
ለዎላይታ ብሔር ጥንታዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ወታደራዊ ሳይንስ የታከለበት እንደሆነ ኢትዮጵያ በፋሽስቱ ጣሊያን በተወረረችበት ጊዜ ልዩነትንና የዉስጥ ችግር ዉስጥ ቢኖሩማ ሆ ብሎ ከየትኛውም አከባቢ በላይ የሰለጠኑ የጦር መሪዎች (ጋዳዎችን)፣ በርካታ ወታደሮችን፣ የቀንድ ከብቶችን፣ የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም ባህላዊ የህክምና ባለሙያዎችን መላኳ ዎላይታ የሰለጠነ ሰራዊት በአድዋ ድል አንበሳ ድርሻ እንዳላት የሚያሳይ የመሰረታዊነት እና የአንድነት ሚስጥር ነዉ በሚል የተለያዩ የታሪክ ድረሳናት ያስረዳሉ።
ካዎ ጦና ጋጋ (ንጉስ ጦና) የዎላይታ ህዝብ በ19ኛው ክ/ዘመን ገደማ በታላቅነትና በግርማ ሞገስ ተላብሶ በፍፁም ዲሞክራሲያዊ ወደሚያስብል አኳኃን በጥበብና በእውቀት ከመምራትም ባሻገር፥ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ብቸኛው ወደ ሚያስብል ደረጃ የመገበያያ ገንዘብ ማርጯ (The Wolaita people local currency) በመቅረፅ የግብይትና የንግድ ሰንሰለቶችን ከአባይ ማዶ እስከ ሱዳን፣ እንዲሁም እስከ ሩቅ ምስራቅ ህንድ ሀገራት ድረስ የወጪና የገቢ ንግዶች ላይ ተሳትፎ እንዲኖር የበኩላቸው ድርሻ የተወጡ ታላቅና ገናናው ንጉስ እንደ ነበሩ ህያው ታሪክ ይመሰክራል።

ከዛም ባሻገር የጣሊያን ወረራ ጊዜ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ እስከ ቦረና ድረስ የጦር መሪ እንደነበራቸው፥ ይህንን እውነተኛ ታርክ እነሆ አዲስ አበባ 4 (አራት ኪሎ) በባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ በኢተገ ጣይቱ የተተከለው የካዎ ጦና ጋጋ የክብር ሐውልት ህያው ምስክር ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን እስከ ሰሜን ክ/ሀገር ድረስም ከአፄ ሚኒሊክ፣ አሉላ አባ ነጋና ከሌሎች ጀግኖች ጋር ሆነው ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ዋጋ በመክፈል የጣሊያን ባንዳዎችን አንበርክከዋል።
“የአድዋን ድል ስናከብር እውነቱ ተሸፍኖ መሆን የለበትም። በእርግጥ በጦር ሜዳ ማሸነፍና መሸነፍ በጦር ብቻ አለመሆኑ ግልጽ ነው። ለወታደሩ ስንቅ ለማቅረብ ኢኮኖሚ ከሌለ ሠራዊቱ ጠላት በልጦት ሳይሆን ረሃብ ተዋግቶት ይሸነፋል። በቂ ስንቅ እያለም ሠራዊቱ በስነልቦና መረበሽ እንዳይሸነፍ የሠራዊቱን ሞራል የሚያነሳሳ የሙዚቃ ባንድ ጭምር ለድሉ መገኘት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ነገር ግን ድሉ የሁሉም አካላት ድምር አስተዋጽኦ ውጤት ሆኖ ሳለ ከድሉ በኋላ የሙዚቃ ባንድ የጦርነቱ አሸናፊ እኔ ብቻ ነኝ ቢል አሳፋሪ ነው። በአድዋ ጦርነት የዎላይታን ተሳትፎ ለየት የሚያደርገው ሠራዊትንም የሠራዊት ስንቅ ከማቅረብም ረገድ ከድርሻው በላይ ማዋጣቱ ነው።
እኛ የዛሬዎቹ ትውልድችም የታጋረጡብንን ፈተናዎች በአብሮነትና በአንድነት መንፈስ በማሸነፍ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ልዕልናዋ በመውሰድ ሌላ ደማቅ ታሪክ ለመስራት መነሳሳት እንዳለብን ከዓድዋ ትውልድ መማር ይገባናል። በመሆኑም ጊዚያችንን፣ እውቀታችንን፣ ጉልበታችንና ጥረታችንን ማዋል ያለብን ለታጋላጭነታችን ምንጭ ሆኖ በቆየው ድህነታችንና በከፋፋዮቻችን ላይ መሆን አለበት::
የአድዋ ድል ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቀውን ነጭ ጥቁር ማሸነፉና ሌሎች ብዙ የሚያስደምም እውነታዎች ያሉበት ሆኖ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሆነን ሳናከብር የጥቁር ሕዝቦች ድል፤ የአፍሪካውያን ድል ምናምን እያልን አድማሱን ከማስፋት መጀመሪያ እኛ ኢትዮጵያዊያን የጋራ በዓላችን መሆኑን አምነን አብረን እናክብር፡፡
ጅቡቲ፣ ኬንያ ኡጋንዳና ሩዋንዳ ወዘተ ጎረቤቶቻችን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጡበትን ዕለት እንጂ የአድዋ ድልን መቼ ተቀብለውት ብሔራዊ በዓላቸው አድርገው አውጀው መድፍ ተኮሱ? ለነገሩ እኛ መች ተስማማንና እነሱ ያክብሩት፡፡

አንዳንዱ የአድዋ ድል የአፄ ምኒልክ የግላቸው ጀብድና ጥንካሬ ውጤት እየመሰለው ለሌላው ትግል እውቅና መስጠት ይሳነዋል፡፡ ሌላኛው ተነስቶ በወቅቱ የጠቅላይ ጦር አዛዡን የአፄ ምኒልክን ጀግንነት ላለመቀበል እኔ ብዙ የጦር ባልደራሶች አዝምቻለሁ፤ ብዙ መስዋዕትነት ከፍያለው ወዘተ ብሎ ይቀባጥራል፡፡
የአስተዋጽኦ ዓይነትና መጠን ይለያያል እንጂ በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ አንድነት የተቀላቀሉ ሕዝቦች ሁሉ በአቅማቸው ልክ በአፄ ምኒልክ ጥሪ መሠረት ከጎናቸው በመቆም ለአድዋ ጦርነት በሰውም በንብረትም ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰዋል፡፡ የጋራ ትግል አድርገው አስደማሚ የጋራ ድል የሆነውን የአድዋ ድል አስመዝግበዋል፡፡
በታርክ ፀሃፊት ምንም ትኩረት ያልተሰጠው በአደዋ ጦርነት ላይ ጀብድ የፈፀሙ ከዎላይታ በንብ ጦርነት የአፄ ሚንልክን ጦር 7 ጊዜ በማንበርከካቸው ለአዱዋው ጦርነት ለመድፍ ውግያ ተመልምሎ አርበኝነታቸውን ያሳዩ ጀግኖችንና ከዎላይታ ተነስቶ የሸዋ ጦርን በመቀላቀል አድዋ ላይ ጠላትን ያንበረከኩ ጀግኖችን ታርክ ቀኑን ጠብቆ ይዘከራል” የሚለው እምነት ብዙዎች እንዳላቸው ይደመጣል። አድዋ ላይ ማንም ማንንም ቀጠሮ አላዋጋም ማንም የማንም ቅጥረኛ አልነበረም።
አድዋ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ሉዐላዊነት የተዋደቀበት፤ በሀገር ፍቅር ደሙን ያፈሰሰበት አጥንቱን የከሰከሰበት፤ በመስዋትነት ሀገር ያቆየበት የነፃነት የድል በዓል ነው።
የአሁኑ ገዥ ፓርቲ (መንግስት) ከዚህ ስህተት ተምሮ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ትግል ውጤት የሆነውን የጀግንነት በአል አድዋ በነገው ዕለት የካቲት 23 በሀገር ደረጃ ለክብሯ የተዋደቁ ሁሉንም የኢትዮጵያ ጀግኖች በማሰብ እንዲከበር ማድረግ አለበት፡፡
ዎላይታ ብሔር ጥንታዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ወታደራዊ ሳይንስ የታከለበት እንደሆነ ኢትዮጵያ በፋሽስቱ ጣሊያን በተወረረችበት ጊዜ ከየትኛውም አከባቢ በላይ አጋዥ ሀይል ሳይጨምር የሰለጠነ ዘመናዊ በቁጥር 60,000 በላይ የሚሆን ወታደር መላኳ ዎላይታ በአድዋ ድል አንበሳ ድርሻ እንዳላት የሚያሳይ የመሰረታዊነት እና የአንድነት ሚስጥር ነዉ።
በአድዋ ድል 🇪🇹የኢትዮጵያዊያን በተለይም የዎላይታ ህዝብ (ካዎ ጦና አስተዋጽኦ) እንዴት ነበር❓
“የአድዋን ድል ስናከብር እውነቱ ተሸፍኖ መሆን የለበትም። በእርግጥ በጦር ሜዳ ማሸነፍና መሸነፍ በጦር ብቻ አለመሆኑ ግልጽ ነው። ለወታደሩ ስንቅ ለማቅረብ ኢኮኖሚ ከሌለ ሠራዊቱ ጠላት በልጦት ሳይሆን ረሃብ ተዋግቶት ይሸነፋል። በቂ ስንቅ እያለም ሠራዊቱ በስነልቦና መረበሽ እንዳይሸነፍ የሠራዊቱን ሞራል የሚያነሳሳ የሙዚቃ ባንድ ጭምር ለድሉ መገኘት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ነገር ግን ድሉ የሁሉም አካላት ድምር አስተዋጽኦ ውጤት ሆኖ ሳለ ከድሉ በኋላ የሙዚቃ ባንድ የጦርነቱ አሸናፊ እኔ ብቻ ነኝ ቢል አሳፋሪ ነው። በአድዋ ጦርነት የዎላይታን ተሳትፎ ለየት የሚያደርገው ሠራዊትንም የሠራዊት ስንቅ ከማቅረብም ረገድ ከድርሻው በላይ ማዋጣቱ ነው።
