1000034046

በቅርቡ የኮዎ ጦና አለም አቀፍ ስቴዲየም እውን ይሆናል ?! እንዴት ? መፍትሔውስ ? ….. የዛሬው የዎላይታ ታይምስ የፖለቲካ ወጌሻ ጥንቅር እንደሚከተለው ምላሽ ይዟል 👇

በቅድሚያ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እንላለን🙏 መልካም ንባብ👇

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በቅርቡ የዎላይታ ዞን፣ አለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ የእግርኳስ ሜዳና የመሮጫ track ያለዉን እንዲሁም ከ50ሺ በላይ ሰዉ የሚይዝ ስቴዲየም ለመገንባት አቅዶ የቀድሞ ዲዛይን ተሻሽሎ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወሳል። በቅድሚያ ምን ተሰማዎት ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል። የአካባቢዉ ሕዝብ ያለዉ የስፖርት ፍቅርና የወጣቶቻችንም በእስፖርቱ ለዘመናት የዘለቀ ዉጤታማነትን ያገናዘበ ነው። ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አንዳች ትርጉም ያለዉ ትልቅ ፕሮጀክት እንደሚሆን አልጠራጠርም። ስቴዲየሙ ግን የሚይዘዉ ሰዉ ቁጥር ግን ከ60ሺ በላይ ቢሆን ባይ ነኝ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ ምናልባት ወደፊት ለግንባታዉ ቴሌቶን ማዘጋጀትን የመሳሰሉ ገቢ ለማሰባሰብ ብዙ ዘዴዎችን መጠቀም ሊኖርብን ቢችልም፣ አሁን እንደመነሻ ምልኣተ ሕዝቡን ለማሳተፍ መሰራት አለበት ብለዉ የሚጠቁሙን ነገር ካለ ቢገልጹልን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ዎላይታ ሶዶ የደቡብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ከተማ እንዲሁም የፖለቲካ እና የአስተዳደር ማዕከል፣ የሰፊዉ ደቡብም የታሪክና የኢኮኖሚ ማዕከል እንደመሆኑ ክልሉ ሆነ የፌደራሉ መንግስት አንዳች ደረጃ ፕሮጀክቱን የሚያደርስ መነሻ ገንዘብ መስጠት አለባቸዉ ብዬ አምናለሁ።

ከዛ ዉጪ ግን ሁሉም ሕዝባችንና የልማት አጋር ኢትዮጵያዉያንን ባሳተፈ መልኩ ትልቅ ገቢ ለመሰብሰብ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ ጋር በተለዬ ሁኔታ በመተባበር ከፍተኛ ና አጓዋጊ ሽልማቶችን የሚያስገኝ በ100ብር የሚሸጥ የቶምቦላ ሎተሪ በማዘጋጀት የተሻለ አማራጭ ይመስለኛል።

ሎተሪዉን፦ በ100ብር፦ 1 የእጣ ቁጥር ያለዉ
በ1ሺ ብር፦ 10 የእጣ ቁጥር ያለዉ
በ10ሺ ብር፦ 100የእጣቁጥር ያለዉ አድርጎ ማሳተም ይቻላል።

⨳⨳ባለ 100 ብሩን ለ1ሚሊየን ሰዉ ከሸጥን፣ 100 ሚሊየን ብር ይገኛል።
⨳ባለ 1ሺ ብሩን ለ 100ሺ ሰዉ ከሸጥን 100ሚሊየን ብር
⨳ባለ10 ሺ ብሩን ለ10ሺ ሰዉ ከሸጥን 100ሚሊየን ብር

⨳ባለ 10ሺ ብሩን 10በአንዴ በ100ሺ ብር የሚገዙ 500 ሰዎችን ካገኘን 50 ሚሊየን
⨳ባለ 10ሺ ብሩን 5በአንዴ በ50ሺ ብር የሚገዙ1000 ሰዎችን ካገኘን 50 ሚሊየን
⨳ባለ 10 ሺ ብሩን 100በአንዴ በ1 ሚሊየን ብር የሚገዙ 50 ሰዎች ካገኘን 50 ሚሊየን እናገኛለን።

በተጨማሪ ሎተሪዉ በዲጅታል አማራጭም ከተሸጠ ተጨማሪ ሰዉ የሚገዛዉ ይመስለኛል

ይህንን ካደረግን፣ በመላዉ ኢትዮጵያ ለሚኖረዉ ሕዝባችንና ለልማት ወዳድ ኢትዮጵያዉያ፣ ለዳያስፖራዉ፣ በከፍተኛ እርብርብ ከሸጥን በትንሹ፦ 350ሚሊየን ማሰባሰብ ይቻላል፣ የሕትመት ወጪዉ እንዳለ ሆኖ መንግስት ግብር እንዳይከፈልበት ብያግዝ፣ ከሽልማቱ በሁዋላ የተጣራ 300 ሚሊየን ብር ማሰባሰብ ይቻላል።

ሽልማት 10 ሚኒ ባስ፣ 10 የቤት መኪናና 30 ሞተር ሳይክል ቢደረግ፣ መንግስት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ካገዘ 50 የእድለኛ እጣ ይኖራል ማለት ነው። ባለሐብቶች ጀግሞ ለእጣ የሚሆኑ ነገሮችን በፈቃደኝነት ከለገሱ የእድለኛ ቁጥር መጨር ይቻላል። በዚህ መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ በቴሌዠዥኖች አጠያይቆ በነጻ ማስታወቂያ እንዲተላለፍ ከተደረገ፣ ከላይ ከተጠቀሰዉ በላይ ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል።

በተለይ ባለ 100ብሩን በብዙ ሚሊየን መሸጥ ይቻላል፣ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸዉን ደግሞ በቅድሚያ ሰዉ እየከፈለ የሚያገኝበት መንገድ ከተመቻቸ፣ በተለይ ተቋማት ወይንም በየተቋማቱ ያሉ ሰራተኞች እያዋጡ ከገዙ ብዙ መሸጥ የሚቻል ይመስለኛል።

በመላዉ ኢትዮጵያ ያለዉ የእስፖርቱ ማህበረሰብ ሎተሪዉን እንደየአቅሙ እንዲገዛ ቢደረግ፣ የተለያዩ ሚዲያ የእስፖርት ፕሮግራሞች ለአድማጭ ተመልካቶቻቸዉ እየገዙ በሽልማት መልክ ቢያስተላልፉ፣ በጥቂት ወራት ዉስጥ ግባችንን ማሳካት የሚቻል ይመስለኛል።

ይህ የሎተሪ ቲኬት ለእድል ብቻ የሚገዛ ሳይሆን በዎላይታ ሶዶ ለሚገነባዉ አለም አቀፍ ስቴዲየም የሚደረግ የአስተዋጽኦ ማረጋገጫ ሰነድም ስለሚሆን ታሪካዊ ነው። በባዶ ሰዉን ገንዘብ ለግሱ ከማለትም በሎተሪ መልክ መሸጡም የተሻለ ይመስለኛል። ይሕንን አሁኑኑ የዞኑ መንግስት ማድረግ የሚችል ይመስለኛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እንላለን🙏 በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Dichasport