1000033702

በክልሉ ምስረታ ወቅት የተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ብር በላይ ከካቢኔ ውሳኔ ውጪ በክልሉ ፕረዚዳንት ትዕዛዝ ብቻ ወጪ ቢደረግም የገባበት እንደማይታወቅ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ወቅት ከተለያዩ መንግሥታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከታዋቂ ግለሰቦች ጭምር ከተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ በየወቅቱ ያለማንም ካቢኔ ሆነ አስተባባሪ ውሳኔ በክልሉ ፕረዚዳንት በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ አዛዥነት እና በአቶ ተፈሪ አባቴ (የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አማካይነት ወጪ የተደረገ ቢሆንም ያለበት ቦታም ሆነ ምን ያህሉ ጥቅም ላይ እንደዋለም እንደቀረም እንደማይታወቅ ያገኘነው የሰነድ መረጃ ያመለክታል፡፡

በክልሉ የካፒታል በጀት/ኘሮጀክት ከፍተኛ ችግር ያለበት ስሆን አጠቃቀሙም ቢሆን ምኑም ከምንም እንደሆነ የማይታወቅ በክልሉ ፕረዚዳንት በጎ ፍቃድ ብቻ የሆነበት ተጨባጭ እጅግ የከፋ ነው ተብሏል።

ይህም እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ በቅርቡ በድጎማ እና በድጋፍ ስም ወደ አርባምንጭ እየፈሰሰ ያለው ስሆን ይህ ተቋም አርባምንጭ ላይ ቤት ስለምሰራ ብቻ ከክልሉ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖ ተልኳል፡፡

በክልሉ የዘላቂ ልማት በጀት አጠቃቀም የሀገሪቱን የፌደረሽን ም/ቤት ህግ ያከበረ እና የተቀመጠውን የበጀት ማከፋፈያ ቀመር የተከተለ አይደለም ብሏል።

የክልሉ ፕረዚዳንት ዎላይታ ሶዶ ከተማ የአስተዳደርና የፖለቲካ መቀመጫ መሆኗን ስለማያምን ህዝቦች አንድ ሆኖ እንዳይኖሩ በከፍተኛ ትጋትና ፍጥነት እየሰራ መሆኑ አንዱ መገለጫው በቀጥታ የኢምግሬሺን መ/ቤት ወደ አርባምንጭ እንድሄድ ማድረጉ እንቅስቃሴ ነው በማለት አስረድቷል።

“ወደ አርባምንጭ ለመውሰድ ለሎችም ተቋማትም እየተዘጋጁ የሚገኙ እንዳሉ መረጃዎቻች ያሳያሉ፡፡ ሌላው ከዚህ በፊት ተነግሮ እንደነበረው የፖሊስ ማሰልጠኛ ከእጃችን ወጥቷል ነገር ግን ለስሙ ፖሊስና ምልሻ ጽ/ቤት በድልድሉ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ናቸው” ብሏል።

ሌላኛው የመረጃ ምንጩ እንዳብራራው፦ “አቶ ጥላሁን ከበደ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንጅ በምንም መመዘኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት ልሆኑ አይችሉም ስንል ያለምክንያት አይደለም፡፡ ባለው ትንሽም ግንዛቤም ከፍተኛ የቅንነት ችግር ያለበት፤ እንደ ሰው ያለው እውቀት ለበቀል የሚጠቀም፤ ሌቦችን ለራስ አድቫንተጅ (ጥቅም) ቁጭ አድርጎ የሚጠቀም፤ “የአሁኑን እንጅ የነጌ ጉዳይ የማይታየው በመሆኑ ለአብነትም፡- ከህዝብ ለህዝብ ሰላማዊ ግንኙነት ጉዳዮችን አርቆ ከማየት ይልቅ የተገኘውን ሁሉ ወደ አርበምነጭ የሚል ጭፊን እይታ፤ ዎላይታንና ብልጽግናን የእንጀራ እናት ልጅ ሆኖ በመሀላቸው ጥርጣሬ እንድኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ጋርም በተቃራኒው እነደቆሙ አስመስሎ በማቅረብ ይህንንም አስተሳሰብ በእኔ አቶ አገኘው ተሻገር በኩል እንድሰርጽ በማድረግ ማስኬድን እንደ ብቸኛው አማራጭ የወሰደ ሴራ ሰው” ብሎታል።

በመሆኑም በክልል ምስረታ ወቅት ከተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ በየወቅቱ ያለማንም ካቢኔ ሆነ አስተባባሪ ውሳኔ በክልሉ ፕሬዝዳንት በሆኑት በአቶ ጥላሁን ከበደ አዛዥነት እና በአቶ ተፈሪ አባቴ (የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ታዛዥነት ወጪ የተደረገ ቢሆንም እስካሁን ያለበት ቦታም ሆነ ምን ያህሉ ጥቅም ላይ እንደዋለም አይታወቅምና የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርቧል።

ማሳሰቢያ፦ የተሰበሰበው 2 ቢሊዮን ገደማ ገንዘብ የሚመለከት ሰነድ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰ ቢሆንም ለሚመለከታቸው አካላት ምርመራ ሂደት እንዲያግዝና እንዳያደናቅፈው ይፋ አላደረግንም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita

ቢደ