1000035989

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ጋር በፍሪታውን በሚገኘው ቤተመንግሥት ላይ ባደረጉት ውይይት የአገሪቱን የምግብ ዋስትና፣ የስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን የሚተገብር ፕሮግራም “ፊድ ሳሎኔ” (Feed Salone) ተነሳሽነት ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

አቶ ኃይለማርያም እንደገለጹት፣ “AGRA ከአፍሪካ መንግስታት ጋር በመተባበር የግብርና ልማትን ለማጎልበት እና የህዝብን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ለዘርፉ ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ ቁርጠኛ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም ሴራሊዮን በግብርና ምርታማነት ማሳደግ፣ የግብርና ሜካናይዝሽን አጠቃቀምን ማስፋፋት እና የምርት ሰንሰለቶችን በማጠናከር ራስን በራስ ለመቻል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለሌሎች ምሳሌያዊ እንደሆነም አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ጁሊየስ በበኩላቸው፣ “የ’ፊድ ሳሎኔ’ ተነሳሽነት ለአገራችን ኢኮኖሚ ወሳኝ ነው። በግብርና ውስጥ ያለውን ዘዴ በማዘመን፣ ለወጣቶች ስራ ለመፍጠር እና የገቢ ምንጮችን ያሳድጋል” ብለዋል።

የአገሪቱ መንግስት በግብርና ላይ ያተኮረው ይህ ስትራቴጂ የተለያዩ የልማት አጋሮችን፣ የቴክኖሎጂ አቅርቦቶችን እና የገንዘብ መድረኮችን በማስተባበር አገር አቀፍ የሆነ የምግብ ነፃነት እንዲዘረጋ እየተሰራ ሲሆን በአፍሪካ ውስጥ የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ለማራመድ የሚደረጉ ስራዎችን የሚያጠናክር እንደሆነም ተገልጿል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #SierraLeone