1709902406523

ኮምሽነሩ የት ጠፉ❓

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ናቸው። የዎላይታ ህዝብን በፓርላማ የወከሉት ናቸው። የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ፕረዚዳንትም ነበሩ።

እኚሁ ኮምሽነር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ይባላሉ። በአሁኑ ወቅት የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን እያገለገሉ እንደሆነ ይነገራል።

ነገር ግን ኮምሽነሩ በምርጫ ካርድ ጥለው ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባልነት ያስገቡ የአከባቢው አርሶአደሮች “ማዳበሪያ ጠይቀው የወረዳው አመራሮች ከአፍር ጋር ቀላቅሎ” ለመስጠት ሲሞክሩ በአጋጣሚ በህብረተሰቡ ትብብር በይፋ ተይዞ ጉዳዩን ወደ እሳቸው ቢሮ በዝርዝር መረጃና ማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡም ጉዳያቸውን ዞር ብለው አላዩም፣ ለማየትም አልፈለጉም።

በዎላይታ ዞን በተለይም አንዳንድ በክልል፣ በፌደራል ካሉ አመራሮች ጋር በመመሳጠር ራሳቸው ባደራጁት ጥቅምና ጎሳ አደረጃጀት የህዝብና የመንግስት ሀብት በተለያዩ መንገዶች እየዘረፉ የህዝብ ውግንና ያላቸው ግለሰቦችና አመራሮች በየጊዜው ለእሳቸው ቢሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአቤቱታ ዶሴ ቢያርብላቸውም፥ እኛም እንደ አንድ የአከባቢውን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ በሚዲያ በተለያዩ ጊዜ ተጨባጭ መረጃ እያቀረብን ቢሆንም ይሄንን ጉዳይ ለመስማት ሆነ ለማየት ለኮምሽኔሩ ጊዜ የላቸውም።

እንዲያውም በቅርቡ በእልህ አስጨራሽ ትግል በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ላይ የተፈፀመውን አስነዋሪ ዝርፊያና ሌብነት በተመለከተ የአማራ ህዝብ ተወካይ የሆነው እነ ክሪስቲያን ታደለ እስኪያጋልጥ፣ የሶማሌ ህዝብ ተወካይ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ለዩንቨርሲቲው የገንዘብ ማሳገጃ እስኪፅፍ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው ደረጃ ተጋልጦ በይፋ እርምጃ የተወሰደበት ክስተት በቅርበት ዩንቨርስቲውን ፕሬዘዳንት ሆነው የመሩት፥ የእዛ አከባቢ ህዝብ በፓርላማ ተወካይ የሆኑ ኮምሽነር ቀደም ተብሎ ከበቂ በላይ መረጃ እያላቸው ለመንካት አልደፈሩም የሚለው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የእሳቸው መስሪያቤት ቤት ( የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ) ኦፊሼል የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች እንቅስቃሴ በተመለከተው ላይ ኮምሽነሩ ብዙም አይታዩም፣ አንዳንድ በሙስናና በብልሹ አሰራር ምክንያት የሚወሰደው ጥቃቅን ጉዳዮችን ሌሎች መዋቅሮች በራሳቸው መንገድ እርምጃ ከወሰዱ በኃላ በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ከሚያደርጉት እየቀዱ ከመለጠፍ በስተቀር እንደ በሀገሪቱ ጉዳዩ ቀጥታ ከሚመለከተው ተቋም ትብብርና ስራ የተወሰደ አንዳች የተለየ ነገር አለመኖሩን ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል።

የቀድሞ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ፕረዚዳንትና የወቅቱ የፈደራል ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር፥ በተጨማሪም በፓርላማ የዎላይታ ህዝብ ተወካይ ቢሆኑም ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በሀገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች በተጨባጭ የሚፈፀሙ መንግስታዊ ሙስናና ብልሹ አሰራር “አይመለከተኝም” ብለው ዝምታ ከመረጡ እሳቸው “ወከልኩ” በሚለው ክልል፣ ዎላይታና አከባቢ እየተፈጸመ የሚገኘውን የተደራጀ ከፍተኛ ሙስናና ሌብነት በተመለከተ እየሰሙ፣ እያዩ እንዲሁም እስከ ቢሯቸው ድረስ ያስተማራቸው አርሶአደሮች ጭምር በተደጋጋሚ ላቀረቡት ቅሬታም ምንም ምላሽ እየሰጡ አይደለምና ክቡር ኮምሽኔሩ የት ጠፍተው ይሁን❓

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቤታሎ የተጠናቀረ ዘገባ