በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው
“የዎላይታ ዞን አስተዳደር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነት ለክልል አሳልፎ መስጠት ጭንቅላት የተቆረጠውን ሰውነት መሸከም ማለት ነው” – ባለሙያዎች
ሰሞኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዎላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ከተሞች ሪጅዮፖሊታን ከተማ ሆኖ እንዲደራጁ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ተጠሪነታቸውም ለክልሉ ይሆናል መባሉን ተከትሎ ከተለያዩ አካላት ከፍተኛ ተቋውሞ እየተሰማ ይገኛል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ ከተለያዩ ባለሙያዎች እንዲሁም ሁኔታውን በቅርበት ከሚከታተሉ አመራሮችና ግለሰቦች ሀሳቦችንና መፍትሔ አቅጣጫዎችን አሰባስቧል።
በተለይም በክልሉ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ 100% በራሷ የውስጥ ገቢ የምትዳደር፣ በህዝብ ቁጥር ሆነ በኢኮኖሚያዊው አበርክቶ አንፃር ከፍተኛ ድርሻ ባለችው ዎላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ የጠየቅናቸው ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት “የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከፈርጀ አንድ ደረጃ ወደ ሪጅዮኦፖሊትነት ከፍ ማለቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ክርክር ባይነሳም በተቃራኒው በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠርነት ለክልሉ ነው የሚል ድንጋጌ መቀመጡ አዝማሚያው ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ኢህገመንግስታዊ ነው” ይላሉ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲደራጅ አደራጅ አካላት ትኩረት ያደረጉት እንዴት ዎላይታን እጅእግሩን በማሰር የነበሩ ልማቶችን እንደሚቀሙና ወደፊትም በምንም መልኩ እንዳይለማ እንዴት እንደሚሠሩ ተማምለው ነው። በመሐላቸው መሠረት ይህ ክልል ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ የቦዲቲ የአረካ ከተሞችን ከዓለም ባንክ ፕሮግራም ተጠቃሚነት ማስወጣት ጨምሮ ቀደም ሲል በእጁ የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ነጥቀው ለሌሎች አስተላልፈዋል ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁኔታዎችን በቅርበት የተከታተሉ አመራር አስረድተዋል።

በቢሮ ድልደላ እና በአመራር ምደባ ከፍተኛ በደል ተፈፅሟል አሁንም ቀጥሏል። ክልላዊና ሀገራዊ ዝግጅቶች በዎላይታ እንዳይደረጉ፣ በሶዶ ከተማ የተጀመረው መንገድ ፕሮጀክት እና የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት እንዲሰናከል ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ። የዎላይታ ተወላጅ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ቢሮዎች እንዳይመደቡ፣ የተመደቡትም ያለ ምክንያት እንዲፈናቀሉ በይፋ እየተሠራ እንደሚገኝ አስተያየት ሰጪ ጠቁመዋል።
ዎላይታ ከሰሜን ኦሞ ትብታብ ከተፈታ በኋላ ያለማንም ድጋፍ ከሕዝቡ በሰበሰበው እና በዎላይታዊያን ጥረትና ድካም ፈጣሪም ጥቂቱን ባርኮ ከተማ ሊመስል ችሏል። ይህ ያስቆጫቸው እና ሕዝቡን በጎሪጥ ሲመለከቱ የከረሙት የትኛውም ልማት በዎላይታ ሲሰራ የሚያንገበግባቸው አካላት ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመዘዋወር ሥልጣን ማግኘቱን አስታውሰዋል።
አክለውም፦ አሁን ደግሞ ይዘው የተነሱት የዎላይታ ሕዝብ የዓይኑ ብለን የሆነውን ከተማ በመንጠቅ ዳግማዊ ዎጋጎዳ ለማንሰራራተሰ ላይ ታች እያሉ ነው። ሪጂኦፖሊታን ለማወጅ የቸኮሉ አካላት የክልሉ መንግሥት መቀመጫ የሆነው የዎላይታ ሶዶ ከተማ ስሙ በክልሉ ሕገመንግስት በግልጽ እንዳይጠቀሰ ሽንጣቸው ገትሮ የሚሞግቱ፣ ዎላይታ ሶዶ ከተማ የክልሉ ዋና መቀመጫ ከሆነ የሐይቅ አዞ ይብላን ብለው የተገዘቱ፣ ከዎላይታ ጋር በሰማይ በምድር አንገናኝም ያሉ አካላት ናቸው” ብለዋል።
የሪጂዮፖሊታን ዋናው ውጥን የዎላይታ ሕዝብ የታሪኩ፣ የፖለቲካው፣ የእምነቱ፣ የተስፋው፣ የከፍታው ማዕከልና ማጠንጠኛ የሆነችውን የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነት ለክልሉ ማድረግ ከህዝብ እጁ በመንጠቅ ለሴራኞች የማስረከብ ግልጽ አጀንዳ ነው። በዚሁ አደረጃጀት ከጅምሩ ዎላይታ ጠል ክልላዊ ኃይላት በዎላይታ ጉዳይ እንደፈለጉ እጅ እየሰደዱ እንዲፈተፍቱና በሂደትም የዎላይታን ብሄርተኝነት፣ ቋንቋውን፣ ታሪኩንና ባህሉን በማክሰም ዎላይታነት ከምድረገፅ እንዲጠፋ የተወነጠ ፕሮጀክት እንደሆነም በማስረዳት።
“የሶዶ ከተማ የዎላይታ የሁሉም ነገር ማዕከል ነው። ከተማውን ከዎላይታ አመራር እጅ ነጥቀው ተጠሪነቷን ለጥላሁን እና ለብርሃኑ ለማድረግ ነው። ከዚህ በኋላ እያንዳንዱ የሶዶ ከተማ ጉዳይ የዞኑ ምክር ቤት ሳይወስነው በከተማ ልማት ይሁንታ የሚፈፀም ነው የሚሆነው። የዞኑ ምክር ቤት መክሮበት የወሰነው ነገር ሳይኖር የዎላይታ ሶዶ ከተማ ለአደገኛው የክልል መዋቅር ማስረከብ መዘዙ ብዙ እንድምታዉ አደገኛ ነው” በማለትም አስረድተዋል።
“ዎላይታ ሶዶ ከተማ የመልማት ጭላንጭል የታየው ከሰሜን ኦሞዎቹ መዋቅር እጅ ከወጣች በኋላ ነው። አሁን መልሰው እያስረከቡ ነው። ምክያቱ ደግሞ ሶዶ ከተማ ከዞኑ ጋር ከኢኮኖሚው ሆነ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ አንፃር ዕኩል ስታተስ ስለሚኖረው ያንን ሥልጣን ለመቀራመት ነው። ይህ ጉዳይ እጅግ የሚያስብና ትኩረት የሚፈልግ ነው። ጥንቃቄ የሚሻ ጉዱይም ነው። በሂደትም የክልል ጥያቄአችን ላይ አደጋ የሚደቅን ነው። ምክያቱም የክልል ጥያቄ በሁለት የተለያየ መዋቅር ሆኖ አደራጅቶ ማስከሄድ አደጋም አለው” ይላሉ።
በተጨማሪም አልፎም ጥቂት የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም የዎላይታ ሕዝብና አመራሩን በመከፋፈል አከባቢው እንዳይረጋጋ፣ ምንም ዓይነት ክልላዊ ፕሮጀክት በዞኑ እንዳይሰራ ያለ ዕረፍት እየተጉ ይገኛሉ። የክልሉን በጀት ከሕግና አሠራር ውጭ በመጠቀም ለአንድ አከባቢ አድልተው እየሰሩ እየመዘበሩም እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ፦ “ችግሩ የሚመነጨው ከህገመንግስቱ ነው። የክልሉ ዋና ከተማ ያልሰየመ ብቸኛው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህገመንግስት ነው። ስለ 6ቱ ማዕከላት እንጂ ስለ ዋና ከተማ አያወራም። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ ነው የተደረገው። የክልሉ “ዋና ከተማ” እና “ማዕከላት” በጽንጸ ሀሳብ ይለያያሉ። ሀገርም ይሁን ክልል ዋና ከተማ መሰየም ግዴታ ነው። ማእከላት በሚሰጡት አገልግሎት የተለያዩ እና ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ” ብሏል።
“ለምሳሌ በዚህ በጀት አመት 3ቱ ከተሞች እኩል ናቸው በሚል እሳቤ ካፒታል በጀት ተብሎ ለእያንዳንዳቸው 80 ሚሊዮን ነው የተመደበው። ይህ አግባቢ አይደለም። ዲላ በራሱ መጠን ማግኘት አለበት እንጂ ከአርባምንጭ ጋር እኩል ማግኘት የለበትም። የክልሉ ርዕሰ መዲናና ዋና ከተማ ከሆነች ተያይዞ የሚመጡ መዋቅሮችንም ሆነ አገለግሎቶች የማግኘት መብት መረጋገጥ አለበት። ማንም ይሁን ማን ክልሉ የሚታወቅ በህግ የተደነገገ አንድ ዋና ከተማ መኖር አለበት። ከዛ ውጪ የተለያዪ ማእከላትና የከተማ ፈርጆች ሊኖሩ ይችላሉ። ከተሞች የፋብሪካ ምርት አይደሉም። የራሳቸው ታርክ፣ ያከማቹት ሀብት፣ የተፈጥሮ ምቹነት፣ የነዋሪው ጥረትና መሪነት ሚና መጠን የእድገት ደረጃቸው ይለያያል። ይህን ሀቅ የማይቀበል ህዝብን መምራት የለበትም” ብሏል።
“በአለመአቀፍም ሆነ በአገርአቀፍ መስፈርቶች ዎላይታ ሶዶ በአዋጁ ከተጠቀሱ ከተሞች በብዙ ስለሚትበልጥ እና ይህንን ሀቅ የማይቀበሉ ፖለትከኞች ለጊዜው ባገኙት ስልጣን አድበስብሰው እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት እየሰሩ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው በሚል አክለዋል።
የዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጠሪነቱ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ለማድረግ ማሳብ የሀገሪቱን ሕገመንግስት የሚጻረርና የዎላይታን ሕዝብ የሚጎዳ አደገኛ ውሳኔ በመሆኑ ዳግም ሊጠን ይገባል፤ ምክንያቱም የከተማዋን መፃኢ ዕድል የመወሰን ስልጣኑ የዎላይታ ሕዝብ በተለይም የዞኑ፣ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ምክር ቤት እና የዎላይታ ብሔር ምክር ቤት እንጂ የክልሉ ካቢኔ ወይም ሌሎች ብሔረሰቦች ስለከተማችን ሊወስኑ አይገባም” ብሏል።
በመሆኑም በአጠቃላይ ያነጋገርናቸው አካላት የሰጡት ማብራሪያ “የዎላይታ ዞን አስተዳደር የዎላይታ ከተማ ተጠሪነት ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠትን በአጭር ቃል ሲገለፅ፦ ጭንቅላት የተቆረጠው ሰውነትት መሸከም መሆኑን ተረድቶ ከተማውን አሳልፎ ከመስጠት መቆጠብ አለበት። ለችግሩ ዋነኛ መፍትሔ የራስን ክልላዊ መስተዳድር መመስረት ነው። የዞኑ አመራሮች ትግሉን ማቀጣጠል አለባቸው። መላው የዎላይታ ሕዝብ፣ ሲቢል ሰርቫንቱ፣ ወጣቱ፣ ምሁሩ፣ ነጋዴው አርሶ አደሩ በሀገር ውስጥ በውጭ ያለው ሁሉ ዎላይታ ዳግማዊ ዎጋጎዳ ከሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥፍነጋ እስር ቤት ወጥቶ የራሱን ክልል የመመስረት ትግል ዳግም አዲሶ እንዲጀምር ሕዝባዊ ጥሪ መቅረብ አለበትም ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ከቀናት በፊት የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሥራ አስፈፃሚ በላከልን መግለጫ ክልሉ “እንደ ክልል በጋራ አጀንዳ ከመምከር እና ሕግ ከማውጣት ውጪ የአንድ ብሔርን የዘመናት ልፋት እና ጥረት የሆነውን ከተማ ተጠሪነቱን ከብሔሩ ምክር ቤት በመቀማት የክልሉ ምክር ቤት ለዚያውም የብሔሩ ውክልና በሌላቸው ተወካዮች ተጠሪነት ስር ማድረግ በሕገመንግስት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሥት የተደነገገውን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ከመቀማት ባሻገር የዴሞክራሲ ምሶሶ የሆነውን የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን እና የማስተዳደር የሕዝብ ልዕልናን የሚገረስስ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ መሆኑ አጽንኦት ልሰጥበት ይገባል” ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል።
መግለጫው በተጨማሪም የክልሉ መንግስት የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ክትትል እና ድጋፍ ከማድረግ የዘለለ ያለ ብሔሩ ዕወቅና ያልተወከሉ የሌሎች ብሔር አባላት በጋራ ያቋቋሙት ምክር ቤት የተጠሪነት ሚና ሊኖረው የማይገባ መሆኑን በመግለፅ ጉዳይ በማንአለብኝነት እምቢ ተብሎ እንድሁም ይህ አዋጅ የፓርቲውን አስተያየት ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ሳይሻሻል የሚጸድቅ ከሆነ ፓርቲችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ የአዋጁ ሕጋዊነትን የማይቀበል ከመሆኑም ባለፈ የክልሉን ምክር ቤት እና ሕግ አውጪውን አካል በህግ የሚከስ መሆኑንና አዋጁም ከተፈጻሚነት ሊታገድ የሚችል መሆኑ ሊታወቅ የሚገባ መሆኑን በአንክሮ የምናስገነዝብ ሲሆን የአዋጁን ጉዳይ ፓርቲያችንና መላው የዎላይታ ሕዝብ እስከመጨረሻው በአጽንኦት የሚከታተል መሆኑንም ጭምር አጥብቀን እንገልጻለን” በሚል ጠንካራ አቋም መያዙን ዘግበናል።
ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በጉዳዩ ዙሪያ የሶዶ ከተማ አመራሮች፣ የዞኑ አመራሮች እንዲሁም አንዳንድ በክልል ደረጃ የሚገኙም ባለመስማማት እሰጥአገባ ውስጥ እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን የተሟላ መረጃ እንዳገኘን እንደምናቀርብ ከወዲሁ ለመጠቆም እንወዳለን።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
Ethiopia #southernethiopia
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው