አንድ የዩንቨርስቲ መምህር “የቤት ሰራተኛዋን አስገድዶ ደፍሮ በመግደሉ” ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋሏል።

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ግለሰቡ “በቤቱ የቤት ሠራተኛ ሆና ስታገለግል የነበረችውን ቤተልሄም ሽፈራው የተባለች የ12 አመት ህፃን አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ገድሏል” በሚል ተጠርጥሮ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ከሶዶ ከተማ ፓሊስ ፅ/ቤት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃው ከሆነ ተጠርጣሪው ግለሰብ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር ስር እንዲወል ተደርጎ በከተማዋ አንድ ፓሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የከተማ ፓሊስ ፅ/ቤት የተጣራ ምርመራ ሂደት እንዳይደናቀፍ በሚል ዝርዝር መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከመስጠት ተቆጥቦ የቤት ሠራተኛ ሆና ስታገለግል የነበረችውን የ12 አመት ህፃን አስገድዶ ከደፈራት በኃላ ተገደለች የተባለውን አሰክሬኗን በዛሬው ዕለት ተጨማሪ መረጃ ሲባል ወደ አዲስ አበባ ለፎረንሲክ ምርመራ እንደተላከ አብራርቷል። Wolaita Times

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *