ዶ/ር ጌትነት በጋሻው በምክትል ማዕረግ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ ግብር 8ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሄደ።
ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በዚሁ መሠረት ዶክተር ጌትነት በጋሻው ከተማ:- በምክትል ማዕረግ የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ኢንጂነር ተመስገን ጣሰው:- ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በተያያዘ ዜና የጎፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ማሩፋ መኩሪያ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።