
የዎላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ሲኒዬር ጂኦሎጅስት አሸናፊ ደስታ ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ግድያው በዞኑ ውስጥ ስር የሰደደው በውሃ፣ መስኖና ማዕደን ዘርፍ ላይ መበራከቱንና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና ንብረት ዘረፋ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል በርካታ መረጃዎች እየወጡ ነው።
አሸናፊ ደስታ በዎላይታ ዞን የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ውስጥ ከርሰ ምድር ተመራማሪ ሆኖ ባገለገለበት ዓመታት በስነምግባር የተገነባና በታታሪነት የተመሰከረለት እንደመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው በጥናት፣ በምርምር እና በመሰል ሥራዎች ስሆን ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ተፈጽሞበት በዚያው ዕለት ምሽት ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም ለማትረፍ እንዳልተቻለ ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።

በዕለቱ አደጋው ከመድረሱ በፊት ከሥራ በጊዜ ወደ ቤቱ ገብቶ ካረፈበት አንድ ጓደኛው (ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው) “ሻይ ቡና እንበል” በሚል ከቤቱ ጠርቶ ለቆ እስኪወጣ አንዳች የሕመም ስሜትም ሆነ ምልክት ያልታየበት፣ አጣዳፊ የሆነ ህመም የለለበት እንዲሁም ህይወቱን ሊነጥቅ የሚችል ምንም ግላዊ ፍንጭ የለለበት ጤናማና ሠላማዊ እንደነበርም ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
ከቤተሰቦችና ከአይን እማኞች የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ፦ አደጋው ከደረሰበት ከ10 ሰዓታት በኃላ ወደ ሆስፒታል መወሰዱንና ለረዥም ሰዓታት ጎዳና ላይ ወድቆ መገኘቱን የገለፁ ሲሆን አሟሟት ሁኔታ በተመለከተ ከሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል የተገኘ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሟቹ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የሳንባ እብጠት፣ የትንፋሽ ማጣት፣ አጣዳፊ የልብና የደም ቧንቧ ችግር፣ በግራ ጆሮ የደም መፍሰስ፣ የስሜት ሕዋሳት በመሉ መዳከማቸውንና እነዚህ አደጋዎች ለሞት መዳረጋቸውን ያረጋግጣሉ።
በሌላ በኩል የፌዴራሉ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዎላይታ ውስጥ ንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት በየዓመቱ የሚያፈሱት ሥራው ሳይሰራ ተመሳጥረው የሚበሉትን እንዲሁም ከዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበው ድንጋይ ከሰል ማዕድን ሻጩ፣ ገዢውና ተቀባዩ ባልታወቀበት የአከባቢው ማህበረሰብ አንዳች ጥቅም ሳያገኝ በየቀኑ በርካታ ተሳቢ ጭነት ተሽከርካሪዎች የሚወስዱትን እንዲሁም ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተጀምሮ ቁፋሮ የተጀመረለት ስምንቶ፣ ፌሮ፣ አሸዋና የመሳሰሉ የግንባታ ቁሳቁሶች ቀርበው በዞኑና በክልሉ ባለሥልጣናት ተመዝብሮ ገና ከጅምሩ የቆመው የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት በተመለከተ ለተቆጣጣሪ ተቋማትና ለሚመለከታቸው አካላት መረጃ ያቀብላል” የምለውም ለግድያው መነሻ ሊሆን እንደሚችል በቅርበት የሚያውቁ ጠቁመዋል።
የመረጃ ምንጩ ጥርጣሬውን ለማጠናከር “ጂኦሎጅስት አሸናፊ ደስታ በተገደለበት ቀን ከማንም አስቀድሞ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ እንዲሁም የቀድሞ የዚሁ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ የነበረው አቶ ተመስገን አለማየሁ በግል ፌስቡክ ገፅ ያስተላለፈው መልዕክት ግዲያው የታቀደና ሌብነታቸውን ለመሸፈን የተወሰደ ፓለቲካዊ ትርጉም እንዳለው ያረጋግጣል” በሚል አስረድተዋል።

የቀድሞ የዚሁ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ የነበረው ከአቶ ተመስገን አለማየሁ መልዕክት “ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ አልፏል” ሲል “ምን አይነት ድንገተኛ አደጋ ነው? ድንገተኛ አደጋ መሆኑን እንዴት አረጋገጠ ? ድንገተኛ አደጋው ከሰው ነው ወይስ ከተፈጥሮ ነው? የሆስፒታልና የፖሊስ ምርመራ ውጤት መጠበቅ ስገባው ራሱን ለምን የሕክምና ባለሙያና መርማሪ ፖሊስ አድርጎ አቀረበ? የዞኑ የመንግስት ተጠሪነት ኃላፊነት ያለው ሰው የግድያውን ምርመራ ውጤት መጠበቅና ከውጤቱ በኃላ ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ ያለውን ዝግጁነትን ትተው እንዴት “ምን ይባላል” በሚል መደምደምና ሌሎችም ወደ ድምዳሜ እንዲመጡ ማድረግ ለምን አስፈለገ?” ጥያቄ በርካቶች እያነሱ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት የዎላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ሲኒዬር ጂኦሎጅስት አሸናፊ ደስታ ግዲያ በተመለከተ ቤተሰቦቹ እውነተኛ ፍትህ በገለልተኝነት እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው፥ በሌላ በኩል የሶዶ ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ቤት መርማሪዎች ጉዳዩን እየመረመሩ ሲሆን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩ የተደረሰበትን ተከታትለው ለማቅረብ ከወዲሁ ቃል ይገባል። #WolaitaTimes #Ethiopia