1000028159

“የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት ልብ፤ ሃሳብ፤ ተግባርና መኖሪያቸዉ ሌላ ቦታ በመሆኑ ሶዶ ከተማ የርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ አድርገዉ አይቀበልም…. “ርዕሰ መስተዳድሩ ዎላይታ ሶዶ ስገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል” የሚለዉን መመልከት ለዚሁ በቂ ማሳያ ነው” ተብሏል።

“ዛሬ በይፋ ስለተመረቀዉ ዎላይታ ሶዶ ኢቢሲ ስቱድዮ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተራችንን እያመሰገንን ሳይደራጅ ለፈረሰዉ ክልላችን መፍትሄ ከእርስዎ እንጠብቃለን!” በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ እና ቀጣይ ሁኔታ ላይ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።

“ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚል የለዉጥ ሀሳብ ህብረተሰቡን በቅርበት ሆኖ በማገልገል ህዝቡ ድምጹን የሚያሰማባቸው፤ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮቹን የሚያስተጋባባቸው፤ ባህሉን፣ ወጉን፣ እሴቱን፣ ሀብቱን የሚያስተዋውቅባቸው ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን በየአካባቢው መገንባት መጀመሩ ለሀገር መንግስት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላለዉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩ ልመሰገኑ ይገባል” ሲሉም ያብራራሉ።

አክለውም “ዛሬ በይፋ የተመረቀዉ የዎላይታ ሶዶ ስቱዲዮ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ሆኖ ስራ መጀመሩ የክልሉን ብሔር ብሔረሰቦች ባህልና ወግ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ታሪካዊ ስፍራዎች፤ እንዲሁም ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች በማጉላት የተጀመረውን ሁለንተናዊ ሀገራዊ የልማትና የለውጥ ሂደት ለማፋጠን ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል” ብሏል።

“ይህ ትልቅ ፋይዳ ያለዉ ተቋም በተግባር ሳይሆን በጽሁፍ ብቻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ ተብላ ለሚትጠራዉ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ትልቅ ትርጉም አለዉ፡፡ ለዚህም በዎላይታ ሶዶ እንድገነባ ለፈቀዱት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንደ ዎላይታ ህዝብ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፤ እናከብርሃለን፤ እንወድሃለን” በማለት አመሰግነዋለሁ።

እነኚህ የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ እና ቀጣይ ሁኔታ ላይ በሰጡት የጋራ ሀሳብ “ለጎረበትና ወንድም ለሆነዉ ለጋሞ ህዝብ ትልቅ ክብርና ፍቅር አለን፡፡ አንድነታችንና ወንድምነታችን ከአንድ ግለሰብ ስብዕና ጋር ልቆራኝ አይችልም ነዉ፡፡ ከዛ ዉጪ ዎላይታ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች እንደቤታቸዉ በፍቅር የሚኖሩባት ዞን ናት” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በተያያዘ በአሉታ የሚጻፈዉ ግለሰቡን በብሄሩ ወይም በጭፍን ጥላቻ መነሻ ሳይሆን በግለሰቡ ሰይጣናዊ ተግባሩና እንደ ግለሰብ ለዎላይታ ብሄር ካላቸዉ ተፈሯዊ ጥላቻ ነዉ፡፡ ይሄንን ስንል በማስመሰል ብቃቱ የተካነ ስለሆነ ሰዉን በቀላሉ ስለሚሸዉድ ለሚሰማዉና ለተመልካቹ ግርታ ልፈጥር ይችላል፡፡ እሱን የሚያዉቀዉ ከተግባሩ የቀመሰ ሰዉ ብቻ ነዉ” በሚል ምክንያት አስቀምጧል፡፡

“ለማሳያነት ሌላዉን ሁሉ ትተን በትንሹ ከዚህ ዎላይታ ስቱዲዮ ግንባታ አንጻር ብንወስድ የእሳቸዉ ልብ፤ ሃሳብ፤ ተግባርና መኖሪያቸዉ ሌላ ቦታ ስለሆነ ትዝ ስለዉ ብቻና ለሚድያ ፍጆታ ከ10 ጊዜ በላይ ጎብኝቷል፡፡ በዚህ ግንባታ ላይ የእሳቸዉ ምንም አበርክቶ የላቸዉም ምክንያቱም ህንጻዉ ለሌላ ዓላማ ተገንብቶ የቆየና አሁን ለማስዋብ ሥራ የሚያስፈልገዉ አነስተኛ ወጪ በፌደራል መንግስት የተሸፈነ ነዉ” በመግለጫቸው አስታውሷል።

“ዎላይታ ሶዶ በተግባር የርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ አድርገዉ እንደማይቀመጡ በቀን 23/03/2017 ዓ.ም በሁሉም የዞኑ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ እንድነሳ የተደረገዉ “ርዕሰ መስተዳድሩ ዎላይታ ሶዶ ስገቡ በክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል” የሚለዉን መመልከት በቂ ነዉ፡፡ ይህችን ለምሳሌ ያክል ነች። በክልሉ በርዕሰ መስተዳድሩ የሚሰራዉ ሥራ ድራማ ነዉ እንጅ በተግባር አናገኘዉም፡፡ ይህንን እዉነታ በደህንነት አካላት ማረጋገጥ የሚቻል ነዉ” ብሏል።

አክለውም “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ስላደረጉልን ከልብ እያመሰገንን ከእርስዎ ጋር በተደጋጋሚ እንደተወያየነዉና የእርስዎን ምክር ተቀብለን ወደዚህ አደረጃጀት የገባን ብሆንም በትዕግሰት ብንጠብቅም ከአቅማችን በላይ ሆኗል፡፡ ህልዉናችን በአደጋ ላይ ወድቋል፡፡ ህገ-መንግስታዊ መብታችን የሆኑ ጉዳዮችም ጭምር በአንድ ግለሰብ በጎ ፍቃድ የሚፈጸምበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የህዝቡን የመብት ጥያቄ በመድረክ በፓርቲዉ አሰራር መሰረት ያቀረቡ አመራሮች ከስልጣን እንድነሱ አድርገዋል” በሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

በተጨማሪም “ግማሹ በየፖሊስ ጣብያ እስር ላይ ይገኛሉ፡፡ክልለችን ሆነ ዞናችን በብልፅግና ፓርቲ ሳይሆን በዉስን ቡድኖች እየተመራ ይገኛል፡፡ በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ታፔላ እንጅ እርስዎ የሚመሩት ብልፅግና ፓርቲ የለም፡፡ በእርስዎ ብርቱ ክትትልና ድጋፍ የተደራጀዉና ትልቅ ተስፋ የተጣለበት አድሱ ክልል በጋራ የመበልፀግ ህልማችን እርሶ ባደራጁት አስተባባሪ ኮሚቴ ምክንያት መንገድ ላይ ቀርቷል፡፡ በጋራ አምጤን ያዋልድነዉን እዉነተኛን እርስዎ የሚመሩትን የብልፅግና ፓርቲ ወደ ክልላችን እንድገባ እንድደረግ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን!!! “በታሪክ የምንመዘነዉ ለዎላይታ ሕዝብ ባሳየነዉ ዉግንና መጠን ነዉ!” በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia