የጦና ንቦቹ በኢትዮጵያ ዋንጫ ፈረሰኞቹን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ አልፏል።

በዛሬው ዕለት በአራተኛ ዙር የኢትዮጵያ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠሙት ዎላይታ ዲቻ ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጧል።

በሁለተኛ ዙር ጨዋታ ሀምበሪቾን ሁለት ለአንድ፣ በሦስተኛው ዙር ደግሞ ሻሸመኔ ከተማን አምስት ለሁለት በማሸነፍ ወደ አራተኛው ዙር የተሻገሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአፍሪካ ውድድሮች ያላቸውን ተከታታይ ተሳትፎ ለማስቀጠል ዎላይታ ድቻን የገጠሙ ቢሆንም ጉዟቸውን በሽንፈት ቋጭቷል።

በሌላ በኩል ደሴ ከተማን ሦስት ለአንድ አሸንፈው ውድድሩን የጀመሩት ዎላይታ ድቻዎች በሦስተኛው ዙር ጠንካራ የተከላካይ ክፍል ያለውን ሀድያ ሆሳዕና በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፈው ወደ ዙር እንደመብቃታቸው ትልቅ ግምት በተሰጠው መሠረት ተሳክቶላቸዋል።

ትናንት በተካሄደ አንድ ጨዋታ የጀመረው አራተኛው ዙር የኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ላይ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያሸነፈው ዎላይታ ዲቻ የኢትዮጵያ መድንን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 – 2 ዎላይታ ዲቻ
82′ ታምራት ኢያሱ   45+1′ ቢኒያም ፍቅሩ
                           49′ ብስራት በቀለ

1 thought on “የጦና ንቦቹ በኢትዮጵያ ዋንጫ ፈረሰኞቹን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜ አለፉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *