1000035078

ማስታወቂያ 👇

እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል። – ትንቢት ዘካሪያስ 14:9

ገንደባ ቤቴል፣ ዎላይታ ሶዶ – ኢትዮጵያ 🙏

“ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።” – 1 ዜና 16፥29

በኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን የዎላይታ ሰበካ ከጥር 22/17 እስከ ጥር 25/17 ዓ.ም ድረስ 18ኛው ዙር አመታዊ ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ያካሂዳል።

በዚሁ ኮንፍራንስ የሚሳተፉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ሐሙስ ዕለት ከየአቅጣጫው በተመሳሳይ ሰዓት በከተማዋ በሁሉም መግቢያዎች በሰልፍ በመግባት እስከ ገንደባ ቤቴል ድረስ ለፈጣሪ ምስጋና፣ ዝማሬ እንዲሁም ፀሎት እያደረጉ በእግር ጉዞ ፕሮግራሙን እዚያው በይፍ ይጀምራሉ ተብሏል።

የሰላምና ለሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት በሆነችው #ዎላይታ #ሶዶ #ከተማ ላይ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዎላይታ ሰበካ ከጥር 22 እሰከ 25/17 ዓ.ም ድረስ በሚያካሂዱት ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ምዕመናንና ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች ከዎላይታ፣ አጎራባች ዞኖችና ክልሎች አንዲሁም ከተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ያለልዩነት ቀኑን በጉጉት ጠብቀው የሚሰበሰቡበት ጉባኤ ይካሄዳል።

በኮንፈረንሱም ምዕመናኑ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለፈጣሪያቸው ፀሎትና ምልጃ የሚያደረሱበት ዓመታዊ ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በየጊዜው የኃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በአከባቢው የሚያበረክቱት አውንታዊ ሚና ለኮንፍራንስ ቱሪዝም ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ ዜጎችን በመልካም ስነምግባር በማነፅ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

ኑ የበረከቱ ተካፋዮች ሁኑ፤ ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል 🙌

ከሐሙስ እስከ እሁድ ወንጌል በስልጣን ይሰበካል 🙌

በጉባኤው መንፈስ ቅዱስ በኃይል ይወርዳል፤ ኢየሱስ በእውነትና በመንፈስ ይመለካል 🙌

አድራሻ፡- ከዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 400 ሜትር ወረድ ብሎ ባለው በሰፊው ገንደባ ሜዳ ላይ🙏

የኢትዮጵያ #ሐዋሪያዊት #ቤተክርስቲያን🙏

Apostolic #Church of #Ethiopia 🙏

GENDEBA #BETHEL #WOLAITA2025