ዎላይታ የአገሪቷ 2% ቁጥር ይዞ 25% ሠራዊት አዋጥቷል። ከሰራዊቱ ስንቅም አንጻር ከ50% በላይ ስለማዋጣቱ ታሪክ ምስክር ነው። ይህ በፎቶ የተካተተው ደህንነቱ ከተሰኘ ከይስማዕከ ወርቁ ድርሰት በገጽ 94 ከተመለከተው ጽሑፍ የተወሰደ ፎቶ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ረቂቅ የስነ-ጽሑፍ ችሎታው የተንጸባረቀበት ነው። ‘ደህንነቱ’ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመሥርቶ ዓለም በስለላና በጦርነት የደረሰበትን የዕውቀት ደረጃ በልብወለድ መልክ የሚያሳይ ድንቅ ስነ-ጽሑፍ ነው። የአድዋ ድል በትክክል የኢትዮጵያዊያን የጋራ ድል ነው።
አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ በጀመሩት ሂደት ከአድዋ ጦርነት ሁለት ዓመት ቀድሞ በ1894 (በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር) ኢትዮጵያ ከሞላ ጎደል አሁን ያላትን ቅርጽ ለማስያዝ የቀራቸው ከባዱ ትግል በካዎ ጦና ከሚመራው ዎላይታ ጋር የመጨረሻውን የኢትዮ-ዎላይታ ጦርነት መግጠም ነበር፡፡
አፄ ምኒልክ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ድል ይሰጣቸው የነበረውን ታቦት አስቀድመው ራሳቸው ጦር መርተው ሁሉንም የጦር መሪዎቻቸውን አስከትለው ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ወደ ዎላይታ ዘመቱ፡፡
ጣሊያን ከሰሜን በኩል የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ሙሉ የኤርትራን ግዛት ይዞ ጠላትን ለመፋለምና የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበር ለጦርነቱ ዝግጅት እየተደረገ እያለ አፄ ምኒልክ የዎላይታውን ዘመቻ ለምን አስቀደሙ ?
ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሚሆኑ በርካታ ነጥቦች የአፄ ምኒልክ ኢትዮጵያ እና የካዎ ጦና ዎላይታ ያደረጉትን ዘመቻ አብሯቸው ወደ ዎላይታ ዘምቶ በአካል ጦርነቱን አይቶ የዘገበው ፈረንሣዊው ጄ.ጂ. ቫንደርሃይም “ዘመቻ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር” በሚለው መጽሐፉ ላይ ጠቅሷል፡፡
1) ዎላይታ ኢትዮጵያን በሦስት አቅጣጫ የሚታዋስን ሀገር የነበረች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ አንድነት ለማምጣት ራስ መንገሻ አትከምን ጨምሮ በተለያዩ የጦር አበጋዞች የተመሩ ተደጋጋሚ ጦርነቶች ውጤት አልባ በመሆናቸው አፄ ምኒልክ ራሳቸው ጦሩን መርተው ዎላይታን በማሸነፍ ከቤተመንግሥቱ አካባቢ ጭምር የነበረባቸውን ጫና ለመቀነስና ትልቁን የቅርብ ጠላት ቀድሞ ለማሸነፍ፣
2) የንብ ጦርነትን ጨምሮ ዎላይታዎች የሚጠቀሟቸውን ( Biological weapons ) የተለያዩ የውጊያ ስልቶችንና መሣሪያዎችን ቄራ ጎፋ ላይ አርፎ ከኢትዮጵያዊያን ፈረሰኛ ጦር ጋር ተዋህዶ አድዋ ላይ ያስደመመውን የዎላይታን ፈረሰኛ ጦር ለመጠቀም፣
