን ባደራጃቸው ህቡዕ ቡድን እየተደናቀፈ መሆኑን አንድ የኮሚቴው አባል ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

ባለፈው ሳምንት ከፌደራል ጀምሮ በተለያዩ ደረጃ በአመራርነት የሚገኙ የአከባቢው ተወላጆች በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከዞን እና ከክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር መድረክ ባለፉት አራት አመታት በፓለቲካ ልዩነት ምክንያት ከስራቸው የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወደ ስራቸው የሚመለሱበት ሁኔታና በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ አመራሮች አንድነት እንዲጠናከር ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እንዲሆን በተደረሰው በጋራ ስምምነት መነሻ ያንን የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን” መዘገባችን ይታወሳል።

ይሄው ኮሚቴ ከተደራጀ በኃላ አለአግባብ በሀሳብ ልዩነት ምክንያት ለበርካታ ጊዜያት ደመወዛቸው ለተያዘባቸው ማስከፈል፣ ከስራ የተፈናቀሉ ግለሰቦችን ወደ ስራ መመለስና ሌሎች ተግባራትን እያከናወነ ቢሆንም በጋራ ስምምነት መነሻ የታለመውን አላማ ለማሳካት ሁሉአቀፍ መድረክ ለማዘጋጀት በይፋዊ ደብደቤ የዞኑን አስተዳደር ቢጠይቅም ፈቃደኝነት አለማሳየቱን ይፋ አድርጓል።

ኮሚቴው ለዞኑ አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ላይ ሁኔታውን ለማሳካት የሚያደርገው እንቅስቃሴ መደናቀፉን ቃል በቃል “ይህ በጎ ዓላማ ለዎላይታ ህዝብ ጥቅም እስከሆነ ድረስ ዞኑ መድረኩን በማዘጋጀት ውይይት እንዲደረግ መቸገሩ ብዙ ጥያቄ የሚያጭር እና ግራ የሚያጋባ ሆኗል” ስል ገልጿል::

ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት በቅን ልቦናና ለዎላይታ ህዝብ ሊባል በከፍተኛ የሥራ ዉጥረት ውስጥ ሆኖ ያዘጋጀው የውይይት መነሻ ሃሳብ እንዳያቀርብ መደረጉ ለዎላይታ ህዝብ እድገትና ልማት የበኩላቸውን ድጋፍና አስተዋፅኦ ለማበርከት ይህንን የዉይይት መድረክ በጉጉት ለሚጠብቀው አመራርና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እጅግ ተስፋ አስቆራጭ እንደሚሆን ኮሚቴው ይረዳል” በሚል ሁኔታውን አክለው አስረድቷል።

ሁሉም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ ለአጎራባች ህዝቦች ጭምር በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ አሁን የተጀመሩ በጎ እንቅስቃሴ የመንግስት ስልጣን ይዘው ህዝቡ ከመንግሥት ጋር እንዳይስማሙ የራሳቸውን ህቡዕ ቡድን በግልጽ አደራጅተው ክፍፍል በመፍጠር እንቅፋት እየፈጠረ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተደድር እነ አቶ ተስፋዬ ይገዙ አይነት ግለሰቦች በየትኛው ህግ ይዳኛሉ❓እንደዛ አይነት ለህዝብና ለመንግሥት አሰራር ንቀት ያላቸው በብልሹ አሰራር የተዘፈቁ እስከመቼ ዋጋቸውን ያገኛሉ የሚለው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ መታገል እንደሚያስፈልግም የኮሚቴው አባል ጥሪ አቅርበዋል።

በአከባቢው በተለይም ባለፉት አራት አመታት ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት መብት እንዲከበር ወጣቶች፣ ምሁራን፣ በመንግሥት መዋቅር የሚገኙ ባለስልጣናት፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የትግሉ አካል በመሆን የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል፣ አካል በማጉደል፣ ከስራና ከስልጣን በመነሳት፣ ለእስርና ለስደት ህይወት በመዳረግ መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን እስከዛሬም በዛ ምክንያት ከስራቸው ተፈናቅለው ቤተሰብን ለችግር አጋልጠው የስደት ህይወት እየገፉ የሚገኙ በርካቶች መሆናቸው ይታወቃል። በWolaita Times ሚዲያ የተጠናቀረ በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቤታሎ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *