አርሶአደሮች ለዘመናት አርሰው ከሚበሉበት ለም መሬታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ቤተሰቦቻቸው በመበተኑና ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ተስፋ ቆርጠው እስካሁን ከ4 በላይ አርሶአደሮች ራሳቸውን እስከማጥፋት መድረሱ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ አረካ ከተማ አቅራቢያ ሱማሞ ሜዳ ላይ ሊገነባ የታቀደው አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ መክፈል ባለመፈለጉ የግንባታ ሂደቱ ከመስተጓጎሉ በተጨማሪ የመሬታቸው የተነሱ አርሶአደሮች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው አሳሳቢ ስለመሆኑም ተገልጿል።
በሌላ በኩል ከቦታው ለሚነሱ አርሶአደሮች ለመስጠት የተገመተው የካሳ ክፊያ መጠን በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ቅሬታ በሚያቀርቡ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ የግድያ፣ የእስርና የማስፈራራት ጥቃት እየደረሰባቸው እንዲሁም ለዘመናት አርሰው ከሚበሉበት ይዞታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በመበተኑና ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ተስፋ ቆርጠው እስካሁን ከ4 በላይ አርሶአደሮች ራሳቸውን እስከማጥፋት እንዳደረሱ በመጥቀስ ስለሆነ የፌደራል መንግስት ጠልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።
ከአስር ወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ለመንንባት አቅዶ የቦታ መረጣ በማድረግ በቅርቡ ወደ ስራ ለመግባት በፕላን መሰረት በይዞታ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውም ንብረቶች አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ በመፈፀም እና ከቦታው ለሚነሱ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተለዋጭ ቦታ በመስጠት ቦታውን ከይዞታ ነፃ ተደርጎ የይዞታ ማረጋገጫ በአስቸኳይ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሶ ለክልሉ በፃፉት ደብዳቤ ማሳሰባቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ሆኖም ግን እንደተባለውም ተቋራጮቹ ክልሉን “በአንድ አመት አጠናቀን እናስረክባለን ቦታውን ከይገባኛል ነፃ አድርጉልኝ” ካሉ 9 ወር አልፏል፤ ከክልሉ እንዲሸፈን የተጠየቀው 130 ሚሊየን ብር ብቻ የካሳ ገንዘብ ቢሆንም ትኩረት ተነፍጎ ክልሉ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ በጊዜው መክፈል ባለመፈለጉ ሂደቱ እንዲስተጓጎል ማድረጉ በአከባቢው ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠረ ስለመሆኑ ተገልጿል።
የግንባታ ሂደቱን ቶሎ ለማስጀመር የፕሮጀክቱ ስራ በሚከናወንበት አከባቢ ንብረትና ቤት ያላቸው አርሶአደሮችን ለማስነሳት ኮሚቴው ተዋቅሮ ስራ ውስጥ የገባ ቢሆንም ሆን ተብሎ በየትኛውም ቦታ ታይቶ የማያውቅ የአርሶአደሩን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ግምት ከ40ሺህ-140ሺህ ብር በሚገመትበት ሁኔታ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙትን መግደል፣ ማሰር እንዲሁም ከፍተኛ ማስፈራሪያ እያደረሱ ስለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አርሶአደር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

በርካታ የአከባቢው አርሶአደሮች ለዘመናት አርሶ ከሚበሉበት መሬታቸው ቢነሱም ተገቢ ካሳ ባለመሰጠቱ ቤተሰቦቻቸው በመበተኑ ተስፋ በመቁረጥ እስካሁን ከአራት በላይ ራሳቸውን እስከማ’ጥፋት መድረሱንም አክለዋል።
ከሁለት አመት በፊት ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው አየር ማረፊያ ግንባታ እንዲቋረጥ ተደርገው በአንድ አመት ለማጠናቀቅ የተጀመረው ይሄው አዲሱ የሱማሞ አየር ማረፊያ ግንባታም በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ ክልሉ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር የካሳ ክፊያ ውዝግብ በመፍጠር እንዲሁም ትኩረት በመንፈግ የካሳ ክፊያ በመከልከል እንዲስተጓጎል እያደረገ ስለመሆኑ አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምሁር ለWT ጠቁመዋል።
የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ1950ዎቹ እስከ 1970ዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው የነበረ ሲሆን የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በ1999 የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉንም ምሁሩ ገልጸዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