

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የብላቴ ማሰልጠኛ ተቋም በዎላይታ ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ከዲምቱ እስከ ብላቴ ማሰልጠኛ 22 ኪ/ሜ ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ዝርጋታ መጀመሩ ተገለፀ
የብላቴ መከላከያ ሰራዊት ማሰልጠኛ ተቋም የሀገር መንግስትና የህዝብ መከታ ደጀን በመሆን የተለያዩ ሀገራዊ ግዳጅ ከመወጣት ባሻገር በተለያዩ ልማት መስክ ላይ ፈር ቀዳጅ በመሆን የአከባቢው ህዝብን እያገለገሉ መሆናቸው ይታወቃል።
ይህ በመሆኑ ለአካባቢው ህዝብ እና ለተቋሙ ምቹ የሆነ ከዲምቱ እስከ ብላቴ ማሰልጠኛ ተቋም ድረስ 22 ኪ/ሜ የሚሸፍን ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ሥራ ለመዘርጋት በማቀድ ወደ ተግባር ለመግባት ችሏል።
ከዚህ በፊት በአከባቢው የሚስተዋሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመቅረፍ ለአካባቢው ህዝብና በተለያዩ መስክ ተሰማርተው የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ለሀገርና ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡት ኢንቨስተሮች ደረጃውን የጠበቀ መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ያመረቱትን ምርቲ በቀላሉ ለማውጣት የተቸገሩትን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመቅረፍ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዲምቱ ብላቴ መንገድ ከፍተኛ ሚኛ እንደሚጫወት ከወረዳው አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።