3) የዎላይታ ምድር እጅግ በጣም ለም መሆኑን ገልጾ ከጦርነቱ ማብቂያ በኃላ ወደ ማዕከላዊ መንግሥት የተነዱ 36,000 ከብቶች መሆናቸውን በጦርነቱ ወቅት በማረኳቸው ቦታዎች የአፄ ምኒልክ ሠራዊት ያረዱትን በልተው ሳይጨርሱ ሌላ ከብት ያርዱ እንደነበር፣ ጦርነት አልቆ ካዎ ጦና ተማርከው እንኳን ዝርፍያ እንዳልቆመ በመጥቀስ የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል በክፉ ቀን ድርቅ በእጅጉ ስለ ተጎዳ በበቂ ሁኔታ ተጨማሪ ስንቅ ለአድዋ ለማግኘት፣
4) አፄ ምኒልክን ከቀድሞ ዘማቾቻቸው የሰሙትና መጨረሻ ላይ በአካል መጥተው ካስደመማቸው ነገር ውስጥ አንዱ በዎላይታ የነበረው የሕዝብ ቁጥር በመሆኑ ዳግም ሕዝቡ እንዳያምጽና ወደ ንግሥና ሥርዓቱ እንዳይመለስ እንዲሁም የሀገርቱን ጦር ለማጠናከር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ፣ ወሎ፣ ሸዋ ወዘተ ተወስደው አገልጋይና ወታደር ለማድረግ ወዘተ የሚሉ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፡፡
ይህ ለአድዋ ጦርነት በቅርብ ርቀት ላይ ወደ ኢትዮጵያ አንድነት የተቀላቀለውን የዎላይታ ሕዝብ አስተዋጽኦ ብቻ ሲሆን በዘመናዊው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ የአድዋ ድል ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በሁሉም አቅጣጫዎች ኢትዮጵያዊያን የአቅማቸውን ያበረከቱበት የኢትዮጵያዊያን የጋራ ድል በመሆኑ በሁሉም አከባቢ ብሔራዊ በዓላችን በድምቀት ሊከበር ይገባል፡፡
ዎላይታ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ ዳር ይዞ አያዉቅም። የዎላይታ አባት የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ፓትርያርክ የሆነ አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያ ህዝብ ከጠላት አድነዉ አገራቸዉን ከወራሪው ፋሽስቱ ነፃ አዉጥቶ ለራሳቸው የተሰዉ የዚህ ታላቋ ዎላይታ ብሔር የተገኙ ጀግና ናቸዉ።
አቡነ ጴጥሮስን ፋሽስቱ እንዲህ ሲል ነበር “ይህ ህዝብ በባርነት እንድገዛ ገዝቷቸዉ” ብለው ባሉበት ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ እንደዚህ ብለው ገዘቱ፣ “ይህ በገዛ አገሩ ለጠላት ተገስቶ እንዳይኖርና ከጠላቱ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል እንድያካሂድ፣ በገዛ አገሩ ሀይማኖቱን ሳይቀይር፣ በራሱ መሪ እየተመራ በነፃነት እንድኖር ገዝችያለሁ” ብለዉ ጣሊያን ያለዉግያ የጣሉ አቡነ ጴጥሮስ ከዚህ ታላቋ ዎላይታ ብሔር የተገኙ ነበር።

ከንጉስ ጦና ጋጋ ጋር አድዋ ከዘመቱ የዎላይታ ጦር መሪዎች ውሰጥ የተወሰኑት ስም ዝርዝር በጥቂቱ👇
- ጋዳዋ ቦርሳሞ አንጁሎ
- ጋዳዋ ዋላና አልቤ
- ጋዳዋ ሃጤሮ ሃንቼ
- ጋዳዋ ዶዮ ላቼሮ
- ጋዳዋ አዲማ ዳሌ
- ጋዳዋ አልዳዳ ቃጄላ
- ጋዳዋ አዴሎ ቃጄላ
- ጋዳዋ ዳጎዬ ዳንዶ
- ጋዳዋ ወያሞ አኮ
- ጋዳዋ ዳራራ ዶጄ
- ጋዳዋ ዳስ ፓቴ
- ጋዳዋ ደራራ ማራ
- ጋዳዋ አዴ ወሼ
- ጋዳዋ አልኣ ማኬ
- ጋዳዋ ቀሌ ኮቴ
- ጋዳዋ ፕፓዶ ሌሞ
- ጋዳዋ ማዛና ሌንጎ – – መሆኑን የታሪክ ማህደር ይመሰክራል።
ዎላይታነት ምስጢር መቼም ከቀደምትነትና ከምንጭነት ጋር እንዲሁም ከኢትዮጵያ አንድነት ታሪክ በትክክል በማይነጣጠል ገመድ የተሳሰረ ነው።
እንኳን ለ128ኛው አድዋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🇪🇹🙏🙏
አድዋ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነው🇪🇹🇪🇹