በደቡብ ኢትዮጵያ ዎላይታ ዞን ከአራት በላይ ወረዳዎች ላይ “የበረሃ አንበጣ መንጋ” የሚመስል ተከስቶ በእንሰት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ ተገልጿል።

የአከባቢው አርሶአደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ባለው እንስት ተክል ላይ የተጋረጠውን አደገኛ ችግር ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ከሁለት ሳምንት ጀምሮ በዎላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ፣ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ፣ ካዎ ኮይሻ ወረዳና ባይራ ኮይሻ ወረዳዎች ካሉት አብዛኛው ቀበሌዎች ላይ አዲስ እንደ “በረሃ አንበጣ መንጋ” አይነት ትናንሽ ነገሮች እንሰት ቅጠል እየበሉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ስለመሆኑ ከስፍራው ከአርሶአደሮችና ግብርና ባለሙያች የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባገኘው መረጃ አረጋግጧል።

ያነጋገርናቸው በአከባቢው አርሶአደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ ለእለት ተዕለት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ባለው እንስት ተክል ላይ ስለተከሰተው ነገር ለዞኑ መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት ሪፓርት ቢናደርግም እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ እንዳልተሰጠው ገልጿል።

በበሽታና በትል የተጠቁ እንሰት ተክሎች መካከል በዎላይታ ዞን ክንዶ ኮይሻ ወረዳ ቦርኮሼ ቀበሌ ላይ የተከሰው አዲስ እንሰት ላይ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው ትል ከታች በፎቶ የሚታየው በዛሬው ዕለት የተወሰደ ነውና ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ከፍተኛ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አስቸኳይ መፍትሔ ቢሰጡ የሚል ጥያቄ አርሶአደሮቹ አቅርቧል።

በተለይም በደቡብ የአገሪቱ ክፍል አከባቢ ዋነኛ ለምግብነት የሚያገለግለው የእንሰት ምርት ሲሆን የተለያዩ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከ25 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አርሶአደሮችም ይህንን ተክል በአግባቡ በመንከባከብ የዕለት ምግባቸውን ከመሸፈንም ባለፈ የገቢ ምንጫቸው አድርገው ይጠቀሙበታል።

ይሁን እንጂ በዎላይታ በዚሁ ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ባለው ተክል ላይ እየታየ ያለውን በሽታ በዘላቂነት ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ትኩረት ባለመስጠቱ፣ የተቀናጀ ጥናት እና ምርምር
ባለመደረጉ ምክንያት በሽታው አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ችግሩ በተከሰተበት አከባቢ እየሰራ የሚገኝ አንድ የግብርና ባለሙያ አስረድተዋል፡፡

በእንሰት ላይ የሚከሰተውን በሽታ መቋቋም የሚችል አዲስ የእንሰት ዝርያ በጥናት እየተደረገ ነው ቢባልም እስካሁን ወደ አርሶአደሮች ጋር አልደረሰም በዚህ ምክንያት በሽታውን ለመከላከል አርሶ አደሩ በባህላዊ መንገድ ቢጠቀምም በሚፈለገው መጠን በሽታውን “መቆጣጠር አልተቻለም” ሲልም ባለሙያው አክለው ተናግረዋል።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *