የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ስብራትና ብልሽት በተመለከተ በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ባሉ 6 ምሁራን የተደረገ አጭር ጥናት ይፋ ሆነ
በወቅታዊና ክልላዊ ጉዳይ ላይ በዲላ በጂንካ በአርባምንጭ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ምሁራን በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ዳሰሳ የተካተቱ ወጣቶች መምህራን ነጋዴዎችና አርሶአደሮቹን በአጭር መጠይቅ ተዘጋጅቶ በምስጢር የተካሄደ ነው ተብሏል።

እኚህ ምሁራን በአከባቢያቸው ሆኖው ያጠኑ ሲሆን በጋራ የጥናቱን ውጤት ለሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በኩል ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።
እነዚህ 6 ሙሁራን በአራቱ ዩኒቨርስቲ ያሉ በዶክትሬት ትምህርታቸው አብረው በዉጪ ሀገር ያሳለፉና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታን ተመልክተው መፍትሄ ለማስቀመጥ አልመው ያጠኑት እንደሆነ የጥናቱ አስተባባሪና በዲላ የኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ሲሆን ጉዳዩን በገለልተኝነት ለማድረግ እጅግ ጥንቃቄ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
የክልሉን ብልሽት በአንድ ቃል ተጠያቂዎች ምላሻቸው ላይ አካተዋል። ብልሽቱን የከፋ ያደረገው ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በስነምግባር ብልሽት ውስጥ መግባትና በሌብነት ሰንሰለት ውስጥ መውደቃቸው ዋነኛ ነው ይላሉ አስተባባሪው።
በመቀጠል የክልሉ የመንግስትና የፓርቲ ስራ ሙሉ በሙሉ የወደቀ ሲሆን የክልሉ ህዝብም በመንግስትና በፓርቲ ላይ እምነት እንደሌላቸው በተቻለ መጠን ብልፅግናን ከክልሉ በቀጣይ ምርጫ ለማስወገድ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ከጥናቱ ማግኘታቸውን ይገልፃሉ።
እንደ ጥናቱ ውጤት የክልሉ ብልሽት በመንግስትም በፓርቲም ደረጃ እጅግ የከፋ ያደረገው የክልሉ የፓርቲና አመራርና ርዕሰ መስተዳድሩ በተመሳሳይ ብልሽት ውስጥ መውደቃቸው አንዱ አንዱን የመናቅና የሁለቱም ተግባር ከውጤት ይልቅ ለሌብነት ቅድሚያ መስጠታቸው ነው።
አቶ ጥላሁንና የእሳቸው ሎሌ በክልሉ ባሉ ዞኖች ውስጥ በእሳቸው በቀጥታ የተሾሙ የየዞኑ አስተባባሪዎች አቅም የሌላቸው ህዝቡን የሚያጉላሉ በሌብነት የተዘፈቁ መሆናቸው ምሬቱ ሀገራዊ ገፅታ እንዲይዝ አድርጓል።
በክልሉ ወሳኝ የሚባሉ ቦታዎችን በቅርብ ዘመዳቸው ሹመት መስጠታቸውና በእሳቸው የተሾሙ ሁሉ በአለቃቸው በመተማመን የብልሽት ማዕከል ክልሉ እንዲሆን በማድረግ በእሳቸው የሚደገፍና በእሳቸው ትዕዛዝ የሚሰደዱ አመራርችም መኖሩ ክልሉ በሁለት ጎራ ተከፍሎ ወደ መበተን እየሄደ እንዳለም የጥናቱ አስተባባሪ ገልጿል።
በጥናቱ ያሉ መላ ምት ተብሎ የተቀመጡ ክልሉ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ እንዳለ ያገኙ ሲሆን ይህም የብልፅግና መንግስት ምናልባት ርዕሰ መስተዳድሩን አስቀርተው ሌሎችን አስተባባሪዎችን ብቻ በመበተን ሊወስዱ የሚችሉት እርምጃ መፍትሄ አካል ይሆናል የሚል አቅጣጫ ካለ በእርግጥ ህዝቡ ጥናቱ በተካሄደበት አከባቢ በከፊል አርባምንጭ ከተማን ጨምሮ እጅግ እሮሮ ባለበት በአስቸኳይ ሳይታረም የሚቀጥሉበት አዝማሚያ ካለ ክልሉ በእርግጠኝነት 100% የመፍረስ አደጋ እንደሚጋረጠው አረጋግጠናል ብለዋል።
አሁን ላይ በክልሉ ተንሰራፍቶ ያለው አድሎአዊ አሰራርና አንዱን ልጅ ሌላውን የእንጀራ ልጅ አድርጎ የሚሄዱበት አግባብ እጅግ የሚያንገሸግሽና ህዝቡ አይቀጤ ቅጣት በምርጫ ብቻ ለመቅጣት ቀን እየጠበቁ እንዳለ ከዚሁ ጥናት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።
የጥናቱ አስተባባሪ በመጨረሻም በሰጠው አስተያየት፦ “ምናልባት የብልፅግና መንግስት በአቶ በአደም ፋራህ በብልፅግና ምክትል ፕሬዝዳነት የተመራ ልኡክ በቂ ግንዛቤ ጨብጠው የሄደ በመሆኑ የፓርቲ ውግንና ካለ የህዝብ ውግንና ካለ በእርግጥም ፓርቲው ሰው ተኮር ከሆነ የክልሉን የመንግስትና የፓርቲ 6ቱ አስተባባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት” ብለዋል።
“በክልሉ የተገፉ እና የጥላሁንን የተሳሳተ አካሄድ የታገሉ አመራሮች ወደ ፊት እንዲመጡ ጭምር ጥናቱ መረጃ ከህዝቡ ማግኘቱን ከአስተባባሪው አግኝተናል” በማለት አክለዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southernethiopia