1708692694345

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በፈረቃ እንደሚከፈላቸው ገልጸዋል።

በሥልጤ፣ ሀዲያ፣ ከምባታ፣ ጉራጌና ዞን እና ሌሎች መዋቅሮች ላይ የመንግሥት ሰራተኞች እንደገለፁት ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያቸው ከአንድ እስከ ስስት ወራት ይዘገይባቸዋል።

የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እንዳሳደረባቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ በተለይም አንዳንድ ሠራተኞች ልጆቻቸውን ለመመገብና ለማሳከም ልመና እስከመውጣት መድረሳቸውን ገልፀዋል።

በተለይም ሰራተኞቹ ለዶቼቬለ እንደገለፁት «ደሞዛችንን በወቅቱ ለማግኘት ያልቻልነው ክፍያው በፈረቃ በመፈፀሙ የተነሳ ነው» ብለዋል።

እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ በተያዘው የካቲት ወር መከፈል የነበረበትን የጥር ወርና የዘገየ ደሞዝ ያገኙት ገሚሶቹ የመንግስት ሠራተኞች ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በቀጣዩ ወር የሚከፈላቸው ነው የሚሆነው።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጨምሮ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ተመሳሳይ ችግር ይስተዋላል። ነገር ግን ክልሎቹ ከህብረተሰቡ ግብር እየሰበሰቡ ከፌደራልም የበጀት ድጎማ እየተደረገላቸው ደሞዝ በፈረቃ ወይንም ለወራት ለምን መክፈል እንዳቃታቸው የተባለ ነገር የለም። Wolaita Times