IMG-20240311-WA0013

የዎላይታ አመራር ምደባ ስርዓት ብልጽግና ፓርቲ ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ መሆኑ በብልጽግና ፓርቲ መገምገሙ የዞኑን አመራር ጭንቀት ውስጥ እንደከተተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የአመራሩ ምደባ ከብልጽግና ዕሳቤ እና አሰራር መሪህ ውጭ የሆነው በአራት ዋና ዋና የኔትዎርክ ሰንሰለት እንደሆነ የተገለጸው ኔትዎርክ እንደሚከተለው ይገለጻል፡-

1ኛ. በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፤
2ኛ. በአከባባዊነት ኔትወርክ፤
3ኛ. በትውውቅ እና በጥቅም ላይ የተመሰረተ፤
4ኛ. የቤተሰባዊ ኔትዎርክ ናቸው፡፡

እንደ ታማኝ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ በአቤ-ልጃዊ ኔትወርክ ውስጥ በመሆን ዎላይታን እንደፈለጉ እንዳልነበረ እያደረጉ የሚገኙት ዋና ዋና ግለሰቦች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡-

  • የአሁን የክልሉ ፓርቲ ሪዕዮተ-አለም ዘርፍ ኃላፊ የአቶ ዮሐንስ በየነ የአይን አባት አቶ ተስፋዬ ይገዙ ስሆን ከታች ከወረዳ ጀምሮ በአመጣጡ የክልሉ ምክትል ፕዝዳንት እጅ የነበረው ስሆን ( በአከባባዊነት ነትዎረክም ጭምር የሚገለጽ ግንኙነት ያላቸው ስሆን የአንድ ቀቤለ እንድሁም ሰፈር/መንደር ሰዎች ናቸው፡፡ )
  • በመሠረቱ ለአቶ ዮሐንስ በየነ ሶስት ወንድ ልጆች ስኖሩት የመጀመሪያው ወንድ ልጅ አይን አባት ተብዬው አቶ አሳምነው አይዛ ( የአሁን የዎላይታ ዞን የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ) ስሆን ሁለቱ ወንድ ልጆች መንቲያዎችን ደግሞ የአንዱን አይን አባት አቶ ተመስገን አለማዬው ( የአሁኑ የዞኑ ፓርቲ ሪዕዮተ-አለም ዘርፍ ኃላፊ) እንድሁም ሶስተኛውን ልጅ አይን የያዘው በወቅቱ የዎላይታ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጅ መምሪያ ኃላፊ የነበሩ በአሁን ሰዓት የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጅ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆን የተሸለሙ ሹመኛ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል አቶ መስፍን ዳዊት ( የዎላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ) ወንድ ልጅ አይን አባት በመሆን ወደ ሥልጣን ከዞን ከተማ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊነት በአንዴ ወደ አረካ ከተማ ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊነት የተሸጋገረው አቶ አድማሱ አይዛ ስሆን የተዋጣለት የመሬት አሻሻጭ ነው፡፡

በዋናነት የአበ-ልጅ ኔትዎርኩ በዞን ባለው ልምድ ወረዳዎችም ተለክፈው ሁሉም ወንድ የወለደ ለአይን አባትነት የሚሽቀዳደሙበት እንድሁም የሴት ልጅ አባት የሆኑት ዎላይታ ዞን ላይ ወደ ስልጣን የመምጣት እጣ-ፋንታውን ያመከነ ሆኖ ይታመናል፡፡

  • በተጨማሪም አቶ አሳምነው አይዛ የዮሐንስ በየነ እና ለአቶ ተስፋዬ ይገዙ ልዩ ተጠሪ፤ ተወካይና የሀብት ማካበቻ ቱቦ ስሆን ከፍተኛ የጥቅም ትስስርም ከዚሁ ጋር የሚገለጽ ነው፡፡

የዎላይታ ህዝብ በዚህ በሌብነትና በጥቅም ትስስር በተደራጀው የኔትወርክ ቡድን የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት እንዲሁም በደል እየደረሰበት ይገኛል።

ነገሩን ደግሞ ፍጹም አስገራሚ የሚያደርገው ይህ ለህዝቡም ለፓርቲውም እኩይ አላማውና ድርጊቱ ገሃድ የወጣበት የኔትወርክ ቡድን በተለይ የመንግስት ሰራተኛውን በአበልና በጥቅማጥቅም ዝም ለማሰኘት የሞከረው ሙከራ ሊከሽፍ መቻሉንም ምንጮቻችን አረጋግጧል።

በቀጣይም የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል የዞኑ አመራር የተዘፈቀበትን የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር አንድ በአንድ ስም እየጠቀስን ከሙሉ ማስረጃ ጋር ለህዝብና ለመንግስት ተጨባጭ መረጃና ማስረጃ አስደግፈን እንደምናጋልጥ እየገለፅን በጉዳዩ ዙሪያ የሚወጡ ተከታታይ የምርመራ ዘገባዎች እንድን ግለሰብ በተለየ መንገድ ለመጉዳት ያለመ ሳይሆን አከባቢው ላይ የአመራር ምደባ በጥቅምና በዝምድና በመሆኑ የተከሰቱ ዘርፈብዙ ችግሮችን ለመፍታትና ህዝቡን በቅንነትና ያለልዩነት በእውቀታቸው ብቻ ሊመሩ የሚችሉትን አካትተው በሁሉም መዋቅር እንዲደራጁ ያለመ ስለመሆኑ እንገልፃለን።