1000016032

ፕረዚዳንቱ ከክልሉ ካብኔ ውሳኔ ውጪ በግላቸው አምስት መቶ ሚሊዮን ብር መስጠታቸው ህገወጥና ኢፍትሃዊነትን በአደባባይ የገለጠ አድሏዊ አሰራር መሆኑን አንድ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ ለትውልድ አካባቢያቸው በክልሉ ካብኔ የጋራ ውሳኔ ባልተሰጠበት ለአርባምንጭ ከተማ ስታዲየም ግንባታ በሚል ከመንግሥት በጀት በዛሬው ዕለት 500 ሚሊዮን ብር መስጠታቸው ጫፍ የወጡ አድሏዊ አሰራሮች አንዱ ማሳያ እንደሆነም አስረድተዋል።

እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደማሳያነት ከአራት ወር በፊት ገደማ በዎላይታ አረካ አቅራቢያ ለመገንባት በይፋ የተጀመረው የአውሮፕላን ማረፊያ ጉዳይ ሲሆን ተቋራጮቹ ክልሉን “በአንድ አመት አጠናቀን እናስረክባለን ከይገባኛል ነፃ አድርጉልኝ” ካሉ 4 ወር አልፏል፤ ከክልሉ እንዲሸፈን የተጠየቀው 130 ሚሊየን ብር ብቻ የካሳ ገንዘብ ቢሆንም ትኩረት በመነፈጉ በአውሮፕላን ማረፊያ እጦት ምክንያት ከተማዋ በርካታ ልማት እያጣች መሆኑም ግልጽ የፓለቲካ ሴራ አካል ነው” በሚልም ገልፀዋል።

ሌላው በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ የአስፓልት መንገድ ስራ ተስተስጓጉሎ የሚገኝ ሲሆን “አመራሮቹ በሚዲያ እርስ በእርስ ሹክቻ ተጠምዷል፥ ዛፍ ነቅሎ አስቆርጦ የመንገድ ስራው ተጧጡፏል እያሉ ቢሆንም የመብራት፣ የስልክ እንጨትና የትራፊክ መብራት አልተነሳም፥ ግንባታው ከተጀመረ 2 ወር ሞልቶም ያኔ ፌስቡክ ላይ ለመልቀቅ በቆፈሩበት ቆሟል፤ ምንም እንቅስቃሴ የለም” ሲል አንድ የአከባቢው ነዋሪ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

እኚሁ የፓለቲካ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተለው አሁን ያለውን ሁኔታ ከብዙ መነሻዎች በመነሳት ሲገልፅ “እንዲያው ደቡብ ኢትዮጵያ የተባለ ክልል በልዩነት የዎላይታ ህዝብ ጥቅምና ዕድገት ወደኃላ ለመጎተት የተመሠረተ እየመሰለኝ ነው፣ ለምሳሌ በቅርቡ ካራት፣ ጂንካ፣ ሳውላ ፈርጅ 1 ከተማ እንዲሆኑ ሲወሰን የክልል ማዕከላት ቢሮ አሏቸው ተብሎ ነው። በሁንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና በሕዝብ ብዛት አረካና ቦዲቲ ከእነዚያ የተሻሉ ሆነው ግን ፈርጅ 2 ተብለዋል። በዚህም በግልፅ የህዝብ ጥቅም የማሳጣት ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ያለ መሆኑን ያስተዋሉት ጥቂቶች ናቸው” ሲል ጥልቅ ትዝብቱን አካፍለዋል።

በተጨማሪም በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዞኑ መንግስት ለክልሉ ምስረታ ከሰበሰበው ገንዘብ ከድርሻው 10% ባገኘው ገንዘብ ከቀይ መስቀል በዩንቨርስቲ አደርጎ ዴሪ መንደር ይዞ ከገሱባ መንገድ ጋር የሚያገናኝ አምስት ኪ.ሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ እንዲሁም ቁስቁም ማሪያም እስከ ዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ጀርባ ይዞ እሰከ ዴሪ ጋንዳባ ድረስ 5 ኪ.ሜ አጠቃላይ 10 ኪ.ሜ አስፓልት መንገድ ግንባታ የዎላይታ ዞን መንግስት ከቻይና ሁና ሆንዳ አለምአቀፍ ተቋራጭ ጋር በመነጋገርና በስራ ውል በመስማማት ለማስገንባት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ በመግባት ከሶስት ወር በፊት በይፋ ለማስጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም በክልሉ መንግስት እንዲቆም መደረጉን የፕሮጀክቱን ሂደት ለመከታተል የተዋቀረ ኮሚቴ አባላት መካከል አንድ አባል አስረድተዋል።

የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ጨምሮ የክልሉ የፓለቲካና የአስተዳደር መዋቅር ማዕከል በመሆን ይፋ ተደርጎ አገልግሎት እየተሰጠበት የሚገኘው ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ የተወሰኑ መዋቅሮች ቢሯቸውን ለመገንባት ከዞኑ መሬት በመውሰድ እንቅስቃሴ እያደረጉ ቢሆንም ቀሪዎቹና ዋናዎቹ በክራይና ቀድሞ በዞኑ በጀት በተገነቡ ቤቶች ላይ በመሆን ይሄንን ለማድረግ ፍላጎት እያሳዩ አለመሆኑ ግልጽ የፓለቲካ ሴራ እንደሚያሳይም ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያዎች አስረድቷል።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባለፈው ይፋ ባደረገው ምርመራ ዘገባው “የአዲሱ ክልል ከህዝብ ፍትሃዊና ዕኩል ተጠቃሚነት አንፃር ምሁራንና የአከባቢው ነዋሪዎች ምን ይላሉ?” በሚለው አንድ የክልሉን ፓለቲካ በቅርበት የሚከታተል ምሁር ስንጠይቅ “ፍትሀዊ እና ተመጣጣኝ መንግስታዊና ፖለቲካዊ ዉክልና ባለማግኘቱ አንኳር በሆኑ ኢኮኖሚያዊ ሆነ ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስገኘት እንዲሁም የልማት ፍትሃዊነት ለማስጠበቅ ግልፅ እና አሳታፍ የህግ ሥርዓት ተዘርግቶ እንዲመራ መግባባት ተፈጥሮ መስራት ሲገባ በአሁኑ ወቅት ከዚያ እውነታ በተቃራኒው ተጨባጭ የሴራ እንቅስቃሴ መኖሩን መጠቆሙ ይታወሳል።