
በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከሌዊ ሪዞርት ሆቴል እስከ ግብርና ኮሌጅ ያለውን መንገድ በያዝነው 2013 ዓ ም ለማሰራት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የአለምአቀፍ ጨረታ ያወጣ ቢሆንም እስካሁን ምንም እንቅስቃሴ አለመጀመሩ በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ ነው ተባለ።
ከሌዊ ሪዞርት አንስቶ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ የሚደርሰው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ አኳያ በአገልግሎት ጥራትና ስፋት ውስንነት የሚስተዋልበት ዋናው ያስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ በኮንክሪት አሰፋልት ሊሰራ መሆኑ ተነግሮ ነበር።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በዎላይታ ሶዶ ከተማ ባለፉት ዓመታት በከተማው ዕድገትና ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምክንያት በማድረግ ለትራፊክ አደገኛ መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ውስንነትና ችግሮች ሲስተዋልበት የነበረውን ከለዊ ሪዞረት አንሰቶ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ የሚወዝደውን ዋና የአስፋልት መንገድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በ2013 በጀት ዓመት የአስፋልት ኮንክሪት ለመስራት አለም አቀፉ ጨረታ እንደወጣ በመረጃ አስደግፈን ማሳወቃችን ይታወቃል። በተጨማሪም ከሶዶ አውራጎዳና ቆንቶ አረካ አስራ አምስት ክ.ሜ መንገድ በአጠቃላይ እንደሚሰራ ጨረታ ማውጣቱም የሚታወስ ነው።
ነገር ግን እስካሁን የበጀት ዓመቱ እየተጋመሰ ቢሆንም ስራውን ለመጀመር የሚደረግ እንቅስቃሴ አለመታየቱ ለብዙዎች ጥያቄ መፍጠሩን ተከታዮች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠይቆናል።
https://t.me/Kiikiya
17/06/13 ዓ. ም/ Wolaita Times, Sodo, Ethiopia🇪🇹