1721149269392

የዎላይታ ኢንዱስትሪ አብዮትን በሚቀጠሉት 20-30 ዓመታት ዉስጥ ለማቀጣጠል ሊወሰዱ የሚገቡ ወሳኝ የስትራቴጂክ ተግባራት⏬ የባለሙያ ትንተና

በዎላይታ ልማት ላይ ለዉጥ ለማምጣትና ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢንዱሰትሪ አብዮት ለማቀጣጠል የሚያስችሉና ስትራቴጂክ ሮድ ማፕ ሊሆን የሚችሉ ተግባራት ከታች በጥልቅ በባለሙያ እይታ በዝርዝር ቀርቧል።

ሀ/ የህዝቡን የሰራተኛነት መንፈስ ስነ-ልቦና መዋቅር ማጎልበትና ማሳደግ (Workaholic and talent mind setting )

በዝህ ስር የዎላይታ ህዝብ በስንፍና ባይታማም ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተያይዞ አይበገርነት፤ የታታርነት፤ የሥራና የቁጣባ ባህል በደንብ ማስረፅና ማጎልበት ይገባል፡፡ ይህም በዉስን የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ላይ ፈጠራና ቁጠባ የታከለበት የማምረት፤ ምርቱን የማዘመን (እሴት በመጨመር) እንድሁም ምርቱን በተገቢ ወቅትና ገበያ በማቅረብ የተሻለ ዋጋ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

የአይበገርነት ባህል በማዳበር ህዝቡ፤ በማምረት ወቅት የተኛዉንም ችግርና መሰናከል ሲያጋጥም በቆራጥነትና በቀላሉ ተስፋ ባለመቁረጥ መንፈስና ወኔ መሻገር ይገባል፡፡ ለዝህ አብነት የሚሆነዉ በመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች መካከል እጅግ ዉስን የሰዉ ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት የያዘች አስራኤል አገር በዓለም በአይበገርነት ተምሳሌት በመሆን በአጭር ጊዜ በረሃዉን ወደ ገነት መለወጧን ማጤን ያሻል፡፡

ይህ አይበገርነት መንፈስ ማጎልበት አስፈላጊነቱ ከማናኛዉንም ተግባር የዎላይታን የኢንዱስትሪ አብዮት ለማቀጣጠል ወሳኝ የሰዉ ልጅ አእምሮን ለዚህ ወሳኝ የልማት ተጋደሎ አስቀድሞ ማዘጋጀት ስለሚያስፈልግ ነዉ፡፡ ምክንቱም እኛ በተፈጥሮ ሀብት የተንበሸበሸበን ቢንሆን እንኩዋን ህዝቡ አእምሮዉ በስራ መንፈስና በታታርነት ስነ-ልቦና መዋቅር ካልተጠናከረ በስተቀር ቆራጥነትን በመላበስ የተፈለገዉን ዉጤት ማስመዘገብ አዳጋች ይሆናል፡፡

በዝህም ረገድ በተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ህዘቡን መቀስቀስና ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ ይህም ህዝቡ የኢነዱሰትሪ አብዮት ማቀጣጠሉ ፈይዳውን በወል ተገንዘቦ ደጋፊና ባለቤት በመሆን ስኬታማ ያደረጋል፡፡

ለ/ ቁጠባ ባህልን ማደበርና ማበልጸግ

በዝህ ስር ገጠሩ ሆነ የከተማዉ ህዘባችን ከንግዱም ይሁን በመቀጥር ከሚያገኝዉ ገቢ ወይም የምርት ዉጤት ለወሳኝና ትርጉም ላሌዉ ዓላማ ማዋል ይኖርበታል፡፡ በምንም መልኩ ራሱና ቤተሰቡን ህይወት በዕቅድና በግንዛቤ በተመሰረተ ኑሮ መምራት እንጂ ደክሞና ለፍቶ ያገኝዉን ገቢ በልታይ ባይነት ማበከን አይገባም፡፡

1. የኢንዱስትሪ አብዮት ለማቀጣጠል ወሳኝ ግብአቶች፤

አንድን ልማት ለማረጋገጥ ወሳኙ ባለድርሻ አካላትና ባለቤት ህዝብ ማስተባርና ማሳመን ነዉ፡፡ ህዝቡ ካመነበት መንግስት የፈለገዉን እንቅፋት በመንገድ ቢያስቀምጥ የዉጥን ህዝብ ማቆም አይቻልም፡፡ ለዝህ ነዉ ከላይ (ነቃተ-ህሊ ወይም ማይንድ ሴት) ማጎልበት የሚያስፈለገዉ ብለን በቅድሚያ ከላይ ያስቀመጥነዉ፡፡ ስለዝህ ህዝቡ የለዉጥ አብዮቱ የራሱ እንደሆነ በደንብ ከገባዉና ከተረዳ የተኛዉም ሃይል ከስኬት ጉዞ ወደ ሓላ ሊጎተት አይችልም፡፡

መንግስትም ቢሆን ህዝቡ በልማቱ አጀንዳ ለመተገበር መጨከኑ ሲገባዉ በዚያን ወቅት ከህዝቡ ጎን መቆሙ አይቀረ ይሆናል፡፡ በዝህም በመንግሰት አሻፈረኝ የተባለበትን አየር ማረፊያና ኢንዱስትር ፓርኮችን የመሰሉ ልማቶችን እዉን ሊናደረግ እንችላለን፡፡

2.መንግስት ራሱ

መንግሰት ህዝቡ የሚፈለገዉን የኢንዱሰትሪ አብዮት ለማቀጣጠል ማገዝ ካልቻለ፤ የሚችለዉን ያህል ወሳኝ ድጋፎችን ማደረግ ይገባል፤ ለምሳሌ ያህል የዉጭ ባለሀብቶችን በመሳብ፤ የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማደራጀትና ለሎችንም ድጋፎችን በማድረግ ሊተባበረን ይገባል፡፡

3. የዎላይታ ባለሀብቶችና ዲያስፖራዎች

በወጭ አገር ያሉ የወላይታ ተወላጆች እና ለሎች ኢትጵያዊያን እንድሁም የዎላይታ ወዳጆች የሆኑ ግለሰቦችና አገሮች፤ ድርጅቶችን በማሳተፍ መዋዕለ ንዋይ ወደ ዎላይታ እንዲፈስ ማድረግ ይጠበቅበናል፡፡

ዋና ዋና ኢንዱስትሪ አዉታሮች በከፊል፤

1. የኢንዱስትሪ ፓርክ

• በተለየም የምግብና የምግብ ማቀነባበሪያ ( የአቦካዶ ዘይት ከአከባቢዉ ጥሬ ዕቃነት በመጠቀም፤ )፣ የሜዲሲናል ፕላንት ማልማትና ማቀነባበር (ዝንጅብል፤ አርቲ፤ ጤና አዳም…. ወዘተ ከበቴሰብ ፍጆታ ዉጭ ባሸግር በጥራት በማምረትና በመቅመም ወደ ዉጭ ገበያ ማቅረብ፡

• የእንስሳት ዉጤት የሆኑ ዳልጋ ከብት ርቢ በዘመናዊ ዘዴ በማልማት ስጋን በማሸግ ለዉጭ ገበያ ማቅረብ፤ ወተትና የወተት ዉጤቶችን በማምረትና በማዘመን ለአገር ዉስጥና ለወጭ ገበያ ማቅረብ፤

• ለዎላይታ አርሶ አደሮች አስከዛሬ ማነቆ የሆነዉን ፋብርካ አፈር ማዳበሪያ በብዘትና በጥራት በማምረት ተደራሽ ማደረግ፤ ለሎችም ሀገራችን ክልሎችና ዞኖች ማቅረብ፤

• ባህር ዛፍን የሚጠቀም የእንጨጥ ስራ ፋብርካዎችን ማስፋፋት ( ቺፍዉድ፤ ፕለይ ዉድ፤ እና ለሎችን
• የአዉቶሞቲቪና የከባድ ማሽኒሪ መገጣጠሚያና አሴምብልይ ፋብርካ ተግባራዊ ማደረግ፤

• የህክምና መሳሪያዎች ማለትም፤ ጉሉኮስ፤ መርፌ፤ ስረንጂ፤ ኦክስጆን፤ ቴስት ኪትስ ወዘተ ማምረት፤
• የጨርቃጨርቅ ዉጤቶችን ማምረት፤

• ከእነዚህ በተጨማሪ የአዋጭነት ጥናት የተደረገባቸወ የቢዚነሲ ዘርፎችን በመለየት ተግባራዊ ማድረግ፤

2. ግብርናን ዘርፍ ማስፋፋትና ማዘመን (ኮሜርሻል ፋርም)

ደንግል የሆኑና ጥቅም ላይ ያልዋሉ መሬቶችን ወደ ሰፋፊ እርሻ ልማቶች በመቀየር ከላይ ለተቀመጡ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት አቅርቦት ማመቻቸት፤ ገበሬዉ በጥራትና በብዛት የሚያገኘዉን የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ የሰብልና የእንሳሳት ዘር በመጠቀም ምርትን ከተለመደዉ አሰራር ልዩ ማደረግ ይጠበቅበታል፡፡ በ (እንዱስተሪ ፓርኩ ዉስጥ የአፈር ማደበሪያ ምርት መኖሩን ልብ በሉ)

3. የገንዘብ ተቋማት ዘርፍን ማስፋፋት

ይህ ከላይ የተጠቀሱትን ልማቶችን ተግባራዊ ለማደረግ እና ለአርሶአደሩና ለወጣቶች በጥቃቂንና መካከለኛ ቢዚነስና ስራ -ፈጠራ ተግባራት ለማሳተፍ እንድሁም የኢንዱስትሪ አብዮትን ለማሳለጥ ወሳኝ በመሆኑ ነዉ፡፡ እነዚህም፤

• የዎላይታ ልማት ባንክ (ለኢንዱሰትሪዉ መጎልበት ብድር የሚያቀረብ)

• የዎላይታ ኢንተርናሽናል ባንክ (የንግድ ባንክ ስራ የሚስራ)

• ማርጩዋ ማይክሮ ፋይናንስ ጥቂት ታታሪ ግለሰቦች እንደነ አቶ ማቴዎስ ባልቻ ያሉት ትንታግ አማካሪዎች ብዙ የለፉበት)

4. ማህባራዊ አገልግት ዘርፍ ማስፋፋት፤

• ሁለት ተጨማሪ ዩኒቨርትቲዎችን በተጠናና ከሶዶ በርቀት በሚገኙ ወረዳ ከተሞች መገንባት፣
• ሆስፒታሎችን በየወረዳዉ ማስፋፈት፤ ትምህረት ቤቶችን ማስፋት፤
• የመሰረተ- ልማት አዉታሮችን(መንገድ፤ ዉሃ፤ መብራት አገልግሎት ወዘተ ማስፋፋት)

5. ሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ማስፋፋት

• በዝህም ረገድ በአባላ አባያና አከባቢዉ፤ አጆራ ፉፋቴዎች ስታንዳርዱን የጠበቀ በአፍሪካና በዓላም ታዋቂ የሆነ ሪዞርትና የቱርሪስት ከተማ መመሰረት፤

• ጥራት ያላቸዉ ባለ 4 እና 5 ኮከብ ሆቴሎችን በሶዶና በለሎች ከተሞች በመገንባት ሶዶንና ለሎችን ከተሞች የኮንፈረንስና የጉዞ ቱርስት ማዕከል ማደረግ፡(ለዚህም አሁን እየጀመሩ ያሉትን ባለሀብቶችን ማበረታታትና እና ክትትል በማደረግ መንቀሳቀስ፤

• የዳሞታ ተራራን መልሶ በማልማት የተለያዩ ሰዉ ሰራሽ ሀይቆችንና ቦታንክ ጋርድን፤ ሎጀችን መገንባት፤

6. መዋቅራዊ ና አስተዳደራዊ ልማት

በዝህ ለገድ ዎላይታ ብቻዉን ወይም ለሎች ፊቃደኛ ወንደም ህዘቦችን በማከል በኢትዮጵያ ህገ- መንግሰት በሚፈቅደዉ መሰረት የክልል አደረጃጀት ህልውና መቀዳጀት ከላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መጀመሪያዉ መሆን ይገባል፡፡

በተለይም ይህ የልማት ለዉጥ እንዲረጋገጥ ከህዝብ ብዛት መነሻ አሁን ያለዉን የወረዳ አደረጃጀት ወደ 40 -50 ከፍ በማደረግ አሁን ያለዉን ከተማ አስተዳደር አደረጃጀት 15-20 ከፍ በማድረግ እጅግ ብዙ የተማሩ ወጣቶችን ወደ ስራ ማሰማራት አንዱ ዉጥን ይሆናል፡፡

7. የተማሩት ወገኖቻችን ወደ ዉጭ አገራት መላክ፤

ይህ ዓይነቱ የአካደሚክ ምሁራንን ወደ ዉጭ አገር ስራ ስምሪት መላክ (Expatriate migration ) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በብዙ አፍሪካ አገራት ያልተለመደ ቢሆንም የሩቅ ምስራቅ አገሮች የሆኑት ህንድና ቻይና እጅግ የተማሩ ዜጎቻቸዉን ወደ ዉጭ በመላክና (ወደ አፍሪካ አገሮች) እነርሱ ወደ አገር ቤት በሚልኩት ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ ኢኮኖሚያቸውን እንደደጎሙ ይታወቃል፡፡

ለምሳሌ ከቅርብ ዓመታት በፊት በአዳዲስ መልክ በተመሰረቱ የአገራችን ዪኒቨርሲቲዎች የህንድ አካዳሚክ ፕሮፈሰሮችና ዶክተሮች በብዘት ገበተዉ በማስተማርና በምርምር አገልግሎት እንደሰጡና አሁንም እየሰጡ እንዳሉ ይታመናል፡፡ የዎላይታ ተወላጅ ምሁራን የዉጭ አገር የአካደሚክ የስራ ስምሪት ለማገኝት የአገራችን ትምህርት ጥራት ፈተና እንደሚሆን ቢታመንም በጊዜ ሂደት ግን ይህ ቅዠት ቢመስልም እዉን መሆኑ አይቀረም፡፡

በመሆኑም ይህ በሚቀጥሉት 20 ዓመታ የወላይታን የኘኢንዱስትሪ አብዮት ለማቀጣጠል ወሳኝ ነጥቦች ስለሆኑ ሁሉም ይህንን ሃሳብ በመጋራትና ተጨማሪ ሃሳብና የሚቀር ነገር ካለም በማከል ይህንን በስትራቴጂክ ቅድ አካል በማደረግ መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ በMatusala Mena በድጋሚ የቀረበ Wolaita Times