በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንድ የከፍተኛ ባለስልጣን የትምህርት መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ይፋ ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤትና የካቢኔ ጉዳዬች ሀላፊ በመሆን በሹመት እየሰሩ የሚገኘው የትምህርት መረጃ ለማረጋገጥ ወደ አርባምንጭ ዩንቨርስቲ ተልኮ በማኔጅመንት ድግሪ ተመርቂያለው ብለው ያቀረበው መረጃ ሀሰት ሆኖ መገኘቱን ዩንቨርሲቲው አስታውቋል።

ዩንቨርስቲው የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤትና የካቢኔ ጉዳዬች ሀላፊ የአቶ ተፈሪ ሜንታ ሶስተኛ ተራ ቁጥር ላይ ስሙ የተጠቀሰውን ጨምሮ ለማጣራት በቀረበው መነሻ የሌሎችንም አረጋግጦ ይፋ አድርጓል።

በመሆኑም ክልሉ በተጨባጭ ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ ተጠቅመው በትክክለኛው መንገድ ደክመው የተማሩትን ዕድል ጭምር በመዝጋት የመንግስትንና የህዝብ ሀብት ባልተገባ መንገድ የሚዘርፉትን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በመፈተሽ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ እያቀረብን ከላይ ለሌሎችም ማስተማሪያነት እንዲሆን ለህዝብ በይፋ የተጠቀሰውን የክልሉ የርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤትና የካቢኔ ጉዳዬች ሀላፊ ሀሰተኛ የትምህርት ሰነድ በተመለከተ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የሚወሰደውን ህጋዊና አስተዳዳራዊ እርምጃ ለእናንተ ተከታትለን መረጃ እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልፃለን።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *