1000033696

በዎላይታ አርሶአደሮች ላይ ግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እዳ 120 ሚሊዮን ብር በላይ ወለድ እስኪቆጥር ለምን ? የውሸት ሰነድ ደረሰኝ ፈጥሮ የአርሶአደሩን ገንዘብ የበላው ማነው ?ተጠያቂውስ ? መፍትሔው ምንድነው?- የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ የዎላይታ ዞን በአሁኑ ሰአት በአፈር ማዳበሪያ ብድር ምክንያት የ520 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበትና ከዚህም በጊዜ ብድሩ ባለመከፈሉ 120 ሚሊየን ብር የሚሆነዉ እንደወለድ የቆጠረ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በቅድሚያ ይህ የእዳ ጫና እንዴት ሊፈጠር ቻለ ? ተጠያቂዉስ ማነዉ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ የአፈር ማዳበርያዉ የዞኑ መንግስት በወረዳዎች በኩል ለአርሶ አደሩ በብድር ያደረሰዉ ነው። ገንዘቡ ተመላሽ መደረግ ያለበት፣ ቀጥታ ከአርሶ አደሩ በየወረዳ አመራሮች በኩል ሲሆን በዚህ መሐል እንግዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ገንዘቡ አልተመለሰም ማለት ነው።

ከባንክ የተወሰደ ገንዘብ ደግሞ ወለድ ስለሚቆጥር በየጊዜዉ ይጨምራል። የብር የመግዛት አቅምም በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መንግስት በወሰዳቸዉ እርምጃዎች በጣም ስለተዳከመ ትልቅ ኪሳራ ነው በወቅቱ ገንዘቡ አለመመለሱ። (ኪሳራዉ ለማነዉ የሚለዉ ሊለያይ ይችላል) ተጠያቂነትን በተመለከተ እንግዲህ የተለያዩ እና ብዙ አካላት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል።

በቀጥታ እዳዉን ያልከፈለ አርሶ አደር ካለ ተጠያቂ ነው፣ ተከታትሎ እዳ ያላስከፈለ አመራር ኃላፊነቱን ስላልተወጣ በቦታዉ መቀጠል የለበትም፣ ሌላዉ አርሶ አደሩ ከፍሎ በመሐል ገንዘቡን በየትኛውም መንገድ ወደኪሱ ያስገባ አመራር በሕግ ተጠያቂ ሊደረግ ይገባል።

ማንም የሕዝብን ገንዘብ ዘርፎ የሚፈነጭበት ሁኔታ መኖር የለበትም፣ በቀጥታ ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረግበት መንገድ ካለ ዞኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለበት፣ ያ ካልሆነ ወደተጠያቂነት መሔድ የግድ ነው። በጥቂቶች ጥፋት ጠቅላላ የዞኑ ሕዝብ መሰቃዬት የለበትም።

ከዛ ባለፈ ግን የአፈር ማዳበርያዉ የሚያስገኘዉ ዉጤት ከሚወጣበት ወጪ ጋር ይመጣጠናል ወይ የሚለዉም መጠናት አለበት። አለበቂ ጥናት ለአርሶ አደሮች ከአቅምና ከሚያገኙት ጥቅም በላይ እዳ ዉስጥ እንዲዘፈቁ የሚያደርግ አሰራር ካለም መፈተሽ አለበት።

በነገራችን ላይ በመላዉ ኢትዮጵያ በቂ የአፈር ማዳበሪያ አላገኘንም የሚል የአርሶ አደር እሮሮ መስማት የተለመደ ነው፣ በመንግሥት በኩል እንዲሰራጭ የመጣዉ፣ ተሰርቆ በነጋዴ በኩል በእጥፍ የሚሸጥበት የዝርፊያ ሰንሰለትም በብዙ አካባቢዎች እንዳለም ይነገራል።

ስለዚህ የዎላይታ ዞንም በዚህ እዳ የተዘፈቀበት ምክንያት መሰል ብልሹ አሰራሮች በመንሰራፋቱ ሊሆን ይችላል። ከለዉጡ በሁዋላ በተለይ በዎላይታ ዞን አመራር በየጥቂት ወራት ዉስጥ ሲቀያየር ስለነበረ እና ያልተረጋጋ መሆኑ የራሱ አበርክቶ ሊኖረዉም ይችላል። የአመራር መሳሳትና የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ለዘረፋ ምቹ ከባቢን ፈጥሮ ሊሆን ይችላል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ይህ የእዳ ጫና በዞኑ ላይ የሚያሳድረዉ ተጽዕኖ ምን ያህል ነው ? ከዚህስ የእዳ ጫና ለመዉጣት ዞኑ ከሕግ ተጠያቂነት ባለፈ ማድረግ አለበት የሚሉት ነገር ካለ ቢጠቁሙን ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምናልባት ከዛ በፊት ተጠያቂነት ላይ አንድ ነጥብ ለመጨመር፣ የዞኑ መንግስት ከእርምጃ በፊት ሰዎች አለጥፋታቸዉ እንዳይጉላሉ እና በትክክል ወንጀል የሰራ ሰዉ ብቻ እንዲጠየቅ ጉዳዩን በትኩረት ማጥናት አለበት የሚለዉን ለመጠቆም እወዳለሁ። ወደ እዳ ጫናዉ ተጽዕኖ ስንመጣ ለባንክ በጊዜ ገንዘብ ተከፍሎ ካልተዘጋ ወለድ ስለሚቆጥር፣ የእዳዉ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

