የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ በጠራው ስብሰባ ያለስምምነት ተቋጨ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ትላንት የጠራው ስብሰባ ያለስምምነት መቋጨቱን ተገልጿል።

የፈረንሳዩ ዜና ወኪል የሆነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ድፕሎማቶችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የተወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ተከትሎ “ተፈጥሯል በተባለ የሰብዓዊ ቀውስ” ዙሪያ የጋራ አቋም ለመያዝ የጠራው ስብሰባ ያለስምምነት ተቋጭቷል።

በስብሰባው ላይ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ካላቸው አምስት አገራት ሩሲያና ቻይና እንዲሁም የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል በሆነችው ህንድ በጋራ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት ነው በሚል ውድቅ የምክር ቤቱን የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ እንዳደረጉት የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ያለውን አጠቃለይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ጭምር በግልፅ እንዲዘግቡት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ፈቃድ መስጠቱም የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ ከሁለት ቀን በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣው የአቋም መግለጫ አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ገብተው እጅ ለመጠምዘዝ የሚያደርጉትን ጥረት እንደማይቀበለውም ገልጾ ነበር።