ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዛ ስንዴ በግለሰብ ስም ውጪ ቢደረግም እስካሁን የገባበት እንደማይታወቅ ተገለፀ።

አምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከሌላ ቦታ ዳቦ በማስመጣት ተመርቆ ለነበረው የዎላይታ ሶዶ ዱቀት ፋብሪካ ስራ ለማስጀመር በሚል ከወራት በፊት ከዎላይታ ዞን ለስንዴ ግዢ ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ ተመድበው በዎላይታ ገበሬዎች ዩኒየን በኩል ከተገዛ በኋላ በሶዶ ከተማ አንድ ፋይናንስ ባለሙያ አማካይነት ወጪ ሆኖ እንዲረከብ የተደረገ ቢሆንም ስንዴው የት እንደገባ አለመታወቁ ተነግሯል።

አንድ የዎላይታ ሶዶ ከተማ የኦዲት ባለሙያ ከዞኑ ገንዘብ ተመድቦ በዩኒየን በኩል የተገዛው ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ከዩኒየኑ በሶዶ ከተማ ፋይናንስ ባለሙያ አቶ አየለ ማጣሎ በተባለ ግለሰብ ወጪ ተደርጎ ቢወጣም ወደ ፋብሪካው አለመግባቱን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ የኦዲተሮች ቡድን በአሁኑ ሰዓት ሪፓርት ለማውጣት መቸገራቸውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

ይህ ዳቦ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ሥራ ስጀምር በቀን 300,000 ዳቦ እና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም ያለው፥ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ለ171 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ገበያን በማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተገልጾ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የፋብሪካው ሥራ አመራር ቦርድ ተደራጅቷል ቢባልም ሥራ ባለመጀመሩ፣ የአከባቢው አመራሮች በጥቅም ተሳስረው ከላይ የተገለፀ አይነት ስርቆት ውስጥ በመዘፈቁ፣ ለፋብሪካው በቂ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል ባለመመደቡ፣ ለሥራው በቂ ክህሎትና ልምድ ያለው ሥራ አስኪያጅ በውድድር ባለመቀጠሩ፣ ለየሥራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ በቂ ቴክኒካል ባለሙያዎች ባለመቀጠራቸው፣ ጥራት ያለው በቂ ስንዴ አቅርቦት ውስንነት፣ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ችግር ፈቺ የአመራር ሰጪነትና ድጋፍ ባለመኖሩ እንዲሁም ለሠራተኞችም ሆነ ግብዓትና ምርት ለማመላለስ በስጦታ የተሰጠ መኪና ለሌላ ዓላማ በመዋሉ የአከባቢው ማህበረሰብ ከፕሮጀክቱ መጠቀም አለመቻሉን ባደረግነው ማጣራት ለማረጋገጥ ተችሏል።

ፋብሪካው ግለሰቦች በሙስናና በብልሹ አሰራር ተወጥሮ ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው በአሁኑ ወቅት 15 (8.7% ብቻ) ሠራተኛ ብቻ ያለው ሲሆን በቀን በአንድ ፈረቃ ብቻ ከማምረት አቅሙ 1.7% ብቻ ዳቦዎችን እያመረተ ሲሆን በቂ ምርት ባለመኖሩ የተነሳ ለዳቦ መሸጫነት በከተማዋ ከተከፈቱ ሱቆች መካከል 90% የሚሆኑት ዝግ ናቸው። ይህ ፋብሪካ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ አስተዳደራዊ ወጪዎችን እንኳን መሸፈን አቅቶት በቅርቡ ሊዘጋ እንደሚችልም ተጠቁሟል።

የWT ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ👇
ዌብሳይት፡ wolaitatimes.com
ቴለግራም፡ https://t.me/WolaitaTimes
WT መዝናኛ፦ https://www.facebook.com/WT-መዝናኛ-105588772237484/
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/wolaitatime/
ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/wolaitatimes/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *