1000022352

ህብረተሰቡ በወረርሽኝ በሽታ እየተሰቃየ የተጠራው ድግስና የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች ወግ

በዞኑ ሰሞኑን በተከሰተው ወረርሽኝ በሽታ የበርካቶች ህይወት እያለቀ እንደሆነ ከየወረዳው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በየዕለቱ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ህብረተሰቡ በአከባቢው በቂ የህክምና ቁሳቁስ ባለመኖሩ በቀላሉ ልድኑ በሚችሉ በሽታ ምክንያት እየተቀጠፈ ነው። ህዝቡና በአከባቢው የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች አስቸኳይ ድጋፍ ከሚመለከታቸው አካላት እንዲደረግ እየወተወቱ ይገኛሉ።

በተቃራኒው የህዝብ ሞትና ስቃይ ግድ የማይሰጣቸው የሚመስሉ የዎላይታ ብልፅግና አመራሮች የህዝብ ሞት እንዲቀጥል በትንሹም የተከሰተውን ወረርሽኝ የመከላከል እርብርብ እያደረጉ የሚገኙትን የምን ስልጠና እንደሆነ ባይታወቅም ከ1500 በላይ ለሆኑት ለህብረተሰቡ በሽታ መከላከል የመጣውን ገንዘብ ወደ ድግስ ቀይሮ ለመሰባሰብ ቀጠሮው መያዙን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ለመሆኑ ከህዝብ ሞትና ስቃይ በላይ ሆኖ የተዘጋጀው የምን ስልጠና ይሁን ? ትዝብታችሁን አካፍሉን🙏 Wolaita Times #Ethiopia #health