በትክክል መሬት ላይ የተሰበሰበዉ ገንዘብም ላይከፍለዉ የሚችልበትም አግባብ አለ፣ ጊዜዉ በተራዘመ ቁጥር። ሌላዉ በተደጋጋሚ ደሞዝ ለመክፈል ዞኑ የሚቸገረዉ በዚህ የተነሳ ነው፣ ብቸኛ ምክንያት ባይሆንም። ከዛ ባለፈ ዞኑ በአቅሙ የረባ የ capital project አቅዶ እንዳይሰራ እጅና እግሩ በእዳ ታስሯል፥ ከዛ ባለፈ በሥራ እድል ፈጠራም ረገድ እዳ ዉስጥ የተዘፈቀ ዞን ከባድ ፈተና እንደሚገጥመዉ ግልጽ ነው።

ስለዚህ የዞኑ አመራሮች ከዚህ እዳ ዞኑን ለማላቀቅ በጣም ሕዝቡን ያሳተፈ ንቅናቄ መጀመር አለባቸዉ። በተለያዬ መንገድ ገንዘብ ከሕዝቡና ባለሐብቶች የሚሰበሰብበትን መንገዶች በመዘርጋት ሥራዎችን መሥራት ያስፈልጋል። ሕዝቡ “አመራር ዘርፎ እኛን አዋጡ ትላላቹ?” ማለቱ ስለማይቀር፣ ተጠያቂነትን ማስፈን የግድ ይላል።

እዳዉን ከፍሎ ዞኑን ነጻ ለማዉጣት፣ ገንዘብ በተለያዬ መንገድ ሰብስቦ ለመክፈል innovative መሆንን ይጠይቃል፣ አመራሩ ከዚህ እዳ ዞኑን በራሱ መንገድ ነጻ ማዉጣት አለበት፣ ገንዘቡን የማስመለስ ሥራ ከዛ በሁዋላም መቀጠል ይችላል። አቅም ካላቸዉ የዞኑ ተቋማት የተወሰነ ገንዘብ በመሰብሰብም እዳዉን ለመዝጋት መሞከር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

ለምሳሌ በአካባቢው በሕዝብ ጉልበት መሠራት የሚችልና ለዛ የተመደበን ገንዘብ ወደ ዞኑ ማዞር የሚቻልበት ፕሮጀክት ካለ፣ በበጎ ፈቃድ ሕዝብን በማንቀሳቀስ፣ ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት፣ ለእዳዉ የሚከፈል ገንዘብ ማግኘት ያስፈልጋል።

በተሳካ ሁኔታ እዳ ካስመለሱ ወረዳዎች ተሞክሮ በመቀመር ገንዘቡን ለማስመለስ ከመረባረብ በተጨማሪ ዞኑ በተለይ የባንክን እዳ ከወዲሁ ቢዘጋ መልካም ስለሚሆን አመራሩ የተለያዩ የገንዘብ ማግኛ ስልቶችን መቀየስ አለበት።

በሺያጭ ገቢ ማግኘት የምንችልባቸዉ ነገሮች ካሉ መሸጥ፣ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ መንቀሳቀስ። የተለያዩ ከፍተኛ ገቢ ሊሰበሰብባቸዉ የሚችሉ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ገቢ መሰብሰብ።

ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በመጨረሻም ምናልባት በተለያዩ ቦታዎች አርሶአደሮች ያልወሰዱትን ማዳበሪያ ወስዷል ተብሎ በውሸት ሰነድ እንዲከፍሉ የሚገደዱበትና በዚያ ምክንያት የተለያዩ ጫናዎች ሲደርስ ይስተዋላል። ምናልባት መንግስት ይሄንን ዕዳ መሠረዝ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር ምን ይመስላል?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እውነት ነው ይሄ በአብዛኞቹ የሚሰማ ቅሬታ ነወሰ። ምክንያቱም ደሃዉ አርሶአደር ማዳበሪያ የወሰደዉ “የእርሻ መሬት የለኝም” ዕዳዉን መክፈል አልችልም በሚል ቅሬታ እያቀረቡ፣ ሌሎች አብዛኞቹ አርሶአደሮች ማዳበሪያ ሳይወስዱ የተጭበረበረ የዕዳ ደረሰኝ የቀረበባቸዉ ነው። ይሄ ብቻም ሳይሆን የተሰራጨዉ ማዳበሪያ ብልሽት የነበሩበት በመሆኑ አርሶአደሩ ዉዝፍ ዕዳዉን የመክፈል አቅም በማጣት ለችግር የተጋለጡ አሉና መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ መክሮና ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ዕዳ ቢሰርዝ ለአርሶአደሩ እፎይታ ይሰጣል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ “የፖለቲካ ወጌሻ” መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።

በውሸት ደረሰኝ የአርሶአደሩን ገንዘብ የበላው ማነው ? ዕ