ግለሰቡ “የርዕሰ መስተዳድሩን ስምና የፊርማ ቲቴር በቦርሳው ይዘው በመዞር የሹመት ሆነ ሌሎች ወሳኝ ደብዳቤዎችን በህገወጥ መንገድ እንደሚያወጣ” ተነገረ።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከዚሁ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በአሰራር ያላለፉ በመሆኑ ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን አረጋግጧል።
አንድ ሌለኛው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቅ ከፍተኛ አመራር እንደገለፁልን “አመራር ሲጀመር መሾም ያለበት የቤተሰብ ካምፓኒ ይመስል የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የስጋ ዘመድ የሆኑ አካላት እየተፈለጉ በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት በልምድና በሙያ ብቃት በተለያዬ ቦታ በሀላፊነት የሰሩበትና በቦታዉ ሊኖራቸዉ የሚገባ ዲስፕሊን ማሟላትንም ጭምር በትርጉም ተመዝኖ ለክልሉ ዉጠታማነትና ቀጣይነት ፋይዳዉ ብዙ ስለሆነ መሾም እየተገባቸዉ የርዕሰ መስተዳድሩ የአክስት ልጅ፣ የአጎት ልጅ፣ የምስት ወንድም እና በመሳሰሉ በስጋ ዝምድና እና በማህበራዊ ቁርኝት መነሻ በአመራር መስፈርት ዉስጥ ሊገቡ የማይገቡ ሀሳቦችን የአመራር መመልመያ መስፈርት አድርጎ በማምጣቱ አሁን ላለዉ ለክልሉ ብልሽት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ማንም የምናገረዉ የአደባባይ ሀቅ ነዉ” ብለዋል።
እኚህ አመራር ምክንያቱን ሲያስቀምጡ “ርዕሰ መስተዳድሩ ከአመራር ብስለትና ምግባር ራቁ እንጅ ለሳቸዉ ደህንነትም ይሁን ለክልሉ ተረጋግቶ ለመቀጥልም በርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በተለያዩ ሥራ ኃላፊነት ቦታ የሚሾሙ ሰዎች ከቦታዉ ሥራ ክብደትና ፍላጎት አንፃር በልዩ እይታ ከየትኛዉም ብሔር ይሁን ከይትኛዉ ማህበራዊ መሠረት ይሁን ውጤታማነታቸው ብቻ መስፈርት ተደርጎ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ በየዘርፉ የሚንመለከታቸዉ ለሰሚ ጆሮ ጭዉ የምል አሳፋሪ ሥራዎች ወይም ድርጊቶች ባልተፈፀሙ ነበር” በማለት ሁኔታውን አብራርተዋል።
ለአብነትም “የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፕሮቶኮልና ልዩ አማካሪ የሆኑት አቶ ባህሩ ሙላቱ በሥራ ልምድም ይሁን ከቦታዉ ከፍተኛነት አንፃር የልጁ ስነ-ምግባር ጉዳይም ለዛ በፍፁም የሚያበቃና የሚታሰብ አልነበረም፤ ነገር ግን የአቶ ጥላሁን አክስት ልጅ መሆኑ ብቻ የቦታዉ መስፈርት አደረገዉ እንጅ፤ ልጁ የትም ሲዞር ፈላጭ ቆራጭ እሱ እንደሆነ እና በመጠጥ ቤት በጭፈራ ቦታ አመራርን ከሚሾምና ከሚያወርድ ፓርቲ ማዕል አመራር ጋር አብሮ በመሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደሩ የስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ስላሌ አመራርን ከአመራር ምዘና እና ዲስፕሊን መመሪያ ዉጪ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ እየሰራ ነዉ የሚገኘዉ” ብለዋል።

“የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን በእሳቸው መፈረም ያለበትን ጉዳይ በቀጥታ ህጋዊ አሰራር ተከትለው በመፈረም እንዲሁም ሪከርድ ተደርገው በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ተደርገው ደብዳቤዎች እንዲወጡ እየተደረገ ባለበት ሀገር ከዚህ አሰራር ባፈነገጠ መንገድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን በተቃራኒው የእሳቸውን ስምና የፊርማ ቲቴር በእጁ ይዘው በመዞር በህገወጥ መንገድ ደብዳቤ ፕርንት አድርጎ እስከ መስጠት ኃላፊነት ይዞ መቀጠሉ በክልሉ ያለው ህገወጥነት ያለበት ደረጃ አመላካች ነው” በማለት ህገወጥ አሰራርን ተችተዋል።
አክለውም “ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ጉዳዮችን አሠራርን ሳይጠብቅ በአቋራጭ የርዕሰ መስተዳድሩ ይሁንታን እንደ ህግ በመቁጠር ከአሠራር ዉጪ በርዕሰ መስተዳድሩ ማስታዉሻ ብቻ የተግባሩ ባለቤት የሆነዉ ተቋምም ሆነ የአሠራርና አፈፃፀም መመሪያ ሳይከተል በብጣሽ ማስታወሻ የሳቸዉ የስም ቲቴር እየተመታ የሚሰራዉ የማዕድን ሥራ ፈቃድም ሆነ የተለያዩ የኮንቶርባንድ ሥራ ህደቶችና በህገ ወጥነት የተያዙ ሰዎችም ሆነ ንብረቱ የማስለቀቅና ህገ ወጥ ሥራ የሚፈፀመዉ በዚሁ ማህተሙን በእጁ ይዞ በሚንቀሳቀሰዉና አብዛኛው ጊዜ ከአዲስአበባ ሆኖ የሚሰራው በአቶ ባህሩ ሙላቱ መሆኑ ሁሉ የክልላችን አመራር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ” ብለዋል።
“እናዉቃለን ነገር ግን ከተናገርን እንጠፋለን ብሎ ዝም የተባለበት የአደባባይ ምስጥር ነዉ፤ ሌላዉን ብልሽት ይሄን ሚዲያ ተከታይ የሆኑ የተከበሩ ህዝቦችን ስለማይመጥን ለራሱ እንዲታረም በማስታወስ የሚታለፍ ስለሆነ ክቡር ሚዲያ ተከታዮቻችን ከልታረመና በትላንቱ ሥራዓት አልበኝነት የሚቀጥል ከሆነ በምስል የተደገፈ የሱነትንና የአለቆቹንም ጭምር እዉነተኛ ማንነታቸዉን የሚያሳይ የብልሽት መረጃ ሊናቀርብ የሚንገደድ መሆናችን ጭምር ለማስታወቅ እንወዳለን” በማለት ብልሹ አሰራርን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተጨማሪነት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አብዛኛው በተለይም የሹመት፣ የሽረት እንዲሁም በርዕሰ መስተዳድሩ ውሳኔና ፍርማ መውጣት ያለባቸው ደብዳቤዎች በመዝገብ ቤት በኩል ወጪ ገቢ አሰራር ያላለፉ ህገወጥ እንደሆኑና በዚሁም ምክንያት ሰራተኞቹ መረጃዎችን በተገቢው ለማደራጀት መቸገራቸውን ለማረጋገጥ ችሏል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲 🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ 🙌
በድጋሚ ለመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የአብሮነት፣ የሰላም፣ የመቻቻል እንዲሁም እርስበርስ የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን🙏
Ethiopia #southethiopia
የ