በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩና የቢሮ ኃላፊው ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እውቅና ውጪ በጥቅም ትስስር ህጋዊ አሰራርን በመጣስ ከ53 በላይ ፕሮጀክቶችን ለግለሰቦች ማስተላለፋቸው ተገለፀ።

በፖለቲካዉ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚዉም የፈረጠሙ ቱጃሩ ርዕሰ መስተዳድር “የብልፅግና ፓርቲ መነሻና መድረሻ ግቡ የሚመራዉን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ማሟላትና ጠንካራና ቅቡልነት ያለዉን ሀገረ መንግሰት መገንባት ነዉ” የሚለውን መሪ በተቃራኒው እየሄዱ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜ የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በመሆኑም ከገዢው ፓርቲዉ አመራር የሚጠበቀዉ የህዝቡን ህይወት ለመለወጥ ራሱን በመስጠት ጊዜዉ የሚፈልገዉን መስዋዕትነት በመክፈል የህዝቡን ብልፅግና ዕዉን ማድረግ እንደሆነ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በተጻረረ መልኩ ያለ ጠንካራ ኢኮኖሚ ስለ ፖለቲካ ማዉራት ዉጤት አልባ ቅዤት እንደሆነ የሚያምኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደ እምነታቸዉ ግላዊ ብልፅግና ካረጋገጡት ፖለቲከኞች ተርታ በቀላሉ መግባታቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
“ርዕሰ መስተዳድሩ በጣም ብልጥና ሴራ የሚችሉ በመሆናቸዉ ለስልጣን ቆይታ የሚያግዙ አካላትንና ለስልጣን እንድመጡ ከፍተኛ ዉሌታ የዋለሉላቸዉን በቁጥር ሁለት የሚሆኑ ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናትና ተፅዕኖ ልፈጥሩ የሚችሉ ባለሀብቶችን የጥረታቸዉን ትሩፋት እንድቋደሱ በማድረጋቸዉ የቆይታ መተማመኛ እንዳገኙ የዉስጥ አዋቂ መረጃ ይጠቁማል፡፡
በተጨማርም የወቅቱ ኒዩክሌር የሆነዉን ሚዲያ ሠራዊት በማደራጀት ከሾመዉ ፓርቲ በላይ የግል ገጽታ ግንባታ ላይ አተኩረዉ እንድሰሩ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም እኝዉ ምንጫችን ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የትኛዉንም ዓይነት ጥፋት ብያጠፉ እንኳን በቀላሉ ተጠያቂ እንደማይሆኑና ከስልጣን እንደማይነሱ ዕምነታቸዉ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
“ለሀብታቸዉ እንደምንጭ የተጠቀሙት ስልጣናቸዉን መከታ በማድረግ ከባለሀብቶች ጋር በመመሳጠር የከተማ እና የገጠር ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች፤ ባለቤት አልባ ማህበራት አማካይነት የድንጋይ ከሰል ምርት እና ህጋዊ በሚመስሉ አካሄዶች ለግለሰቦችና ለተቋማት ከመንግስት ካዜና በሚደረጉ ድጋፎች ስሆን በተጨማር በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከተሰማሩ ከመንግስት ልማት ድርጅቶችና በቦርድ ሰብሳቢነት ከሚመራዉ ከኦሞ ባንክ ነዉ” ይላል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በስማቸውና በዘመዶቹ በአርባምንጭ፤ በሀዋሳ እና በአድስ አበባ ያሉትን የሚመለከተዉ አካል በራሱ መንገድ ማጣራት የሚችል ስሆን ስለዝርዝር መረጃ ድጋፍ ከተፈለገ ሚድያችን ዝግጁ መሆኑን ከወድሁ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
ከዛ ዉጭ በትንሹ ለማሳየት ያኪል ከክልሉ መንግስት ካዜና 3,000,000 (ሦስት ሚሊዮን) ብር ድጋፍ ለፓራዳይዝ ሎጅ ባለቤት ለሆኑት ለአቶ ኢያሱ የተሰጠዉን እና በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ከተማ ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እውቅና ውጪ 103,410.3 ካሜ የመሬት መጠን ያላቸዉ በቁጥር 53 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በአቶ ጥላሁን ከበደ እና በአቶ ብርሃኑ ዘዉዴ አማካይነት አሰራርን ባልተከተለ መልኩ የተላለፈ ስለመሆኑ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
የፕሮጀክቶቹ ስም ዝርዝር እንደሚከተለዉ የቀረበ ስሆን ከድንጋይ ከሰል ጋር የተያያዙ ምዝበራዎች ሰፋ ያሉ በመሆናቸዉ ሌላ ጊዜ በዝርዝር የሚናቀርበዉ ይሆናል፡፡
