1710089797830

የሰላምና ለሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት በሆነችው ሲዳማ ክልል ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 33ኛው የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ አመታዊ ኮንፈረንስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናንና ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከተለያዩ ሀገራት፣ ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች አንዲሁም አከባቢዎች የተሳተፉበት በዛሬው ዕለት በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኗ የሰው ልጅ በሰብአዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድጉ ኮትኩተው ከማሳደግ ጀምሮ ወደ ዘላለማዊ መንገድ እንዲጓዙ ከማደረጉ ባሻገር በሰብአዊ ድጋፍ አቅም ሌላቸው ወገኖች የምትደግፍ ሲሆን በዚሁ በዘንድሮ ኮንግረስም በሲዳማ ክልል ዳሌ ወረዳ ዋራ ሜዳ አከባቢው ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚውል ጤና ጣቢያ ለመገንባት የየአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ቢሾፕ ደጉ ከበደ መሰረተ ድንጋይ አኑረዋል።

በአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ያካሄደው 33ኛው ዋራ ቤቴል ጉባኤ ከየካቲት 28-መጋቢት 1/2016 ዓ.ም በነበረው ኮንፈረንስ ምዕመናኑ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለፈጣሪያቸው ፀሎትና ምልጃ ያደረሱ ስሆን በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ ቢሾፖች፣ ቄሶች፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቄስ ኃይሌማርያም ጨምረው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ተካፍለዋል።

ዋራ ቤቴል “ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎችና ከተለያዩ አለም ሀገራት ያለዘር፣ ቋንቋና ነገድ ልዩነት በአንድ ልብና ፍቅር የተሰበሰቡ በደሙ የተዋጁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራበት ስም ሁሉ በላይ የሆነውን የታላቁን አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እየጠሩ በፊቱ ሲሰግዱና ሲዘምሩ፣ በደዌና በአጋንንት የታሰሩ ሲፈቱ፣ ያየንበት፣ ከዚህ ጨለማ ዓለም አንዱን አምላክ ከምያስክድ ክፉ ትምህርት ሰዎች በንስሐ ሲመለሱ የታየበት ሚሊዮኖች በጉጉት የሚጠብቁት ጉባኤ” እንደሆነ ይነገራል።

የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን🙏
#WaraBetel2024 #WaraCrusade2024
Wolaita Times