ተራ ቁ የፕሮጄክቱ ስም የኢንቨስትምንት ዘርፍ
1 ግሩም ሙሉጌታ ሎጅ
2 ሐምሌት አሰፋ ደምሴ ትምህርት
3 ይመኙ የስሐቅ ነዳጅ ማደያ
4 ደጉ ደበበ ዘመናዊ ገ/ማዕከል
5 ጳውሎስ ማራ ሆቴል
6 አቶ ከድር የሱፍ ሁለ ገብ ንግድ ማዕከል
7 ጉጌ ቴክ ኢን/ኃ/የተ/የግ/ማ ሎጅ
8 ወ/ሮ ሮማን ፀጋዩ ሁለ ገብ ንግድ ማዕከል
9 ወ/ሮ አብነት በቀለ ትምህርት(አፀደ ሕፃናት)
10 አንጊ ፔትሮሊየም ኃ/የተ/የግ ማህበር ሞቴል
11 ኦሞቲክ ጠ/ንግድ ሞቴል
12 ነጋሳ ተራራ ምንጭ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
13 በፍቃዱ በቀለ ሁለገብ የንግድ ማዕከልና ዘመናዊ ማተሚያ ቤት
14 ወ/ሮ ካሰች ከበደ 1ኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
15 ጌትነት አስቻለው አበራ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
16 አለማየሁ ጎንጮ ሆቴል
17 አቶ ውዝፌ ውዳ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
18 አቶ ገረመው ዓለሙ ንግድና የመዝናኛ ፓርክ
19 አቶ ወንድሙ አስቻለው Recreational Park
20 አቶ መስቀሌ ደስታ ሴሎ ነዳጅ ማደያ
21 አቶ ፍሬው በለጠ በፍቃዱ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
22 ሂዶታ ፎኦ ቱሪስት ሆቴል መ/ህ/ሥ/ማህበር ሆቴል
23 አቶ ሙሉዓለም መስፍን ሁለገብ የንግድ ማዕከል
24 አቶ ዳንኤል ታምራት ሞቴል
25 ዳማ ህንጻ ስዎች መ/ህ/ሥ/ማህበር ሁለገብ የንግድ ማዕከል
26 ባሶ ህንጻ ስራዎች መ/ህ/ሥ/ማህበር ሁለገብ የንግድ ማዕከል
27 ሳታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ ግንባታ
28 አቶ አብረሐም አንጁሎ ሞቴል
29 አቶ መሰለ ዳንኤል ሻጎ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
30 አቶ ሚልኪያስ አንዴቦ ባለ 4ኮከብ ሪዞርት ሆቴል
31 ባምባላ ሁለገብ የንግድ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
32 ወ/ሮ ሰላም ፀጋው ቅይጥ ንግድ ማዕከል
33 ወ/ሮ አለምነሽ አሉላ የባህል ምግብ አዳራሽና
34 አቶ ቆንጬ ሁለታ ባለ አራት ፎቅ ቅይጥ
35 አቶ ዱባለ ዱፎ ባለ አራት ፎቅ ቅይጥ ህንፃ
36 ወ/ሮ ዮዲት ኃ/ሚካኤል ሁለገብ የንግድ ማዕከል
37 ዘመን ቡድን ሁለገብ የገበያ ሁለገብ የገበያ ማእከል
38 አቶ ሙሉዓለም መኮንን ሁለገብ የንግድ ማዕከል
39 ወ/ሮ አታክልት አካሉ ባለ 4ፎቅ ቅይጥ ህንጻ ግንባታ
40 ወ/ሮ ፈትለወርቅ አሰፋ ሆቴል
41 አቶ አዲሱ አናራ ባለ 2ኮከብ ሆቴል
42 አቶ ባህሩ ሲሳይ ሽፈራ ባለ 2ኮከብ ሆቴል
43 አቶ አማረ አንካላ/አማንዝ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል
44 አቶ ሞገስ አንጁሎ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5
45 ወ/ሮ ሀረገወይን ወ/ዮሐንስ አጸደ ህጻናት እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
46 አቶ በስልጣኑ ጌታቸው ባለ 2ኮከብ ሆቴል
47 አቶ ጌቱ ለማ ነማጌ ባለ 2ኮከብ ሆቴል
48 ዶ/ር ግዛቸው ጊያ ሁለገብ የንግድ ማዕከል
49 አቶ ገበየሁ ይመር ባለ አራት ዘመናዊ ህንጻ
50 አቶ ታደለ አባተ ቅይጥ ህንጻ
51 ቅዱስ ገብርኤል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
52 ነጭ ሣር ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
53 አቶ ዮናስ ዘውዴ ባለ ሁለት ኮከብ ሆቴል
ለዛሬው ከብዙ ጥቂቱን ለማሳያነት ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እውቅና ውጪ የተላለፉ 53 ፕሮጀክቶቹን ስም ዝርዝር ከላይ እንደሚከተለዉ የቀረበ ስሆን ከድንጋይ ከሰል ጋር የተያያዙ ምዝበራዎች ሰፋ ያሉ በመሆናቸዉ ሌላ ጊዜ በዝርዝር ከማቅረብ ባሻገር ርዕሰ መስተዳድሩ ወደ ክልል ፕረዚዳንትነት ስልጣን ከመጡ ጥቂት አመታት ውሰጥ በስማቸውና በዘመዶቻቸው በአርባምንጭ፤ በሀዋሳ እና በአድስ አበባ ያሉትን የሚመለከተዉ አካል በራሱ መንገድ ማጣራት የሚችል ስሆን ስለ ዝርዝር መረጃ ድጋፍ ከተፈለገ ሚድያችን ዝግጁ መሆኑን ከወዲሁ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #arbaminch